ጠላት አይናቀም ፤ ወዳጂ አይታማም – ማላጂ

ብዙ ጊዜ ከጠላት ፣ስረታ የ1960ዎች ዓ.ም. ጀምሮ  በጥምረት እና አገር በማክሰም ግብ አድርገዉ በተጠና ስልት የሚንቀሳቀሱትን ታሪካዊ እና ብሄራዊ ጠላቶች ዛሬ እንደተከሰቱ ማድረግ ለምን እንደሚፈለግ ባይገባንም እጅግ ስህተት ሲሆን ትዉልዱም ስለ ራሱ ፣ ስለ አገሩ እና ታሪካዊ ባላንጣዎች  የሚኖረዉን ታሪካዊ እና ወቅታዊ ዕይታ የሚያዛባ ከመሆኑ በላይ ትኩረት እና ፅናትን ይበርዛል ፡፡

ይህም ትዉልዱ በይፋ የህልዉና  እና የአገር ሉዓላዊነት ጥፋት ዘመቻ የተከፈተበት ስለሆነ ሁለንተናዊ የታሪክ፣ የርዕዮተ ዓለም እና ሁለመናዊ የስነ ልቦና እና ንቃተ ህሊና ማዘጋጀት እና ማብቃት  በስነ ንቃተ እና ትጥቅ ማደራጀት እየጠካሄደ ያለዉን ብሄራዊ ፣ታሪካዊ  እና ወቅታዊ የህልዉና እና የሉዓላዊነት  ተጋድሎ አዋጭ እና ተመራጭ ስለሚያደርገዉ ነዉ ፡፡

ለዚህም ነዉ ቀድሞ እና ከዘመናት በፊት ከአንድ ክ/ዘመን ያላነሰ ዕድሜ ያስቆጠረዉን የጠላት ሤራ አቅልሎ እና አሳንሶ ደጋግሞ መናገር አቅም ማዳከም እና  የትግሉን ግለት ከሚገኝበት ደረጃ በላቀ ሁኔታ ለማራመድ ለሚደረገዉ ጥረት የሚበጅ አይደለም ፡፡ታሪካዊ ጠላቶች  ጥምረት በጊዜዉ አገላለፅ  ጋብቻ  ዛሬ ሳይሆን በ1960 ዎች የተጋመደ የጥፋት ቁርኝት ስለነበር  በተግባር የትፋት ሰይፋቸዉን የመዘዙት ከዚያ ጀምሮ አስከ አሁን ከ40 ዓመት በላይ በኢትዮጵያዉያን ላይ የደረሰዉን መጠነ ሠፊ የመከራ ዘመን መረሳት አያስፈልግም ፡፡

አሁን ጥምረት እና የጥፋት ስልት በመቀያየር ማደስ ማለት በቂ ነዉ ፡፡ ሌላዉ አሁንም ጠላትን ማሳነስ ስህተት ብቻ ሳይሆን ማሳሳት ይሆናል፡፡

ጥቂት፣ ቁርጥራጭ፣ የደቀቁ ፣ የበነኑ………. ወዘተ አይተንዋል  ይህ አይሰራም ያዘናጋል፡፡ ጠላት ሲበተን  ደቀቀ ፤በነነ ይህ አንዱ እና ዋነኛ የማደናቀፊያ ቅስቀሳ እና ማደንዘዣ ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይድረስ ለአባይ ባለበት…

ለዘመናት ጠላትን ሽፋን የሚሰጡ እና የሚያዘናጉ  ዞትር  ጠላት “ያቦከዉን እስኪጋግር” ጊዜ መስጠት ከላፈዉ እንማር ፤ያለፈዉ ይብቃ ፤ እንንቃ እኛም ሆነ ኢትዮጵያ የምትጠበቀዉ በእኛ እና በዕኛ ብቻ ነዉ ፡፡

አደንዛዞች በየትኛዉም አኖኗር  እና የዉስጥ እና ዉጭ  ምንደኞች፣ አድር ባዮች እና ሰርጎ ገቦችን የሚነዙትን እና የሚያደርጉትን  አሰልች ንግግር  መመርመር ለዕዉነተኛ ዓላማ በፅናት መቆም ጊዜዉ አሁን ነዉ ፡፡

ወገን አትታበይ ጠላት አይናቅም ፤

ቁንጫ እንኳ በአቅሙ ትጥቅን ያስፈታል፡፡

እናም መናቅም ፤ማድነቅም በልክ ይሁን ፡፡ ጠላት ሳይናቅ ፤ ወዳጂ በዉል ሲታወቅ አስተማማኝ እና ቀጣይነት ያለዉ ብሄራዊ እና አካባቢያዉ  ድል ማስመዝገብ ዕዉን ይሆናል ፡፡

ስለሆነም ጠላት አይናቅም ፤ ወዳጂም በዕዉቀት እና በመከራ የሚገኝ አታማም፡፡

ማላጂ

 

አንድነት ኃይል ነዉ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share