የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የታሰሩት ኮሚቴዎች እንዲፈቱ ለመጠየቅ የጠሩት የዚያራ ፕሮግራም በሰላም ተጠናቀቀ

ስኬታማው የዚያራ ፕሮግራም በሰላም ተጠናቀቀ!
ህዝበ ሙስሊሙ ለመሪዎቹ አጋርነቱን፣ ለዓላማው ፅናቱን ዳግም አረጋገጠ!!!
እሁድ ሕዳር 22/2006

ድምፃችን ይሰማ እንደዘገበው፦

ህዝበ ሙስሊሙ በግፍ ለታሰሩት መሪዎቹ ያለውን ፍቅርና አጋርነት የገለጸበት የዛሬው ‹‹ኑ! ለመሪዎቻችን በዚያራ አጋርነታችንን እናሳይ!›› የዚያራ ፕሮግራም በስኬት ተጠናቀቀ!

ጀግኖቻችን በሚገኙበት ቅሊንጦ በተካሄደው በዚህ ዚያራ ገና ከማለዳው በርካታ ህዝብ የቦታው ርቀትና የጉዞው አስቸጋሪነት ሳይገድበው በቦታው ላይ ተገኝቶ ነበር፡፡ ከአዲስ አበባ ከሁሉም አቅጣጫዎች እና ከአጎራባች ከተሞች የመጣው ህዝበ ሙስሊም ለዚያራው ሲጠባበቅ ከእስር ቤቱ አጠገብ የሚገኘው ሰፊ ሜዳ በረጅም ሰልፍና ጠያቂዎች በሚያቆሟቸው መኪናዎች ተሞልቶ አርፍዷል፡፡ ፍጹም ግብረ ገብነትና መተሳሰብ በታየበት በዚህ የዚያራ ፕሮግራም በሺዎች የሚቆጠሩ ዘያሪዎች ተሳትፈው የነበሩ ቢሆንም እድሉን አገኝተው መሪዎቻችንን የጠየቁት ግን ብዙ አልነበሩም፡፡ በቦታው ከተገኘው ሰው መብዛት ባለፈም የጥየቃ ሂደቱን የማጓተት ተግባር ቦታውን በወረሩት ፖሊሶች እንደተፈጸመ ብዙዎች ተናግረዋል፡፡ ሆኖም ለሁለት አመታት በዘለቀው ሰላማዊ ትግላችን መሪዎቻችን በግፍ ሳይታሰሩ አስቀድሞ የነበረን ወኔ እና አጋርነት ዛሬም ከብዙ ግፍ እና መከራ በኋላም እንደፀና መገኘቱ በሚደንቅ ሁኔታ ተስተውሏል፡፡ መሪዎቻችን እንጂ አላማቸው አለመታሰሩን፣ ይህም የማይታሰር አላማ ከግብ እስከሚደርስ ህዝበ ሙስሊሙ ግዳጁን እንደሚወጣ የዛሬው ርቀት እና እንግልት ያልበገረው የዚያራ ፕሮግራም አስመስክሯል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ ለዚያራ መገኘቱን ተከትሎ በመኪና የተጫኑ የፌደራል ፖሊስ ወታደሮች ከነትጥቃቸው መጥተው ቦታውን በመውረር ትንኮሳ መሰል ድርጊቶችን ለመፈጸም የሞከሩ ቢሆንም ሰላማዊው ህዝበ ሙስሊም ግን በትእግስት ሁሉንም አሳልፏል፡፡ በሰላማዊ የእስረኛ ጥየቃ ፕሮግራም ላይ ለምን ወታደሮች መገኘታቸው እንዳስፈለገም ለብዙዎች ግልጽ አይደለም፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ ከአወሊያ እስከ አንዋር እና የዒድ ህዝባዊ ተቃውሞዎች እንደሚያደርገው ሁሉ ዛሬም ሰላምን የማስከበሩን ሚና ሰላም አስከባሪ ከሚባሉት በተሻለ ኃላፊነት ሲወጣ ውሏል፡፡ ሌሎች ታሳሪዎችን ለመጠየቅ የመጡ የተለያየ እምነት ተከታይ ወንድምና እህቶች ረጅሙን ሰልፍ ተቀላቅለው እንዲጠብቁ ፖሊሶች ለማስገደድ ሞክረው የነበረ ቢሆንም ህዝበ ሙስሊሙ ግን በመተሳሰብ ስሜት ለመደበኛ ጠያቂዎቹ ቅድሚያ በመስጠት ቶሎ እንዲስተናገዱ የድርሻውን ተወጥቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሱዳን እና የሕወሓት መከላከያ መኮንኖች የኢትዮጵያን ተቃዋሚዎች ለማፈን ስለሚቻልበት ሁኔታ በአሶሳ እየተማከሩ መሆኑ ተሰማ

