“በህወሓት ላይ የተወሰደው የመጀመሪያ ዙር እርምጃ በስኬት ተጠናቋል” – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

በህወሓት ላይ የተወሰደው የመጀመሪያ ዙር እርምጃ በስኬት ተጠናቋል ሲሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ። ተጨማሪ ጥቃት መሰንዘር ወደማይችልበት ደረጃ አድርሰነዋል፣ የማድረግ አቅሙንም አዳክመናል ነው ብለዋል ጠ/ሚኒስትሩ።

ዘመቻውም የህወሓት ቡድን ሙሉ በሙሉ ለህግ እስከሚቀርብ ድረስ እንደሚቀጥል ነው ማምሻውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ባደረጉት ንግግር ያመለከቱት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀድም ሲል ባሰፈሩት ፅሁፍ የመከላከያ ሠራዊት እየወሰደ ያለው እርምጃ ግልፅ ውስን እና ሊደረስባቸው የሚችል አላማዎች ያሉት ነው ብለዋል።

ኩሩ ኢትዮጵያዊ የሆነው የትግራይ ሕዝብና ሌሎችም ከህግ ተጠያቂነት ባመለጡ ወንጀለኞች እገታ ሥር ሊቆዩ አይችሉም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ ለወንጀለኞች ቦታ የላትም ሲሉም አክለዋል::

ትናንት በትግራይ ቴሌቪዥን የቀረቡት የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል ደግሞ የተቃጣብንን ጦርነት በድል እንወጣለን ነበር ያሉት።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.