Sport፡ አትሌት መሰለች መልካሙ ወደ ሮተርዳም ማራቶን ተመለሰች

ያለፈው ዓመት የሮተርዳም ማራቶን አሸናፊዋ አትሌት መሰለች መልካሙ በዘንድሮውም የሮተርዳም ማራቶን ክብሯን ለማስጠበቅ እንደምትሮጥ የውድድሩ አዘጋጆች አስታው ቀዋል፡፡ በቀጣዩ ጥቅምት አሥራ ሰባት ቀን በሚካሄደው የሮተርዳም ማራቶን መሰለች የቀድሞ ድሏን ልትደግም እንደምትችል የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ማህበር ድረ-ገፅ ዘገባ አመልክቷል፡፡
መሰለች ባለፈው ዓመት ባሸነፈችበት ውድድር 2፡21፡01 ሰዓት በማስመዝገብ የቦታውን ክብረወሰን ማሻሻል ችላለች፡፡ የተመዘገበው ሰዓት መሰለችን ሦስተኛዋ የምንጊዜም የማራቶን ፈጣን ሯጭ እንድትባልም አስችሏታል፡፡የሃያ ስምንት ዓመቷ መሰለች በአስር ሺ ሜትርም ሁለተኛዋ የዓለም ፈጣን ሯጭ ከመሆኗ በተጨማሪ የአፍሪካን ክብረወሰን በስሟ ያስመዘገበች ጠንካራ አትሌት መሆኗ ይታወሳል፡፡
መሰለች ከመም ውድድሮች ራሷን ካገለለች ወዲህም በአገር አቋራጭ ውድድሮች ድንቅ አትሌት መሆኗን አስመስክራለች፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በማራቶን የተሳካላት አትሌት ለመሆን በቅታለች፡፡
መሰለች ያለፈውን የፍራንክፈርት ማራቶን ባሸነፈችበት ወቅት በሰጠችው አስተያየት በአስር ሺ ሜትር ያሳካችውን ፈጣን ሰዓት በማራቶንም መድገም ትፈልጋለች፡፡ የፍራንክፈርት ማራቶን አዘጋጆች «መሰለች ያሰበችውን የምታሳካበት ወቅት አሁን ነው »ብለዋል፡፡
ባለፈው ለንደን ማራቶን አምስተኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችው መሰለች ባሳየችው ጥንካሬ በሞስኮው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ የማራቶን ቡድን ውስጥ ብትካ ተትም በሞስኮው ሻምፒዮና እስከ ሰላሳ ሰባተኛው ኪሎ ሜትር ድረስ ከመሪዎቹ ጋር ተፎካክራ በደረሰባት የጡንቻ መሸማቀቅ ምክንያት ውድድሩን ማቋረጧ ይታወሳል፡፡
መሰለች የሞስኮውን ሻምፒዮና አቋርጣ ከወጣች ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደ ልምምድ መመለሷ ታውቋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ልምምዷን በተሳካ ሁኔታ በማካሄዷ የፍራንክፈርት ማራቶንን ለመሮጥ ወስናለች፡፡
የፍራንክፈርት ማራቶን የአትሌቶች ማኔጀር ክሪስቶፕ ኮፕ ለአይደብል ኤፍ በሰጠው አስተያየት መሰለች በውድድሩ ለመካፈል ትልቅ ፍላጎት እንዳላትና ፈጣን ሰዓት ለመሮጥ እንዳቀደችም ጠቁሟል፡፡
ማኔጀሩ ከመሰለች በተጨማሪ ከ2፡22 በታች ሰዓት ያላቸው ሌሎች ሦስት አትሌቶችም ይሳተፋሉ ብለዋል፡፡ ይህም ውድድሩን ጠንካራና ክብረወሰን ሊሻሻልበት የሚችል ይሆናል ተብሎ እንዲጠበቅ አድርጎታል፡፡
አትሌት ትርፌ ፀጋዬ በውድድሩ የምትካፈልና ከመሰለች ቀጥሎ በርቀቱ ሁለተኛው ፈጣን ሰዓት ያላት አትሌት ነች፡፡ ትርፌ በውድድሩ የአሸናፊነት ግምት ከተሰጣቸውና ጠንካራ ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁ አትሌቶች መካከልም ግንባር ቀደሟ ነች፡፡
አትሌት ትርፌ ባለፈው በርሊን ማራቶን 2፡21፡19 በመሮጥ የራሷን ምርጥ ሰዓት ማስመዝገቧ የሚታወስ ሲሆን በተመሳሳይ ዓመት የዱባይ ማራቶንን በ2፡23፡23 ሰዓት አሸንፋለች፡፡ በቦስተን ማራቶን ደግሞ በ2፡28፡09 ሰዓት አምስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች፡፡
ኬንያዊቷ ኤኒስ ጂፕኪሩይ ከመሰለችና ትርፌ ቀጥሎ በውድድሩ ትኩረት ያገኘች አትሌት ሆናለች፡፡ ጂፕኪሩይ ባለፈው የአምስተርዳም ማራቶን ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ አይዘነጋም፡፡
አትሌት ማሚቱ ደስካ በውድድሩ ከሚካፈሉ አትሌቶች ጠንካራ ተፎካካሪ ትሆናለች ተብላ የምትጠበቅ ኢትዮጵያዊት አትሌት ነች፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት የፍራንክፈርትን ማራቶን ፈጣን በተባለለት 2፡21፡59 ሰዓት ማሸነፍ የቻለችው ማሚቱ እአአ የ2o11ክብሯን መልሳ ለማግኘት ጠንካራ ፉክክር እንደምታደርግ ታውቋል፡፡ ኬንያዊቷ ካሮሊን ኪሌል በውድድሩ ሌላ ትልቅ ትኩረት ሊሰጣት የሚገባ አትሌት ሆናለች፡፡
አትሌቷ ከሦስት ዓመት በፊት የፍራንክፈርት ማራቶንን በ2፡23፡25 ሰዓት ማሸነፍ ብትችልም ከእዚያ በኋላ ሌላ ተመሳሳይ ድል ማጣጣም አልቻለችም፡፡ ይሁን እንጂ አትሌቷ ከጊዜ ወደ ጊዜ በርቀቱ የነበራትን ሰዓት እያሻሻለች መምጣቷ በዘንድሮው ውድድር ትኩረት እንዲሰጣት አስችሏታል፡፡ ኪሌል ከሁለት ዓመት በፊት የቦስተን ማራቶንን በ2፡22፡36 ሰዓት ማሸነፏ ይታወሳል።
ለሰላሳ ሁለተኛ ጊዜ በሚካሄደው በእዚህ ውድድር ከተለያዩ አገሮች የተውጣጡ ከአሥራ አምስት ሺ በላይ አትሌቶች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአርሰናል የምንጊዜውም ምርጥ ተጫዋች ዴኒስ ቤርካምፕ "ከአርሰናል ጋር መሥራት እፈልጋለሁ" አለ
Share