በዛሬው ውሎ ምንም እንኳን እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ አጋርነቱን ለመግለፅ በቦታው ቢገኝም ለአጫጫር ዚያራ እድሉን ያገኙት ግን በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ የጥየቃ ሰአቱ ሲጠናቀቅ ሙስሊሙ ወደየቤቱ የተመለሰው ከወትሮው በተለየ የጥየቃ ሰአቱ ዘግይቶ እንዲጀመር በመደረጉ ቅር እንደተሰኘ፣ በሌላ በኩል ደግሞ አጋርነት የማሳያ ፕሮግራሙ በስኬት በመጠናቀቁ እንደተደሰተ ነበር!

በማረሚያ ቤቱ የሚገኙት የሰላም አምባሳደሮቻችን እንደተለመደው አጋርነቱን የገለጸላቸውንና ገና ሲያያቸው እምባው የሚቀድመውን ህዝብ አጽናንተዋል፡፡ ህዝብ ላነሳቸው ህጋዊ ጥያቄዎች መፍትሄ ለማፈላለግ በሰላማዊ መንገድ የታገሉት መሪዎቻችን ከመታሰር እና መሰቃየታቸውም በላይ የወከላቸው ህዝብ ደህንነት እንደሚያሳስባቸው ከፍርግርግ ጀርባ በሙሉ ወኔ የሚታየው ፊታቸው ያስታውቅ ነበር፡፡ ህዝበ ሙስሊሙም በሃገራችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የመሪ እና ተመሪ ጥብቅ ቁርኝቱን አሳይቷል፡፡ በነሱ መታሰር የታሰረው መላው ህዝበ ሙስሊም መሆኑን፣ የፖለቲካ ውሳኔ የሚሰጥበት መጪው ቀጠሮም በህዝብ ላይ የሚሰጥ ውሳኔ እንደሆነ ከወዲሁ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

ውድ የሰላም አምባሳደሮቻችን ሆይ!!! መስዋእትነታችሁን ከንቱ የምናደርግ አይደለንም!!!

ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

2 Comments

  1. እግዜብሔር ይባርካችሁ!
    ጥያቄያችሁ የእስልምና ተከታዮች ጥያቄ አይደለም። ጥያቄያችሁ መብታቸውን የተነጠቁ ኢትዮጵያዊያን ጥያቄ ነው። የጠየቃችሁት መብታችሁን እንጂ የሃይማኖት ጥያቄ አይደለም። ማናችንም ለኢትዮጵያዊያን መብት የምንታገል ኢትዮጵያዊያን በሙሉ፤ ይህ የኔ ጥያቄ ነው ብለን አብረን መነሳት አለብን። የሃይማኖት ጥያቄ ቢሆን ኖሮ፤ እስልምና ተከታዮች ባሉበት ሀገር ሁሉ ትያቄው በተለሳ ነበር። ጉዳዩ ግን ይኼ አይደለም።
    በሁለታችንም ወገኖች ጥፋት አለ።
    የእልምና ተከታይ ባልሆንነው መካከል ይኼን የእልምና ተከታዮች ጉዳይ አድርገን መመልከታችን ጥፋታችን ነው። በእልምና ተከታዮች መካከል ደግሞ ይኼን የእስልምና ተከታዮች ጉዳይ ብቻ አድርጋችሁ በናንተ የተወሰን ማድረጋችሁ ጥፋት ነው።
    ይህ ጉዳይ የኢትዮጵያዊያን በሙሉ ጉዳይ ነው። የምብት ጉዳይ ነው። እናም አብረን ጥያቄውን ይዘን እንነሳ። ከሌሎች የኢትዮጵያዊያን መብት ጥያቄዎች ጋር አንድ ነው። በሳዑዲ አረቢያ ከተገደሉት ወገኖቻችን ጉዳይ ጋር። በአዲስ አበባ ሰላማዊ ደልፍ እንዳያደርጉ ከተከለከሉትና ከታሰሩት ጋር።
    የሚያስመሰግነውና የሚያኮራው የትግል እንቅስቃሴያችሁ ለሌሎቻችን ትምህርት ሊሆን ይገባዋል። የሰላማዊ ትግልን አካሂያድ በደንብ አስተምራችሁናል። አሁንም የሰላማዊ ትግል ዋናው መንገድ መሆኑን አሳይታችሁናል። መማር ይገባናል። ዋናው ጉዳይ ደግሞ፤ ይሳካ ዘንድ፤ ሕዝቡን በሙሉ ኢትዮጵያዊ በሆነ መልክ አብዝቶ፤ ጥያቄዎቻችንን መግፋት ነው። የሕዝብ ቁጥር ሱበዛ፤ የመሳካት ዕድሉ ያይላል። የጥያቄዎቻችን ኢትዮጵያዊ መሆን የሕዝቡን ቁጥር ያበዙታል።
    ጥያቄዎቻችን የምብት ጥያቄዎች ናቸው።
    – የመምረጥና የመመረጥ
    – የመሰብሰብና የመደራጀት
    – የራሳችንን የየግል ሃይማኖት የመከተልና
    – በሃይማኖት ድርጅቶች አሠራር የምንግሥት ጣልቃ አለመግባት
    እነዚህ ሁላችን የምንጠይቃቸውና ሁላችንን በአንድ የሚያሰባስቡን ኢትዮጵያዊ ጥያቄዎቻችን ናቸው።
    አምላክ ሁላችንን ይርዳን
    አሜን

