ከተለያየ የአማራ ክልል በግፍ ታሰረው በግንቦት 7 የተከሰሱ የአማራ ክልል ተወላጆች የደረሱበት አልታወቀም

ለገሠ ወ/ሃና

በአንባገነኑ አገዛዝ ከመላው አማራ ክልል ታፍነው የታሰሩት የአማራ ክልል ተወላጆች ግንቦት ሰባት ምን እንደሆነ በቅጡ የማያውቁት ግን በግንቦት ሰባት ተከሠው መካራቸውን የሚያዩት የአማራ ልጆች በትላንትናው እለት ማለትም ግንቦት 2/2010 ዓም 10 ሰዓት አካባቢ ከ400 በላይ ልዩ ሀይል ባለ ቀይ ቦኔት ሀይል ወደ እስረኞች ቤት በመግባት በርካታ እስረኞችን በመደብደብ ከ97 በላይ የአማራ ክልል እስረኞችን ወዳልታወቀ ቦታ ተወስደዋል የተወሰኑ እስረኞች በትላንትናው እለት ሳይወሰዱ ዞን አንድ ቢያድሩም ዛሬ ጠዋት ዘመነ ጌቴ ,ተስፋየ አያሌውን ጨምሮ በርካታ እስረኞች ተወስደዋል ይህንን መረጃ የሰጠኝ የጎንደር ልጅ የግንቦት ሰባት ተከሳሽ የሆንን በአሁኑ ሰዓት የቀረነው በጣት የምንቆጠር የግንቦት ሰባት ተከሳሾች በየቤቱ እየገቡ እየለቀሙ ስለሆነ ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ ከዚህ መወሰዳችን አይቀርም የተወሰዱትም ወዴት እንደሆነ አናውቅም እኛም ካሁን በኋላ የምንሆነው አይታወቅም ይህንን ለህዝባችን አድርስልን ካሁን በኋላ ላታገኙን ትችላላችሁ ብለውኛል ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  "በህወሓት ላይ የተወሰደው የመጀመሪያ ዙር እርምጃ በስኬት ተጠናቋል" - ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ
Share