በአዲስ አበባ የጦር መሳሪያ ዋጋ ይፋ ሆነ

በተመስገን ደሳለኝ አማካኝነት በአዲስ አበባ አየታተመ የሚወጣው <ፍትህ> መጽሄት በዛሬ እትሙ በከተማው በህገ ወጥ መንገድ እየተሸጠ ስላለው የጦር መሳሪያ ዋጋ ይፋ አድርጓል::

መጽሄቱ ይፋ ባደረገው የምርመራ ሪፖርቱ ከመትረየስ ጀምሮ እስከ ስናይፐርና ሽጉጥ ድረስ የጦር መሳሪያ በጥቁር ገበያ እየተቸበቸበ እንደሆነ አስረድቷል:: በዚህ መሰረት ከፍተኛው አርፒጂ ሲሆን ዋጋውም 120 ሺህ ብርና የጥይቱ ዋጋ ደግሞ 130 ብር መሆኑን ጠቁሟል:: በሁለተኝነት የተቀመጡት ስናይፕርና ብሬን ሲሆኑ ዋጋቸውም 100 ሺህ ብር መሆኑን ያስረዳው ፍትህ መጽሄት የስናይፐር ጥይት በ125 ብር እንዲሁም የብሬን ጥይት በ100 ብር እንደሚሸጥ ገልጿል:: የፒኪኤም መትረየስ ዋጋ ደግሞ 80 ሺህ ብር እንደሆነና ጥይቱ በ75 ብር እንደሚሸጥ ተናግሯል:: ኤምፎርቲና ኤኬኤም የተሰኙት ክላሾች ደግሞ በ65ሺህና በ50ሺህ ብር እየተሸጡ መሆኑን ዐስረድቷል::

በአዲስ አበባ በጥቁር ገበያው ላይ ስድስት አይነት ሽጉጦች መኖራቸውን የጠቆመው ፍትህ መጽሄት የእነዚህ ዋጋም
– ስታር 35ሺህ ብር ጥይቱ 70 ብር …
– ማካሮቭ 50 ሺህ ብር ጥይቱ 70 ብር…
– ፎርቲ ፋይፍ 40 ሺህ ብር ጥይቱ 90 ብር…
– ቱርክና አሜሪካን ኮልት እያንዳንዳቸው 12 ሺህ ብርና ጥይታቸው 50 ብር እንደሆነ ዘርዝሯል::

በአዲስ አበባ ቦምብም ገበያው ላይ አለ:: እንደመጽሄቱ ኤፍዋንና የጭስ ቦምብ በ1ሺህ ብር በህገ ወጥ መንገድ ይሸጣሉ::

የተመስገን ደሳለኝን ሰፊ ትንታኔ በዘ-ሐበሻ ኦፊሻል ቱብ ይዘን እንቀርባለን::
https://www.youtube.com/watch?v=ibs_Mi6_X_s

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሽብርተኛው ወያኔ/ኢህአደግ በሀይማኖቶችና በህዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚያደረገውን እኩይ ሴራ እናወግዛለን! -ENTC
Share