  2. Dimtsachin yisema, the voice of satan and the renaissance of khawarijites.

    Dimtsachin yisema from Ethiopia are collections of salafis, and these present day salafis are wahabbis/takfiri. These are all the seeds of khawarijites. They are dogs of the hellfire as mentioned in a Hadith. Therefore dimtsachin yisema are the bells of satan and not the Muslims.
    Present day salafis (Wahabbis/takfiris)
    1. Follow footsteps and views of Individual persons like ibn abdulWahab which is the kernel faith of ibn al Saud family state structure.
    2. Immature ( Most of them are under 45 age)
    3. Ignorant (They have surface knowledge only about the Quran and the hadith. They have little or no knowledge about the basic tenets of faith in Islam).
    4. They have no knowledge of social, religious and political events happened in different countries in the past and present history.
    5. Worldly (Materialist, which give high value for wealth and luxury life)
    6. Disrespecting older people
    7. Fake (show biz that is outwardly seem very religious while inwardly nonsense)
    8. Cosmetic ( stick and stress on minor and insignificant Islamic issues like shortening trouser, growing beard etc. which are weightless and worthless in the sight of ALLAH)
    9. Public wearing unnatural (Some men look like artist, some look like sportsman, some look like womanish)
    10. They walk in pride and deny greeting outside their community
    11. They seem to dislike shirk but do themselves shirk ignorantly in different circumstances
    12. No life experience in all sorts of life challenges
    13. Deciding to themselves perfection and looking others as defective and imperfect)
    14. They do not know why and to whom they are performing Salat in Islam.
    15. They mislead many young Muslims by imitating externality (no analytical approach)
    16. Arrogant
    17. Boastful
    18. Tyrant (They are the ever worst people seen on earth in the history of Islam like that of the cruel colonialists of the western countries during the colonial era)
    19. They declare or do takfir on a Muslim. (But as to the question of a person being in fact a believer or not, it is not the duty of any human being to decide it. This matter is directly to do with ALLAH, and it is He Who shall decide it on the day of Judgment)
    20. They Collaborate with and receive support from Western countries like Britain and USA, who are non-Muslims.
    21. They do not like to be named by the title of “Wahhabi”. This is because of the desire to shade over their bloody historical record. All of Wahhabism’s recent cosmetic changes to improve its own image are to deceive most Muslims.
    22. They do their own business in the name of Muslim affairs and at the expense of poor Muslim’s life, energy, time, and money.
    23. Have no clear idea about innovation (Bidaa). They are highly confused about this issue.
    24. Ideally they hang up themselves high in the sky and look down the rest Muslims as inferior and dust particle.
    25. Many more …
    ALLAH Knows best

Comments are closed.

Share