ሸንጎ “ዓባይን መገደብማ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሕልም ነው!” ሲል መግለጫ አወጣ

የሸንጎ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደወረደ ይኸው፦
ኅምሌ ፭ ቀን ፳፻፭
July 12, 2013
በስተሰሞኑ ዓባይን አስመልክቶ ህወሓት/ኢህአዴግ በተለመደ ፕሮፖጋንዳው የራሱን ‘አገር ወዳድ ሚና’ በማጉላት ተቃዋሚውን አኮስሶ ለማሳየት የሚያደርገው ጥረት እየተንፀባረቀ ነው። በዓባይ ግድብ ዙሪያም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች የህወሓት/ኢህአዴግ የመገናኛ ብዙሃን መሣሪያዎችና ተባባሪዎቻቸው የሚያናፍሱትን ፕሮፖጋንዳ ሕዝባችን ማዳመጥ ካቆመ ሰንብቷል። ይሁንና በዓባይና በግድቡ ጥያቄ ላይ ለወዳጅም ሆነ ለጠላት ሸንጎው አቋሙን ግልጽ ማድረጉ ደግሞ ተገቢ ነው። ስለዚህ በመጀመሪያ ሸንጎው በግድቡ መሠራት ላይ ያለውን አቋም (ህወሓት/ኢህአዴግም የዓባይ ግድብን ራዕይ ብቸኛ አፍላቂና ባለቤት ነኝ ባይነትና በዚህ ጉዳይ ዙሪያ በተቃዋሚው ላይ የሚያካሂደው አሉታዊ ቅስቀሳ በተመለከተ እውነታውን ሲያመላክት) ቀጥሎም ሀገራችን ኢትዮጵያ ወንዙን የመጠቀም መብቷን በተመለከተ ግብፅ በሰነዘረችው ማስፈራሪያ ላይ ሸንጎ ያለውን አቋም ያቀርባል።

(ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ)

ተጨማሪ ያንብቡ:  "ጠላት አለኝ ከሚለው የደጀን ኃይሉ እየራቀ በመጣ ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ወደ ወጥመዱ እየገባ ነው"፦ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ
Share