ዛሬ በትግራይ ትግል አጽቢ ወንበርታ በፖሊስ እና በሕዝብ መካከል ስለተነሳው ግጭት የአብርሃ ደስታ የቀጥታ (Live) ዘገባዎች

የአፅቢ ግጭት

በአፅቢ ወንበርታ በተከፈተው ግጭት የመንግስት ፖሊሶች ተኩስ መክፈታቸው፣ አርሶአደሮች መደብደባቸው፣ እንዲሁም አራት የኗሪዎቹ ተወካዮች በሃይል አስረው ወዳልታወቀ አከባቢ መውሰዳቸው ታውቋል። ህዝቡም (የአካባቢው ምልሻዎች ሳይቀሩ) አስራ ሁለት ፖሊሶችና አንድ የመንግስት ምልሻ ከበው አግተው ይዟቸው ቆይተዋል። አራቱ የህዝቡ ተወካዮች እስካልተለቀቁ ድረስ ፖሊሶቹ እንደማይለቀቁ የአርሶ አደሮቹ ተወካዮች አሳውቀው ነበር። አሁን በተደረገ ድርድር አራቱ ተወካዮች ይፈታሉ፣ በህዝቡ ታግተው የነበሩ አስራ ሁለት ፖሊሶችም ይለቀቃሉ። ህዝቡ የአራቱ ሰዎች መለቀቅ እየተጠባበቀ ይገኛል። ፖሊሶቹ ተለቀዋል፤ አራቱ ገብሬዎች እስኪፈቱ ድረስ ግን እዛው ይቆያሉ። መከላከያ ሰራዊት ጥሪ ቢቀርብላቸውም እስካሁን ድረስ (እስከ ምሽቱ 1:30) ባካባቢው አልደረሱም።

ድርድሩ አልተሳካም፡ ተኩስ ተከፍቷል ህዝብ እየተደበደበ ነው

ፖሊሶች አራት የኗሪዎቹ ተወካዮች በሃይል ሲወስዱ የአፅቢ ህዝብም አስራ አራት ፖሊሶችና አንድ ምልሻ አግተው ነበር። ህዝቡ ፖሊሶቹ እንዲለቅ አስተዳደሩ ደግሞ አራቱ ተወካዮች እንዲለቅ ድርድር ተጀምሮ ነበር። በድርድሩ መሃል የወረዳው አስተዳደር አዲስ ሃይል በመጥራት (ከሌላ ወረዳና ከክልል አስተዳደር የፀጥታ ሃይሎች በመላክ) ህዝብ በተሰበሰበብት መተኮስ ጀመሩ (ከምሽቱ 2:30-2:56)። ምልሻዎቹና ወታደሮቹ የታገቱትን ፖሊሶች ለማስለቀቅ እስከ ሁለት መቶ (በኗሪዎቹ ግምት መሰረት) የሚደርስ ጥይት በመተኮስ የታገቱት ፖሊሶችን ማስለቀቅ ችለዋል። እስከ ሁለት ሺ የሚጠጋ ህዝብ ተሰብስቦ እየጨኸ ይገኛል። አሁን (ከምሽቱ ሦስት ሰዓት) ብዙ ምልሻዎች የጫኑ ብዙ መኪኖች ወደ አከባቢው እየገቡ ነው። በሌላ አቅጣጫ (በስተ ሰሜን በኩል) ደግሞ ሌሎች ብዙ መኪኖች እየገቡ ነው (ምልሻ ወይ ፖሊስ ወይ ወታደሮች መሆናቸው ግን በትክክል አይታወቁም)። ህዝብ በዱላ መደብደብ ጀምረዋል። ህዝቡ እየጮኸና ፈጣሪው እየለመነ ነው። የህዝቡ ጩኸትና ለቅሶ በስልክ መስማት ችያለሁ። እያናግሩኝ ያሉ ሰዎችም መረጋጋት ተስኗቸዋል። አሁን ከምሽቱ 3:05 ሁነዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የመኢአድና አንድነት ውህደት አመቻች ኮሚቴ የባንክ አካውንቱን ይፋ አደረገ

ተኩሱ ቆሟል፣ ምልሻዎቹ ለሁለት ተከፍሏል፣ ወታደሮች ገብተዋል

ታግተው የነበሩ የመንግስት ፖሊሶች ሌሎች ፖሊሶችና ምልሻዎች በከፈቱት ተኩስ ተለቀዋል። አሁን ህዝቡና የመንግስት ምልሻዎች በሜትሮች ርቀት ተለያይተው ማዶ ለማዶ ይተያያሉ። የአፅቢ ወንበርታ ተወላጆች የሆኑ የመንግስት ምልሻዎች የመንግስት አካላትን ከድተው ከህዝቡ ጎን ተሰልፈዋል (ከአንድ ምልሻ በስተቀር ሁሉም የአፅቢ ወንበርታ ምልሻዎች ከህዝቡ ጎን ይገኛሉ)። ሁለቱም ምልሻዎች (የአፅቢ ወንበርታና አስተዳደሩ ከሌላ ወረዳ ያስመጣቸው) ተፋጠዋል። አሁን 3: 15 በደራ ጣብያ ገብረኪዳን ልዩ ስሙ “አፅገበት” የሚባል ቦታ የነበሩ ወታደሮች (መከላከያ ሰራዊት) ባከባቢው ደርሰዋል። እስካሁን ምንም ዓይነት እርምጃ አልጀመሩም። ፀጥታ ሰፍነዋል። ህዝቡ ግን እንደተሰበሰበ አለ። “ተወካዮቻችን ፍቱልን” እያለ ይገኛል። አሁን ከምሽቱ 3:24 ነው።

