ዜጎች ላይ ማንነታቸውን መሰረት አድርጎ የሚፈፀም ጥቃት እንዲቆም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠየቁ

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 25/2013 ዓ.ም

(አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ፣ እናት ፓርቲ፣ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በጋራ በኦሮሚያ ክልል በወለጋ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል እንዲሁም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተፈጸመ ያለውን ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በዜጎች ላይ ማንነታቸውን መሰረት አድርጎ የሚፈፀም ጥቃት እንዲቆም ጠይቀዋል፡፡

ፓርቲዎቹ በጋራ የአቋም መግለጫቸውም በሀገሪቱ ውስጥ በበርካታ አካባቢዎች በተለይም በኦሮሚያ ክልል እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች እና በአጠቃላይ “መጤ” ተብለው በተፈረጁ ዜጎች ላይ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተፈፀመ ያለውን ዘር ተኮር ጥቃት በጥብቅ እንደሚያወግዙ ገልጸዋል፡፡

የፌዴራል መንግሥትና የክልሎቹ መንግሥታት ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ እንዳለባቸው፣ የችግሩን ግዝፈትና መደጋገም እንዲሁም በሀገሪቱ አንድነትና ደኅንነት ላይ የደቀነውን ከፍተኛ አደጋ ከግምት ውስጥ በማስገባት ዘላቂ እልባት የመስጠቱ ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለልተኛ ኮሚሽን በማቋቋም በጥልቀት መርምሮ ውጤቱንም ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

ፓርቲዎቹ “በሀገር አንድነት እና ደኅንነት ላይ የተጋረጠው አደጋ” አስቸኳይ መፍትሄ እንደሚያሻው በማመን የመፍትሄ አካል ለመሆን እና የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ቁርጠኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

በመንግሥት በኩል እስካሁን በተፈፀሙት ጥቃቶች ውስጥ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በተሳተፉ ግለሰቦችና ቡድኖች ላይ እንዲሁም በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የመንግሥት አመራሮች ሆነው የመከላከል ኃላፊነታቸውን ያልተወጡና በጥቃት የተሳተፉትን በሚመለከት በፍጥነት ተገቢው የማጣራት ሥራ እንዲሠራና በሕግ እንዲጠየቁ እንዲደረግም ጠይቀዋል፡፡

መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለያዩ አሰላለፎች ውስጥ ተካትተው ዘርና እምነት ተኮር ጥቃቶችን የሚፈፅሙ አካላትን ለማውገዝ፣ ለማጋለጥ፣ እና ለመከላከል ብሎም ለማሸነፍና በሕግ ጥላ ስር ለማዋል በአንድነት እንዲቆሙ፣ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖኖሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በአማራ ሕዝብ ላይ በጥላቻ ኃይሎች እየተፈፀመ ያለውን ዘር ተኮር ጥቃት ለማውገዝ፣ ለማጋለጥና ለፍርድ ለማቅረብ ያለምንም ልዩነት በጋራ እንዲሰለፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ልዩ መረጃዎች! | "የተደገሰልንን ቀድመን ሰምተናል" - ለገሰ ቱሉ | ከአማራ ክልል የወጣው አዲስ መረጃ!

በተፈፀሙት ጥቃቶች ምክንያት ደጋፊ ወገኖቻቸውን ላጡና በጅምላ ተፈናቅለው ችግር ላይ ለወደቁት ወገኖች በአስቸኳይ የነፍስ አድንና የመልሶ ማቋቋም የተቀናጀ ርብርብ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

ፓርቲዎቹ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ አካባቢና በቤኒሻንጉል ክልል በተፈፀሙት ዘር ተኮር ጥቃቶች ህይወታቸው ላለፈ ወገኖች የተሰማቸውን ሃዘን በመግለጽ የተለያዩ ጉዳቶች ለደረሰባቸው ማገገምን እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

ዘጋቢ፡- እንዳልካቸው አባቡ – ከአዲስ አበባ

ዜጎች ላይ ማንነታቸውን መሰረት አድርጎ የሚፈፀም ጥቃት እንዲቆም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠየቁ

2 Comments

  1. አንድም የፌደራል ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን (ሚኒስትር) ወይም የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች በማንነታቸው ለሚገደሉት ድምፅ ለመሆን እና የተረፉት የተጎጂዎች ቤተሰቦቻቸውን አለማስተዛዘናቸው ፤ በስፍራው በአካል ተገኝተው በሚመሩዋቸው ፓርቲዎች ስም ወይም በመንግስት ስም አለማስተዛዘናቸው ፤ ምን ያህል የደህንነት ስጋት እንዳለ ያሳያል።

    የደህንነት ስጋት ባይኖር ኖሮ ለተጎጂዎች አዝነው ባይሆን እንኳን ለምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ ስለሚያግዝ ምሁራኖች ካድሬዎች እና የዘር አቀንቃኝ ፖለቲከኞቹም በቦታው በፍጥነት ይገኙ እንደነበር አያጠያይቅም። በአለመገኘታቸው ህዝቡ ምን ያህል አደጋ ውስጥ እንዳለ ተገንዝቦ በአስቸኳይ ከማንም እርዳታ ሳይጠብቅ ነዋሪው በያለበት እራሱን ለመታደግ በተጠንቀቅ ዘብ መቆም አለበት። አብን እንኳን አማራዎች በሞቱበት አለመገኘቱ አነጋጋሪ ነው። ወልቃይት ሁመራ እና ራያ ፤ የአማራ ልዩ ኃይል በመስፈሩ አብን እንደ የአማራ-ብልፅግና እንደማይደለል ይታወቃል።

    ” ኦነግ ሸኔ የኦህዴድ ብልፅግና ወታደራዊ ክንፍ ነው ! ” ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ – የባልደራስ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ

  2. It is really painful to watch political groupings or parties voicing the very nonsensical or good for nothing rhetoric and holding press conference and releasing statements over and over and over and over and…. again !!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share