በሳዑዲ ትናንት ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ተጋጭተው የነበሩት ኢትዮጵያውያን ወደ ጅዳ አየር ማረፊያ አምርተዋል

ከነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ በፌስቡክ ገጹ እንዳስነበበው፦
አስደሳቹ ዜና

በትናንትናው እለት ከጊዜያው ማቆያ በር ለቀናት ያለ ምግብና ውሃ ለሶስት ቀናት መሰቃየታቸውን ተከትሎ ከሳውዲ የጸጥታ ሃይሎች ጋር ተጋጭተው የነበሩት ወገኖች ዛሬ ጉዳያቸው አልቆ እና ቲኬት ተቆርጦላቸው ወደ ጅዳ አየር ማረፊያ ማቅናታቸውን ተጨባጭ መረጃ ደርሶኛል !

በትናንቱ ግጭት የጅዳ መካ አውራ መንገድ ለሰአታት ተዘግቶ የነበረ ሲሆን ብዙ ነዋሪዎችን ስጋት ላይ ጥሎን ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለ መካ ውስጥ ኩደይ በሚባል ቦታ ዛሬ እስከ እኩለቀን 8000 የሚደርሱ ኢትዮጰያውያን “ወደ ሀገራችን እንግባ! ” በሚል ተሰባስበው እንደሚገኙ ለማረጋገጥ ችያለሁ።

መዲናን አካባቢ ያለው ሁኔታወች ከቀናት በፊት ሁከት ተፈጥሮ ዩኒቨርሲቲ ለአንድ ቀን ካስዘጋ ወዲህ መረጋጋት ተስተውሏል። የጅዳ ቆንስላ ወደ ዚያው በላካቸው ሁለት ዲፕሎማቶች በኩል የሊሴ ፖሴ መተላለፊያ ሰነድ መስጠት መጀመሩ መረጃ ደረወሶኛል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ መዲና ላይ የመጓጓዣ ሰነድ ያሟሉትን ዜጎች ወደ ሃገር ቤት ለመውሰድ በረራውም ከመዲና አዲስ አበባ እንደሚጀመር ምንጮቸ ያሰባሰቡት መረጃ ይጠቁማል ።

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያዊነትን ከቴዲ አፍሮ ጋር በኒውዮርክ እናክብር – መግቢያ ነፃ (ከዲሲ አውቶቡስ ተዘጋጅቷል)

2 Comments

Comments are closed.

Share