September 18, 2013
4 mins read

አና ጎመሽ – ርዕዮትና እስክንድር “የኅሊና እሥረኞች ናቸው” አሉ

hana

 

ለያዝነው የአውሮፓ 2013 ዓ.ም የአውሮፓ ፓርላማ የሳኻሮቭ ሽልማት ሁለት ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ሰባት ዕጩዎች ቀርበዋል፡፡
ለያዝነው የአውሮፓ 2013 ዓ.ም የአውሮፓ ፓርላማ የሳኻሮቭ ሽልማት ሁለት ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ሰባት ዕጩዎች ቀርበዋል፡፡

ሽልማቱ ለሃሣብ ነፃነት ለሚታገሉና ለታገሉ የሚሰጥ የአውሮፓ ፓርላማ ዓመታዊ ክንዋኔ ነው፡፡

ኢትዮጵያዊያኑን ዕጩዎች ርዕዮት ዓለሙንና እስክንድር ነጋን ለሽልማት ካቀረቡት አርባ የአውሮፓ ፓርላማ አባላት አንዷ የፓርላማው አባል፣ እንዲሁም የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴው እና የሰብዓዊ መብቶች ንዑስ ኮሚቴ አባል የሆኑት አና ጎመሽ ይገኙበታል፡፡

ርዕዮት ዓለሙ


በአሁኑ ምርጫ ርዕዮት እና እስክንድር ቁጥራቸው ወደ 12 ከሚደርስ ከመላው ዓለም ከተጠቆሙ ሰዎች መካከል ወደ ሰባቱ አጭር ዝርዝር የገቡ መሆኑን ሚስ ጎመሽ ጠቁመው ፓርላማው የፊታችን ጥቅምት ውስጥ በሚያደርገው የተሟላ ስብሰባው ላይ አንዱ ለሽልማቱ በድምፅ እንደሚወጣ አመልክተዋል፡፡

እስክንድርና ርዕዮት የተመረጡት ፓርላማው ባወጣው መስፈርት መሠረት የሚያደርጉት ትግል የሃገራቸው ዴሞክራሲ፣ ነፃነትና ፍትህ የለው አስተዋዖ ተመዝኖ መሆኑንም ሚስ ጎመሽ ገልፀዋል፡፡

እስክንድር ነጋ

“እነዚህ ሰዎች እውነተኛ የሰብዓዊ መብቶች ታጋዮች ናቸው – ያሉት አና ጎመሽ ሁለቱ የኅሊና እሥረኞች ብቻ ሣይሆኑ በኢትዮጵያና በመላ አፍሪካም ለነፃነት፣ ለዴሞክራሲ፣ ለሕግ የበላይነት ለሚታገሉ ሁሉም ደወል ወይም መታያ ናቸው” ብለዋል፡፡

የያዝነው የአውሮፓ ዓመት የሃሣብ ነፃነት የሳኻሮቭ ሽልማት ዕጩዎች ስሞች ለውጭ ጉዳዮች እና የልማት ኮሚቴዎቹ ጥምር ስብሰባ መቅረባቸውን የአውሮፓ ፓርላማ ያስታወቀው ከትናንት በስተያ ሰኞ ነበር፡፡

በፓርላማው መግለጫ መሠረት ፓኪስታናዊቷ ማላላ ዩሳፍዛይ፣ አሜሪካዊው ኤድዋርድ ስኖውደን፣ ኢትዮጵያዊያኑ ርዕዮት ዓለሙ እና እስክንድር ነጋ፣ ቤላሩሲያዊያኑ አሌስ ቢያላትስኪ፣ ኤድዋርድ ላባዉ እና ማኮላ ስታትኬቪች በመላ የሃገሪቱ የፖለቲካ እሥረኞች ስም፣ ሩሲያዊው ሚኻይል ኾርዶቭስኪ፣ የቱርኩ “የቆመ ሰው” በሚል መጠሪያ የተጀመረው በቱርክ መንግሥቱ ላይ አፍጣጭ የታክሲም አደባባይ ተቃዋሚዎች ንቅናቄ የመጀመሪያው ተሰላፊ ኤርዶም ግዩንድዩዝ፣ የሲኤንኤን ቴሌቪዥን አውታር “ፍሪደም ፕሮጀክት (የነፃነት ፕሮጀክት)፡- ዘመነኛውን ባርነት ማብቃት” የሚባለው ፕሮግራም ናቸው፡፡

Source VOA

Ethiopian MiG 23
Previous Story

4 የአየር ኃይል አብራሪዎችና አስተማሪዎች ግንቦት 7ን ተቀላቀሉ

sept 19
Next Story

አንድነት መስከረም 19 በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ግማሽ ሚሊዮን ሕዝብ ይወጣል አለ – መኢአድም በሰልፉ ላይ ንቁ ተሳትፎ አደርጋለሁ ብሏል

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop