“የአማራ ህዝብ ተሸንፎ ወሎ ተያዘ የሚለው ፌዝ ነው” – ታዲዮስ ታንቱ

247242225 421976382662381 2655960943504952850 n 300x266 የአማራ ህዝብ ተሸንፎ ወሎ ተያዘ የሚለው ፌዝ ነው  ታዲዮስ ታንቱ

የተከበሩ ታዲዮስ ታንቱ እንዲህ ብለዋል:- “የአማራ ህዝብ ተሸንፎ ወሎ ተያዘ የሚለው ፌዝ ነው”::ከኝህ ሊቅ ጋር በጣም እስማማለሁ::

እና ታዲዮስ ታንቱ “የአማራ ህዝብ ተሸንፎ ወሎ ተያዘ የሚለው ፌዝ ነው” ለምን አሉ? ታዲዮስ ታንቱ በሰጡት ማብራሪያ ላይ አማራ ላይ እየተሰራ ያለዉን ደባ አብራርተዋል::

አማራዉ በደባ እንጂ በጦርነት ከቶም እንደማይሸነፍ አስረግጠዉ ገልጸዋል::

ታዲዮስ ታንቱ ይሄን ያሉት አማራ ጦር ሲገጥም ምን አይነት ባህሪ እንዳለዉ ስለሚያዉቁ ነዉ::አማራን በደባ እና በተንኮል እንዲሁም በክህደት በደንብ ታሸንፈዋለሁ::ፊት ለፊት በጦር ግን አታሸንፈዉም::

በጣም የሚገርም ሌላም ነገር አክለዉ ገልጸዋል:: “ጦርነት ባላስፈለገ ነበር:: ግን አንዴ ሆኖል” ሲሉ ገልጸዋል::

እዉነታቸዉ ነዉ::ጦርነት ባላስፈለገ ነበር ግን አንዴ ሆኗል:: እናም ሀይለኛ ተዋጊ ህዝብ ይዞ እንደ ህዉሃት አይነት ምናምንቴ እና አጭበርባሪ ሀይል አማራን አሸነፈዉ ማለት አይቻልም::ነዉርም ነዉ::

ህዉሃት ባንዳነት:ተላላኪነት: ጥላቻ መስበክ:ተንኮል መስራት:የሌሎች ነገዶችን ዘር ማጥፋት:አንዱን ነገድ ከሌላዉ ነገድ ማጋጨት ብሎም ወንድም የሆነዉን የትግራይ ህዝብ ከወንድሙ የአማራ ህዝብ ጋር ለዘለዓለም ደም ማቃባት የተካነበት ክህሎቱ ነዉ::

ህዉሃት ጦር ገጥሞ ግን በትክክለኛ ዉጊያ በታሪክ አሸንፎ አያዉቅም::ወደ ስልጣን ከሰላሳ አመት በፊትም የመጣዉ በሻዕቢያ ጀርባ ተንጠልጥሎ:በአረብ እና በምዕራባዊ ጸረ ኢትዮጵያዊነት ብሎም ጸረ ሻሊስትነት ደመና ተሳፍሮ ነዉ::

ከዚያ ዉጭ ግን ህዉሃት እንደ ዱር ዉሻ አይነት ባህሪ ያለዉ ፍጥረት ነዉ::

ስለዚህም ታዲዮስ ታንቱ እንዳሉት ጦርነት ባላስፈለገ ነበር ግን አንዴ ሆኗልና የህዝብ መሪ ነን የምትሉ ሁሉ ሚስጢሩን ጠብቃችሁ አማራዉን አዋጉት::ህዉሃትን እንደ ጉም ያተናታል::

ታዲዮስ ታንቱ እናዳሉትም ጦርነት ባላስፈለገ ነበር ግን ሆኗልና ጦርነቱን በአግባቡ ምሩት እንጂ ለዉጊያዉስ ህዝቡ ይጨርሰዋል:: የአማራ ህዝብ ተሸንፎ ወሎ ተያዘ የሚለው ፌዝ ነውና ይሄን ፌዛችሁን በቀናት ዉስጥ ቀልብሱት::

ይሄ ፌዝ የሚቀለበሰዉ ግን የሰራዊት አደረጃጀት እና አመራራ ጉዳዮችን በጥብቅ እና ዉስብስብ የተቋማት ቁልፍ ዉስጥ ስትከቱት ነዉ::ዝርዝሩን ለራሳችሁ ትቸዋለሁ::

እንግዲህ የአማራ ህዝብ መሪነኝ የምትል ሁሉ ከመቁረጥ ዉጭ ምን አማራጭ አለህ? ሚስጢርህን የምትጠብቅበት አደረጃጀት ፈጥረህ ከመዋጋት ዉጭ ምን አማራጭ አለህ? ምንም አማራጭ የለህም::

