ሕወሓት የቅማንትን ካባ ለብሶ በመተማ ጥቃት አደረሰ

ሕወሓት ታላቋን ትግራይ ለመመስረት የቅማንትን ሕዝብ ከአማራ በመነጠል ትግራይን ከቤኒሻንጉል በማገናኘት አባይን ለትግራይ እንደ ኤሌክትሪክ ኃይል ምንጭነት መሬቱን ደግሞ ለልማት መጠቀም ይፈልጋል ሲሉ የቀድሞው የየጎንደር ሕብረት ሊቀምንበር አቶ አበባ ንጋቱ ሚኒስታ ውስጥ በተደረገ ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ በጥናት የተደገፈ መረጃ አቅርበው ነበር:: ሕወሓት የቅማንት ማንነት በሚል በውጭ ሃገር የሚገኙ የቅማንት ተወላጆችን በገንዘብ በመግዛት እንዲሁም የዳኡድ ኢብሳ ኦነግ በሚመራው ኦ ኤን ኤን እና አልፎ አልፎም በጀዋር መሐመድ ኦ ኤሜን ቴሌቭዥን ጣቢያዎች የቅማንትን ጉዳይ ሕዝብን እንዲያነሳሱበት በማድረግ ትልቅ ሴራ በመጫወት ላይ መሆኑን የሚገልጹት ደግሞ የአካባቢው ተወላጅ አቶ ጌታቸው ትርፌ ናቸው::

ባሳለፍነው ቅዳሜ በምዕ/ጎንደር ዞን የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ እንደ አዲስ መመሥረቱን አስመልክቶ በነጋዴባሕር ከተማ የተከናወነን ስነስርዐት ተከታትለው መመለሳቸው ለሕወሓት ትልቅ ሎተሪ ነበር:: የቅማንትን እና የአማራን ሕዝብ ለማጣላት ቀን ከለሊት ገንዘብ መድቦ እየሰራ ያለው ሕወሓት በነዚህ አርሶ አደሮች ላይ ተኩስ እንዲከፈት በማድረግ 3 ቄሶችን ጨምሮ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ:: ከዚህ ቀን በኋላ በአካባቢው ሰላም የለም የሚሉት አቶ ጌታቸው ይህን ተከትሎም እሁድ እና ሰኞች ቀናት በምዕራብ ጎንደር ዞን በሚገኙ በርካታ ቀበሌዎች አለመረጋጋት ተፈጥሮ፣ ጎንደርን በመተማ ከሱዳን ጋር የሚያገናኘው መንገድ ለሁለት ቀን ተዘግቶ እስከመዘጋት ደርሶ ነበር ብለዋል::

“አለመረጋጋቱ ወደ ብሔር ግጭት የተቀየረ ሲሆን፣ ሕወሓት የራሱን ወታደሮች በመጠቀም በቅማንትና በአማራ አርሶ አደሮች መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ሰዎች የሞቱና የቆሰሉ በማስመሰሉ በተወሰነ ደረጃ ተሳክቶለታል” የሚሉት አቶ ጌታቸው “ከትግራይ የመጡ ሚሊሻዎች ቅማንት በመምሰል እንደገና በፈጠሩት ችግር ከትናንት ከሰዐት በኅላ ጀመሮ አዳሩን ግጭቱ ተባብሶ ቀጥሏል:: ግጭቱ በከባድ መሳሪያ የተደገፈ ሲሆን፣ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደተቋረጠ ይገኛል።” ብለውናል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ተወዳጇ ድምጻዊ ከዚህ ዓለም ድካም አረፈች

ትናንት ለሊት ቁጥራቸው ከ12 በላይ የሚሆኑ የአማራ ተወላጆች ከትግራይ በመጡ ሚሊሻዎች መገደላቸውን መስማታቸውን የሚገልጹት አቶ ጌታቸው ሌሊቱን በነጋዴ ባህር እና በሺንፋ መንደሮች ቤቶች መቃጠላቸውን እና 15 ሰዎች በነዚህ አካባቢዎች በተተኮሰ ጥይት ሕይወታቸው ማለፉን አቶ ጌታቸው ገልጸውልናል::

በሌላ በኩል ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በሰጠው አስተያየት “ትህነግ/ህወሓት የሚፈልገው አማራው በወንድሙ ቅማንት ላይ ቃታ እንዲስብ ነው። “አማራና ቅማንት” እየተባባለ እንዲፋጅ ነው። ትህነግ/ህወሓት የሚፈልገው የእርስ በእርስ ፍጅቱን ነው። ይህ ከሆነ የመጨረሻ ስኬቱ ነው። ጦርነቱን ያወጀው ትህነግ/ህወሓት መሆኑ መታወቅ አለበት። ትህነግ በከፈተው ጦርነት የቅማንት ሕዝብ ተጠያቂ እንዲደረግ ይፈልጋል። ከዚህ ሴራ መራቅ ያስፈልጋል።” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል::
https://www.youtube.com/watch?v=0OBDIk-J-Do&t=71s

Share