የሐይቅና መርሳ ወጣቶች መከላከያ ሠራዊት ትጥቁን አስረክቦ እንዲሄድ ጠየቁ

ሐምሌ 21/2013
ንሥር ብሮድካስት

war

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ አስተዳደር እና ትግራይ ክልል አዋሳኝ አሸባሪው ህወሃት የከፈተውን ጦርነት ለመመከት እና የህግ ማስከበር ዘመቻውን ለማጠናቀቅ የዘመተው የመከላከያ ሠራዊት ከውጊያ ቀጠና በመውጣት ወደ መሃል ሀገር እየገባ መሆኑ ያስቆጣቸው የሐይቅና መርሳ ወጣቶች መከላከያ ትጥቁን ለጀግናው የአማራ ህዝብ ማስረከብ አለበት ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ንሥር ብሮድካስት በስልክ ያነጋገራቸው ወጣቶች እንደሚሉት በአፋር ክልል ጭፍራ ወረዳን የሚያዋስነው የሀብሩ ወረዳ ነዋሪዎች ኬላ በመዝጋት መከላከያ ሠራዊት መሳሪያውን ሳያስረከብ መንቀሳቀስ የለበትም በሚል በተከፈት ግጭት 3 የመከላከያ ሠራዊት ሲገደሉ አንድ የአካባቢው ነዋሪም መሞቱ ታውቋል፡፡
የሐይቅ እና መርሳ ከተሞች ወጣቶች በጉበዬ ግንባር ተሰልፎ የነበረው የመከላከያ ሠራዊት የፍርሃትና የሴራ ሰለባ በመሆኑ ሙሉ ትጥቁን ይዞ ከግንባር እየወጣ ይገኛል ብለዋል፡፡ ይህ ተገቢ ባይሆንም ለጀግናው የአማራ ህዝብ፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚኒሻ የሚመጥን ባለመሆኑ መሳሪያውን አስረክቦ መሄድ ይችላል ብለዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ጥላችን ከመከላከያ ተቋም ጋር በመሆኑ ሊታወቅ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የሐይቅና መርሳ ወጣቶች አንደገለጹት የመከላከያ ሠራዊት ሙሉ ትጥቁን ይዞ ከውጊያ ቀጠና የሚሸሽ ከሆነ መላው የአማራ ህዝብ መሳሪያውን የመረክብ ኃላፊነት ሊወጣት ይገባልም ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ዘጋቢ ተፈሪ መኮንን
ባህር ዳር
ኢትዮጵያ
ተጨማሪ ያንብቡ:  በወልቃይት ምሽግ እየተቆፈረ ነው፣ መሳሪያ እየገባ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share