ወደቀኝም ወደ ግራም ማዬት አትችልም::ወደ ምስራቅ ወይም ወደ ምዕራብ ማዬት አትችልም::ጦርነት ዉስጥ ገብተሃል እና ጦርነቱን እሰይ እያልክ እንደ ሀያላኖች ነገስታት በጦር መሪነት ከዉነዉ::

ከመጀመሪያዉም ኦህዴዳዉያንን አምናችሁ ወደ ጦርነት የአማራን ህዝብ አትክተቱ ብለን ብዙ ጮህን ነበር::ግን ማን ይሰማል?የአማራ ህዝብ መሪ ነን ብላችሁ የአማራን ህዝብ እጦርነት ዉስጥ ማግዳችሁታል እና አሁን ጦርነቱን እንደ ኩሩ እና ጀግና የጦር መሪ ሆናችሁ ምሩት::

ማንኛዉንም ምድራዊ ሀይል ከበላያችሁ ላይ አሽቀንጥራችሁ በመጣል የራሳችሁ የጦር እዝ ሰንሰለት ከፈጠራችሁ ብቻ እራስችሁንም ህዝባችሁንም ትታደጋላችሁ::

ሞት ጌጥ ነዉ::ምን ትፈራላችሁ? በዉበት እና በጀግንነት ሲሞቱት ሞት ዉበት አለዉ:: በተለይም ከምድረ ገጽ እንዲጠፋ ለተበዬነበት ህዝብህ መሞት በራሱ ልዩ ዉበት ያለዉ ሞት ነዉ::

ስለዚህ መጀመሪያ የአማራ ህዝብ መሪ ነን የምትሉ በራሳችሁ ህይወት ላይ ጨክናችሁ ቁርጥ ያለ: ሚስጢር የጠበቀ እንዲሁም በራሳችሁ ህዝብ ላይ ብቻ የቆመ የጦር አመራር ስጡ::

አቢይ እንደሆነ በአንድኛዉ ሳምንት “ታጠቅ !” በሁለተኛዉ ሳምንት “ትጥቅ ፍታ” የሚል የጦር ሀይሎች አዛዥ ነዉና ከዚህ መሰል የጦር ሀይል አዛዥ እራሳችሁን ነጻ በሆነ የእዝ ሰንሰለት በማደራጀት እና ህዝቡን በመምራት ህዝቡን አዋጉ::

ከዚያ ብኋላ ብቻ የአማራን ህዝብ የጦርነት ባህሪ ጠንቅቀዉ የሚያዉቁት ታዲዮስ ታንቱ “የአማራ ህዝብ ተሸንፎ ወሎ ተያዘ የሚለው ፌዝ ነው” ለምን እንዳሉ ይገባችኋል::

የግባችሁ መዳረሻም በወያኔ ህሳቤ የተፈጠረዉ የአማራ ክልል የሚባለዉ ቅያስ ሳይሆን የአባቶቻችሁ ሀገር መላዉ ኢትዮጵያ ይሁን::መላዉ ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያዊ መሬቱ እና ምድሩ ነዉ::

ይሄን ከተገበራችሁ ብቻ አሸናፊ ትሆናላችሁ::ኢትዮጵያን ለማዳን ከተነሳችሁ ብቻ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከናንተ ጋር ይሆናል::

ይሄን ሁሉ ሚስጢር አመሳጥረዉ እና አሰናስነዉ ነዉ ታዲዮስ ታንቱ “የአማራ ህዝብ ተሸንፎ ወሎ ተያዘ የሚለው ፌዝ ነው” ያሉት:: ይሄ መራራ እዉነት ነዉ::

——————–

ሸንቁጥ አየለ

12 Comments

 1. አቶ ሸንቁጥ መልእክቶ መልካም እነ አገኘሁ ተሻገርን የመሳሰሉ ከጠላቱ የከፉ ሰዎች ከላይ ቁጭ ብለው ብዙ ሊጓዝ የሚችል አይመስልም ይህ ግለሰብ አብን በአማራ ክልል ቅስቀሳ ሲያደርግ በጥይት እንዲባረሩ ያደረገ ስኒ ለልጅ አይሰጥም ብሎ ያፌዘ ነው። በዚህ ላይ ትግሬ ያደነዘዛቸው የኦሮሞ ፖለቲከኞችና ብርሀኑ ነጋ አንዳርጋቸው ጽጌ ነአምን ዘለቀ የመሳሰሉ ዘበኞች አሉበት በዚህ ላይ ለህዝባቸው ማለቅ ደንታ የሌላቸው ምሁር ባዮችም አሉበት።መፍትሄው እንደ በላይ ዘለቀ በግል የቆረጡ ተዋጊዎችን ማፍራት ነው። የጠቀስካቸው አቶ ታዲዮስ ለኦነግ ወይ ለህወአት ወግነው ቢሆን ኑሮ ደልቷቸው በምቾት በኖሩ ነበር።

