ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ‹‹ዶክተር ዐብይ የምርምሬን ትክክለኛነት መመስከራቸው አስደስቶኛል›› አሉ

‹‹የኦሮሞና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ›› በተሰኘ አነጋጋሪ መፅሀፋቸው የሚታወቁት ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ‹‹ዶክተር ዐብይ የምርምሬን ትክክለኛነት መመስከራቸው አስደስቶኛል›› አሉ፡፡ ነዋሪነታቸው በአሜሪካ የሆነው ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ፤ በቅርቡ የኦሮሞ የአማራና የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ እውነተኛና ትክክለኛ የዘር ምንጭ ምን እንደሆነ ከ5ሺ ዓመታት በላይ ወደኋላ ተጉዘው፣ ማስረጃ አስደግፈው፣ ምንጭ ጠቅሰው፣ እስካሁን ድረስ የምናውቀውን የኢትዮጵያን ታሪክ የሚሽር፣ አዲስ የኢትዮጵያ ታሪክ በዝርዝርና በጠራ አቀራረብ የሚገልጽ ድንቅ መጽሐፍ ማቅረባቸው የሚታወቅ ነው፡፡
ፕሮፌሰሩ በማህበራዊ ገፃቸው ስለዶክተር አብይ ሲናገሩ ‹‹ በፍራንክፈርት ጀርመኒ ባደረጉት ንግግራቸው መጨረሻ ላይ ስለ አማርኛ እና ኦሮምኛ ቋንዎች፥ እንዲሁም ስለ ኦሮሞዎች እና አማሮች ዝምድና ያደረኩትን ምርምር እና ጽሁፍ ጠቅሰው በእኔ ምርምር መስማማታውቸን በማረጋገጣቸው ደስ ብሎኛል።
መጽሀፉ በዐለም ዙርያ 95% በሚሆትኑ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ተቀባይነት አግኝቶ በተለይ አማራውን እና ኦሮሞውን፥ በጠቅላላው የኢዮጵያን ህዝቦች አቀራርቧል። አግባብቷል። ሆኖም አንዳንድ ፓለቲከኞች እና ካድሬዎች መጽሀፉን ተረት ነው እያሉ ለማጣጣል ሞክረው ነበር። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ለእውነት ቆመው ስለተበቀሉልኝ ምስጋናዬ ወደር የለውም።›› ብለዋል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=urrQCDkbbQE&t=489s

ተጨማሪ ያንብቡ:  እነደ ዔሳው ብኩርናቸሁን ለሸጣችሁ የኪነ-ጥበብ ሰዎች (ከአሮን)
Share