መንግስት በኤፈርት ላይ ምርመራ እንዳልጀመረ ገለፀ

ከፍተኛ ሙስና ይፈፀምባቸዋል ተብሎ በብዙዎች በሚነገርለት ኤፈርት ላይ መንግስት ምንም አይነት ምርመራ ማድረግ እንዳልጀመረ ተገለጸ፡፡ የፌዴራል አቃቤ ህግ የ100 ቀናት የስራ እቅዱን አስመልክቶ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሚኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ዝናቡ ጡኑ እንደገለፁት በኤፈርትም ሆነ በተመሳሳይ መልኩ በተቋቋሙ ኢንዶውመንት ድርጅቶች ላይ መንግስት የጀመረው ምርመራ የለም፡፡

እንደዚህ አይነቶቹ ድርጅቶች ተጠሪነታቸው ለተመሰረቱበት ክልል እንደሆነ አስረድተውም በኤፈርት ላይ ምርመራ ማድረግ የሚችለው የትግራይ ክልል ብቻ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ሰሞኑን የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚደንቱ ዶ/ር ደብረፅዮን የሰጡትን አስተያየት በተመለከተ ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ዝናቡ ምላሽ ሲሰጡ በሰብአዊ መብት ጥሰትና በሌብነት ላይ የተጀረው ዘመቻ በማንኛውም ብሄር ላይ ያላነጣጠረና ፖለቲካዊ አንድምታ የሌለው እንደሆነም አስረግጠው አስረድተዋል፡፡

የፀረ ሌብነቱ ዘመቻ በሜቴክ ላይ ብቻ እንደማይወሰንና በተለያዩ ትላልቅ ሜጋ ፕሮጀክቶች ላይም ምርመራው እየተከናወነ መሆኑን ያስረዱት የህዝብ ግንኙነቱ እየተመረመሩ ያሉትን ተቋማት ስም ከመጥቀስ ተቆጥበዋል፡፡ ወደ አገር ው

ስጥ እየገባ ያለውን ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በተመለከተ ደግሞ ከዚህ ጀርባ ለውጡን ለመደናቀፍ ያሰቡ ሀይሎች እንዳሉ አስረድተው በተጨማሪም የተለያዩ ሀገራት፣ ቡድኖችና ግለሰቦች ሀብትን ለማካበት እየተረባረቡ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የህግ የበላይነትን ለማስጠበቅና ፍትህ ስርዓቱ የሚታዩ ማነቆዎችን ለመፍታት ተቋሙ ከመቼውም በላቀ ሁኔታ አገራዊ ለውጡን ለማስቀጠል የህግ እና የፍትህ ማሻሻያ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኑን የነናገሩት አቶ ዝናቡ የወንጀል ድርጊቶችን ትኩረት ሰጥቶ መከላከል ተቋሙ የተሰጠውን አገራዊ ኃላፊነት ለማሳካት የባለ አንድ ገጽ እቅድ አዘጋጅቶ ወደ ተግባር መገባቱን ጠቁመዋል፡፡

የእቅዱ መነሻ ሃሳቦችም የሕግ የበላይነት አለመረጋገጥና ደካማ ፍትህ ሥርዓት፣ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ከፍተኛ ጥሰት፣ደካማ የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥ እና ሕገ ወጥነትና ስርዓት አልበኝነት መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ እነዚህን በመከላከል እና በመቆጣጠር የሕግ የበላይነትና ፍትህ ሥርዓትን ግንባታን ማጠናከር፣የፍትህ አግልግሎትን አሰጣጥ በማሻሻል እና የሰው ሃብትን አቅም በመገባት ላይ ትኩረት ሰጥቶ በህዘብና በመንግሰት አመኔታን ያተረፈ ጠንካራ ተቋም ለመገባት በመሰራት ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ መስሪያ ቤታቸው በማህበራዊ ድረ-ገጽ የሚታዩ የጥላቻ ንግግሮችን የሚያስቀር ሕግ ማውጣትና መተግበር እንዲሁም ሕገ ወጥነትን፣ ስርዓት አልበኝነትንና የመንጋ ፍትህን ለመቆጣጠር ከአሁን በፊት ታይተው የማይታወቁ ህጎችን የማርቀቅና የማሻሻል ስራዎችን እንዳቀደም አስረድተዋል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=wcjYZaYCiUM&t=245s

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሕወሓት ባደራጃቸው የትግራይ ወጣቶች መንገድ ተዘግቶበት የነበረው መከላከያው  መንገድ አስከፍቶ ወደ ተላከበት መንቀሳቀሱን የመከላከያ ምንጮች ገለጹ
Previous Story

ዶ/ር አብይ አህመድ ሁሉንም የተፎካካሪ ፓርቲዎች ጽሕፈት ቤታቸው ጠሩ

Next Story

35 ሚሊየነር ነጋዴዎች ታሰሩ

Latest from ዜና

ልዕልት ሂሩት ደስታ ምን አይነት ሰው ነበሩ?

ከአንሙት ስዩም እስካሁን በኖርኩባቸው አመታት የተረዳሁትና የገባኝ አንድ ነገር አለ፡፡ በዝህብ ላይ መጥፎ ስራ የሰሩትን ወንጀለኞች ለፍርድና ለቅጣት የማቅረብና የማስፈረድ ልምድ ያለንን ያህል፤ መልካም ለሰሩት ግለሰቦች ግን ተመጣጣኝ የሆነ የስማቸው

Share