 2. በመጀመሪያ ደረጃ ምሁር ባልጠፋበት ሃገር እኚህ ግለሰብ እንደ ዋቢ መጠቀስ አልነበረባቸውም። ታዲዮስ ታንቱ የዘነጉት በኦሮሞ ወረራ ግዜና በግራኝ መሃመድ ጦርነት ግዜ … አማራው 250,000 ሰራዊት አሰልፎ ግራኝ መሃመድ 15,000 ሰራዊት ብቻ አሰልፎ አማራው ያፈጠጠ ሸንፈትን አስተናግዷል። ሩቅ ሳንሄድ ኢጣልያ በቀ/ኃ/ሥ ዘመን ያለ ደባና ሴራ ቀጥቅጣ አሸንፋለች ስለዚህ አማራ በታሪክ እንደሚታወቀው ሲቀናው የሰው ርስት ነጣቂ ሲዞርርበት ደግሞ ርስቱን ጥሎ የሚፈረጥጥ ተራ ማህበረሰብ ነው። ሸፍጥና ደባ ደግሞ የአማራ ሀሁ እንደሆነ ግልፅ ነው

  • ወንድ መልስ
   ጥልያንን ካባረርንብህ በሁዋላ ጠምደህ ይዘኸናል ከእንቁላል ተሸካሚነትና ፓስታ ቀቃይነት ብንገላግልህ እንዲህ መሳፈጥ ያዝክ? የጥልያን ካልቾ የለመደ ባንዳ ክብር ለሱ ምንም አይደለም።

  • የምታሳዝን፣ሁዋላ ቀር ፣ ዘረኛ፣ ዝግመተኛ አይምርህ ከሌለህ በስተቀር፣ ከnormal አይምሮ እንዲህ አይነት ጽዪፌ ቃል አይዉጣም።

  • በመጀመሪያ የግራኝ መሀመድን ጊዜ የጦር አሰላለፍ የፃፍከው ውሸት ነው ። በእስላሞችና ክርስትያኖች መሀከል ባልሳሳት ከ12-15 ኛው ክ/ዘመን ብዙ ውግያ ተደርግዋል ( አዳል ) የመሐመድ ግራኝን ጊዜ ለየት የሚያረገው በኦቶማን ቱርኮች መረዳቱ ነው ። ቱርክ በዛ ዘመን አውሮፓን ሁሉ ለብዙ ዘመን ይዛ ነበር። ዘመናዊ ትጥቅ ነበራት።
   ሁለተኛው በ ቀ/ ሃይለስላሴ ዘመን መሣሪያ የመግዛት ማእቀብ ኢትዮጵያ ላይ ተደርጎብን ነበር በዛ ላይ ጣልያን በተከለከለ የመርዝ ጭስ ወታደሩን እና ሕዝቡን ከጨረሰች ቦሀላ ነው ወርዳ ባንዳውን ጃሌ ከፊት አሰልፋ ውጊያ የጀመረችው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ታሪክ የተፃፈ ስለሆነ ባንዳ እና በበታችነት በሚሰቃዩ ድኩማናች አይቀየርም። ያቅርሀል እንጂ እንደናንተ አይነቶቹ መቼም ምንም አያመጡም።

 3. እውነት ነው ኢትዮጵያዊያን አሁን ካጋጠማት ጋግሪን በሽታ በደንብ ቆርጦ የሚያሳርፋት ጅግናው የአማራ ህዝብ ነው
  መራራ እውነት ???

 4. ሽንታም ወያኔ
  ሽርጥ ጠምጣሚ
  ባንዳ
  የታወቀች ነው ጉራ ብቻ ናት
  ከበሮዏን
  ኪሊው እያደረገች እንደ ቁንጫ ከመዝለል በቀር
  250ሺ ሽንታም ወያኔን ማግዳም
  እንቧ እያለች መጨፈሯ
  ያንከተክተኛል ።

 5. ምድር ተዘርግታ እስክትካተት
  እንግዲህ ለትግሬ የለው ወንድነት (ሼህ ሁሴን ጅብሪል)

 6. ምድር ተዘርግታ እስክትካተት
  እንግዲህ ለትግሬ የለው ወንድነት (ሼህ ሁሴን ጅብሪል)

 7. አብይ አህመድ የኦሮሚያ ፖሊስን በሸኔ ስም በማሰማራት በአሩሲ፣ በመተከል ፣ በወለጋና በአጣይ የአማራ ዘር አጥፍቷል አሁን ደግሞ ለወያኔ ስንቅና ትጥቅ በመስጠት መከላከያ እንዳይዋጋ በማድረግ ሁለተኛ ዙር የአማራ ጭፍጨፋ እያካሄደ ነው

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.