ወታደሮቹ ህዝብ እንዲበተን ጥሪ አቀረቡ

በሰባት መኪኖች ሙሉ ተጭነው ወታደሮች ገብተው አከባቢው ተቆጣጥረውታል። “የዞን አስተዳዳሪዎች ነን” ያሉ ባለስልጣናት ህዝቡ “የአሸባሪነት ተግባር” እያከናወነ መሆኑ በርቀት ተናግረዋል። ህዝቡም “አሸባሪዎች እናንተ ናች ሁ፤ ልጆቻችን ፍቱልን” እያለ ሲጮህ ነበር። በመጨረሻም ወታደሮቹ ህዝቡ እንዲበተን ማስጠንቀቅያ ቢሰጡም አራቱ የአፅቢ ወንበርታ ልጆች ካልተፈቱ እንደማይበተን አስታውቀዋል። መከላከያውና አስተዳዳሪዎቹ ቢያስፈራሩም ህዝቡ ግን ለመበተን ፍቃደኛ አልሆነም። ዘጋቢዎቼ ወደ ቤታቸው እየተንቀሳቀሱ ነው። ነገ እንገናኝ። አሁን ከምሽቱ 3:55 ነው። ቸር ያሰማን።

5 Comments

  1. Awo, Cher yaseman, my Brother. This wicked and terrorist group, calls itself tplf must go if we have to live in the country peacefully. These people are brave. We can learn a thing or two from these resilient people. There are lots of our brothers in tplf prisons unjustly. It is time to raise up against this wicked group, and let our brothers free from tplf dungeon. May the Lord protect these brave people who said “enough” to tplf from harm. Cher Yaseman!

  2. May be thier question is IPhone and computer for the whole Tigray .like the queen of France who said why they do not eat cake.

  3. ጊዜው ቆየ እንጂ “እየሳቁ ማልቀስ” የሚል መጽሃፍ እንብቤ ነበር። ወያኔ የትግራይን ህዝብ መነገጃ እንዳደረገው ያለፈ ታሪኩ ይመሰክራል። ወያኔ ለትግራይ ህዝብም ሆነ ለመላ ሃገራችን አንድነትና ደህንነት የማይገደው ጠማማና ጠባብ ብሄርተኛ ቡድን ነው። አሁን አንተ መቀሌ ላይ ሆነህ የምትዘግበው በበረሃ ደጋግሞ የተፈጸመ ተግባር ነው። ስንቶች የሞትን ጽዋ ቀምሰዋል ወያኔ ተቃውመው? ቤቱ ይቁጠረው።
    ለመኖር፤ ማሰር፤ በግደል፤ ያዘው ጥለፈው ማለት የተለመደ የፓለቲካ ስልታቸው ነው። አሁን የታገቱት አማጽያንም ቢፈቱ ነገ ተነገ ወዲያ ተጠልፈው የውሃ ሽታ ይሆናሉ። ምድሪቱ ነጻነት የላትም። በቅርቡ በአዲስ አበባ በድንገት የወጡት የሙታን አጽም የሚነግረን እውነት፤ ፍትህ፤ ሰላም፤ ነጻነት የሌለባት ሃገር እንደሆነች ነው። ዛሬም ሞት ነገም ሞት፤ ዛሬም እሥራት ነገም እስራት – የወያኔ ለውጥ ሃገራችን ለጠላት መሽጥ፤ ህዝብን በጎሳ መከፋፈል፤ ለራስ ሃብት ማካበትና መዘነጥ ነው። በደርግና በወያኔ አጣብቂኝ ፍትጊያ ውስጥ ገብቶ ግፍና መከራን የቀመሰው ያ ሃገር ወዳዱ የትግራይ ህዝብ ዛሬም መራራ እየጋቱት ነው። ወያኔ ለትግራይ ህዝብም ለሃገራችንም አይጠቅምም!

  4. Abraha, you have reported the incident accordingly and we have learned that the people of Atsebi Wonberta have been subjected to inexplicable repercussion. It is our collective responsibility of disseminating the information to the people of Ethiopia to let them know what has happened on the people of Atsebi Wonberta people. The Minority Junta has put the people of Ethiopia under Machiavellian ruling and been killing prominent Political Leaders, activists, elders, opposition political party members and sympathizers, teachers, students and innocent people, who were protesting injustice, for the past 23 years. Unless we unite and stand against this dictatorial, divisive and ethnocentric regime, we will be remain enslaved under Machiavellian rulings for a generation to come. United we are stronger and indomitable, divide we are weak and vulnerable to like Dr. Debretseyon and Berket Simon kleptomaniac myopic dictators. No one is Free until All are Free.

  5. There is a wide spread of decent against the AdwaAxum-Shire dominated tplf by the majority of tigrian from Tenbien-Enderta-Agame-HuletAwulalo andRaya awurajas. Historicaly, these awurajas are more Ethiopian than the Adwa banda when it comes to the interest of Ethiopia.

Comments are closed.

Share