Hiber Radio: በኢትዮ-ኬኒያ ድንበር አዲስ ግጭት ተቀስቅሶ ከሃያ በላይ ሕይወት ጠፋ

/

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
<<...የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባሎችና አመራሮች ቁጥራቸው ከመቶ በላይ ነው። የመንግስት ሰልፍ ካለቀ በሁዋላ የተወሰኑት ተለቀዋል።በታሰሩበት ወቅት ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ተደብድበዋል፣ ሴቶቹ ሳይቀር ቱቦ ውስት አስገብተው ጭቃ ላይ አድርገው ደብድበዋቸዋል።ሞራላቸውን ለመንካት ለመናገር የሚቀፍ ስድብ ሰድበዋቸዋል። በደማችን ያመጣነውን ስልጣን ልትነጥቁ ነው ብለዋቸዋል።ለሰማያዊ የሰልፉ አለመካሄድና የነሱ ጭቃኔ መጋለጥ ድል ነው...>>

አቶ ከባዱ በላቸው የሰማያዊ ፓርቲ የሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ቻፕተር የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ

<<…የመንግስት ሀይማኖቶችን መቆጣጠር ፍላጎት ዛሬ የመጣ አይደለም። ባለፉት ሃያ ዓመታት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የራሱን ጳጳስ ከአንድ አካባቢ እየሾመ አሳይቷል። ስልጣን ሲይዙ መጀመሪያ የመቱት የቤተ ክርስቲያኑዋን ነው።…ሙስሊሙና ክርስቲያኑ አብሮ የኖረ ነው። መንግስት ይለወጣል ከዚህ ስርዓት ጋር ያሉ የሙስሊሙ መሪዎች እንዳይሳሳቱና የገዛ ወገናቸውን በማጥቃት እንዳይሰለፉ ፤መሳሪያ እንዳይሆኑ …>>
አባ ገብረስላሴ ጥበቡ በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ ሀላፊ ሰሞኑን በቬጋስ ያደረጉትን የአንድነት ጉባኤ መሰረት አድርገን ካደረግንላቸው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡ)

(ሌሎችም ቃለ መጠይቆች አሉን)

ስለ ሶሪያ ወቅታዊ ሁኔታ ልዩ ዘገባ ይዘናል..

ዜናዎቻችን

– ከታሰሩት ከመቶ በላይ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ጥቂቶቹ ተደብድበው ተለቀቁ

– መንግስት አሸባሪነትን አወግዛለሁ ብሎ የጠራው ሰልፍ በውጥረት ተጠናቀቀ

– ለጥበቃ ታንክ ጭምር ማሰለፉ የስርዓቱን ፍርሓት ያሳያል ተብሏል

– ከሰልፉ ላይ የታሰሩት ሙስሊሞች አልተለቀቁም

– በኩዌት ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሳንባ በሽተኛ ዜጎቹ ተጨናንቋል መባሉ ባለስልጣናቱን አስቆጣ

– በኢትዮ-ኬኒያ ድንበር አዲስ ግጭት ተቀስቅሶ ከሃያ በላይ ሕይወት ጠፋ

– ኬኒያ የአጸፋ እርምጃ እወስዳለሁ ብላለች

– አንድነት ፓርቲ በኢትዮጵያ ለውጥ ለማምጣት የሚደረገውን ትግል ዲያስፖራው በተግባር እንዲደግፍ ጥሪ አቀረበ

– ጆርጅ ዚመርማን የ17 ዓመቱን ትራይቮን ማርቲንን የገደለበትን ሽጉጥ ፋብሪካና መሳሪያ መሸጫ መጎብኘቱ ቅሬታ ፈጠረ

ሌሎችም ዜናዎች አሉን

ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio: በመስቀል አደባባይ ለተጠራው የአዳር የተቃውሞ ሰልፍ የአደባባይ ቅስቀሳ ይጀመራል፤ ሁበር በኔቫዳ ታገደ
Share