በሃዋሳ አንድ ሌትር ቤንዚን 70 ብር እየተሸጠ መሆኑ ተሰማ

በሃዋሳ ከተማ ከፍተኛ የቤንዚን እጥረት መከሰቱና አንድ ሊትር እስከ 70 ብር እየተሸጠ መሆኑ ተዘገበ፡፡ የከተማው የንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ ሀላፊ አቶ ቦንቲ ቦቼ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት በከተማው 15 ነዳጅ ማደያዎች ቢኖሩም በሙሉ አቅም እየሰሩ ያሉት አምስቱ ብቻ ሲሆኑ አምስቱ ደግሞ እያቆራረጡ አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው፡፡

ቀሪዎቹ አምስቱ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ስራ አቁመዋል፡፡ ለከተማው በቂ ነዳጅ አቅርቦት ስለሌለ ከፌዴራል መንግስት ጋር የከተማዋ ነዳጅ ኮታ ከፍ እንዲል እየተደራደሩ መሆኑን የተናገሩት አቶ ቦንቲ ከአቅርቦቱ እጥረት በተጨማሪ ህገ ወጥ የቤንዚን ንግድ በከተማው መስፋፋቱንም አስረድተዋል፡፡ ይህን ችግር ለመከላከል ማንም ሰው ከማደያዎች በጄሪካን ነዳጅ እንዳይገዛ በመከልከል ጥረት ተደርጎ የነበረ ቢሆንም አሁን ደግሞ አብዛኛው ሰው ሞተር ሳይክልና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ እየገዛ በመሆኑ እጥረቱ እንደተባባሰ ገልፀዋል፡፡

ይህም ሆኖ ሳለ በነዳጅ ማደያዎች ከፍተኛ ሰልፍ እንደሚታይና ሰልፍ ደርሶት የቀዳ አሽከርካሪ ለሌላ ሊትሩን እስከ 70 ብር እየሸጠ መልሶ እንደሚሰለፍም መታወቁን ሃላፊው ተናግረዋል፡፡ የከተማው የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ሃላፊው አቶ ዘሪሁን ሰለሞን በበኩላቸው በከተማው ማታ ማታ ነዳጅን በኮንትሮባንድ የማሸሽ ተግባር እየተፈፀመ እንደሆነና ይህን ተከትሎ በተደረገ ክትትል የወንጀሉ ተሳታፊዎች በህግ ቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን ለአዲስ ማለዳ ገልፀዋል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=et9pbbzq6mg&t=36s

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአረና አመራሮች በሐውዜን ከተማ አዳራሽ ውስጥ ታግተዋል
Share