November 29, 2014
3 mins read

በመቐለ አራት የፖሊስ ኮማንደሮችና አንድ የድህንነት አባል በወንጀል ተከሰሱ

ከአስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኤል

የአንድነት ለፍትህና ዲሞክራሲ (አንድነት) አባል ወጣት ሽሻይ አዘናው ለ24 ቀን መሰወሩ ተያይዞ በ26/02/2007ዓ.ም ከሚሰራበት የስራ ቦታው ታፍኖ በመቐለ ኮሙሽን ፖሊስ ክልል ትግራይ ልዩና ፅኑ እስርቤት ታስሮ ህገ መንግስታዊን መብቱ በመከልከል ጠበቃ እንዳያአማክረው ምግብ እንዳይገባለት ፡ ዘሞዶቹና ጓደኞቹ እንዳያዩት ተነፍጎት 12 ቀን ያህል በህቡእ ታሰሮበት ከነበረበት ተሰውሮ እስከ 18/03/2007ዓ.ም በጠቅላላ ለ24 ቀን በመሰወሩ መጀመርያ ከሰራ ቦታው አስገድደው ቤቱ በርቡረው አስፈላጊ ቁሳቁስ ወስደው የቀረው ንብረቱ `ላፊነት በጎደለው ጥለውት አስረው ለክልሉ ፖሊስ ኮምሽን መርማሪ ኮማንዶሮች ያስረከቡና፡ የክልሉ የምርመራ ኮማንደሮች ደግሞ ወጣቱ አስረው 24 ቀን በመሰወራቸው ምክንያት በመቐለ ቀዳማይ ወያነ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት በወንጀል ተከስው መሪማሪ ፖሊስየተከሰሱት ኮማንደሮች የማጣራት ምስክርነት ለመቀበል ለ23/03/2007ዓ.ም ለምስክሮች እንዲቀሩ ትእዛዝ ሰጥዋል፡፡


ከተከሰሱት ውስጥ የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. ኮማንደር ገ/ሂወት ካሕሳይ የመቐለ ከተማ ፖሊስ ዋና ኣዛዥ
2. ኮማንደር ሙሩፅ በረኸ የመቐለ ከተማ ፖሊስ ምክትል ኣዛዥ
3. ኮማንደር አለም ምስግና የክልል ትግራይ ፖሊስ ኮምሽን ዋና የምርመራ ኣዛዥ
4. ኮማንደር ሰዓረ ምራጭ የክልል ፖሊስ ኮምሽን የምርመራ ተክኒክ `ላፊ
5. ሓጎስ በሚል ሥም የሚታወቅ የድህንነት አባል


የክሱ ዝርዝር ይዘት
የሃገራችን ህገመንግስት በመጣስ፡ ህግ አማካሪ በመከለከላቸው ምግብ እንዳይገባ ፡ ከዘመዳቸውና ጓዶኞቹ እንዳገናኝ ከማድረግ አልፉ ሽሻይ አዘናው አሁንም የለም ተሰውረወዋል በተጨማሪም እስካሁን አሁን በህቡእ ይሁን በግልፅ ፍርድቤቱ መቅረቡ አይታወቅም በማለት ክስ ዛሬ 18/03/2007ዓ.ም ገብቷል ፍትህ ይገኝ ይሆን ክትትሉ ለህዝቡ ከሻሽ ለአንድነት ለፍትህ ለዲሞክራሲ(አንድነት) በመወከል አቶ አስገደ ገ/ስላሴ፡-
የፖሊስ ኮማንደሮችና የድህንነት አባሉ ለፈፀሙት ወምጀል በምስክርነት የተመዘገቡ


1. መምህር ታደሰ ቢተውልኝ ከመቐለ ስ.ቁ. 0914 47 98 11
2. አቶ ገ/ሚካኤል ከመቐለ ሰ.ቁ. 0914 74 83 52
3. ዓንዶም ገ/ስላሴ ከመቐለ ስ.ቁ. 0914 75 43 77
4. መምህር ገብሩ ሳሚኤል ከመቐለ ሰ.ቁ. 0921 38 91 53
5. ጉዑሽ አዘናው ወረታ ከሰሜን ምዕራብ ዞን ስ.ቁ. 0935 80 62 28
ከላይ የተዘረዘሩት ተከሳሽ የፖሊስ ኮማንደሮች ከ30 አመት በላይ የህ.ወ.ሓ.ት ታጋዮች የነበሩ ናቸው፡፡

2007 election
Previous Story

የወያኔ ምርጫ – ገረጭራጫ! (ሥርጉተ ሥላሴ)

Next Story

Hiber Radio: በመስቀል አደባባይ ለተጠራው የአዳር የተቃውሞ ሰልፍ የአደባባይ ቅስቀሳ ይጀመራል፤ ሁበር በኔቫዳ ታገደ

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop