የደሴ ከተማ አስተዳደር ህዝብ አካባቢውን ከሰርጎ ገቦች ነቅቶ እንዲጠብቅ አስታወቀ

(የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል)

ጥቅም 9/ 2014 ዓም
246864460 2095814883908728 1830163255585903696 n
246864460 2095814883908728 1830163255585903696 n

የአሸባሪውን የትህነግ ወረራን ለመመከት የጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን፣ የልዩ ሀይሎች፣ የአማራ ሚሊሻ፣ የቀድሞ የመከላከያ ሠራዊትና የአማራ ፋኖ በጋራ በመቀናጀት እየመከቱ ይገኛሉ ብለዋል።

እንደ ደሴ ከተማ አስተዳደርም የተለያዩ ዕቅዶችን በማዘጋጀትና ከደቡብ ወሎ ዞን፣ በዙሪያው ከሚገኙ የከተማ አስተዳደሮችና ወረዳዎች ጋር በየዕለቱ የጸጥታውን ሥራ ተቀናጅተን እየሠራን እንገኛለን።
ጥቅምት 8/2014 ዓ.ም በከተማችን ውስጥ አይተናቸው የማናውቃቸው ወጣቶች ከደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ አካባቢ ተነስተው የተወሰኑ የከተማችን ወጣቶች ጋር በመሆን በተለይም ሸርፍ ተራና አራዳ አካባቢ የንግድና ሌሎች ድርጅት ተቁዋማትን ለመዝረፍ ሲሞክሩ በጸጥታ ሀይሉ፣ በህዝቡ ፣ በነጋዴዎችና በከተማችን ወጣቶች የጋራ ጥረት ለማክሸፍ ተችሎአል ።
በወቅቱም ህዝቡ እንዲረጋጋ የሚዲያ መግለጫ በመስጠትና በሞንታርቦ ቅስቀሳ ህዝቡ እንዲረጋጋ ተድርጎእል ብለዋል።
በህዝቡና በጸጥታ ሀይሉ አማካይነት በተለያዩ ኬላዎችን፣ አልጋ ቤቶች፣ የእግረኛና መኪናዎች ላይ ጥብቅ ፍተሻ በመካሄዱ ስድስት ጸጉረ ልውጦች የተያዙ ሲሆን የሬዲዮ መገናኛና ጂፒኤስ ጭምር መያዙንም አስታውቀዋል።
ህዝቡም አካባቢውን ከመቼውጊዜ በላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅ፣ ለሠራዊቱም ምግብ አዘጋጅቶ ከማቅረብ ጀምሮ የሁዋላ ደጀን በመሆን ግንባር ድረስ እንዲሰለፍ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ሌሎች ከተሞች ላይ የተደረጉ ሴራዎችና ተንኮሎች ከተማችን ላይ እንዳይፈጸሙ ከወዲሁ በግልም ሆነ በቡድን ሀሰት ወሬና አሉባልታ ከማውራት መቆጠብ አለባቸው ።
እንደሌሎች ከተሞች የከተማችንን ህዝብና ተፈናቅለው የሚገኙ ወገኖቻችን ከተማውን ለቀው እንዲወጡ ለማድረግ የተለያዩ የመገናኛ ጂፒኤስ መሣሪያዎችን ይዘው የተገኙ ሠርጎ ግቦችን በፍጥነት በቁጥጥር ሥር ማዋል በመቻሉና ህዝቡም በተደራጀ ሁኔታ በመንቀሳቀሱ አሸባሪው ያሰበውን ሴራ እንዳልተሳካለት ገልጸዋል።
በቀጣይም ህዝቡ ከአመራሩ፣ ከጸጥታ አካላትና ከወጣቶች ጋር ሆኖ የከተማችን ሠላምና ደህንነት እንዲረጋገጥ በመስራትና ሁሉም የመንግሥት ሠራተኛ፣ የተለያዩ ተቋማትና የንግዱ ማህበረሰብም በመደበኛ ሥራቸው ላይ ተገኝተው በመሥራት ከተማችን ፍጹም ሠላም ሆና እንድትቀጥል በጋራ እንድንሠራ ጥሪየን በከተማ አስተዳደሩ ሥም አቀርባለሁ ብለዋል።

Bahirdar Prosperity Party /

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወደ አዋሳ ሲጓዙ በነበረ የቅ/ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ የሰዎች ሕይወት ጠፋ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share