Hiber Radio: ኢትዮጵያ የአሰብ እና የምጽዋ ወደብን ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ማጓጓዣ እንድትጠቀም ጥሪ ቀረበላት፣ በኦጋዴን ውስጥ በኢሕአዲግ፣ በቻይና እና በጅቡቲ መካከል የተፈረመው ግዙፍ የነዳጅ ፕሮጀክት ከአካባቢው ተቆርቋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመውና ሌሎችም

/

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ መጋቢት 4 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…አሁን መንግስት የያዘው የሰራውን ሰርቶ መልሶ ስህተቱ ይሻሻላል የሚል በተለይ ፕሬዝዳንት ኦባማ መጥተው ከሄዱ በሁዋላ የያዙት ፈሊጥ ነው። አሁን እግዜርም ቢመጣ ሕዝቡ ኢህአዴግን አያምንም። በኦሮሚያ የተነሳውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ችግሩን ለመፍታት ከፈለጉ ገዳዮች ለፍርድ ይቅረቡ፣የታሰሩት ይፈቱ ያ ካልሆነ ይሄን ቀልድ አቁሞ ወደ እውነተኛ ብሄራዊ እርቅ መምጣት ያስፈልጋል…እዚህ አገር ውስጥ ምርጫ ቦርድ ዘጠና ምናምን ፓርቲዎች አሉ ይላል ያው ከታወቁት ጥቂት ተቃዋሚዎች በስተቀር ብዙዎቹ የመንግስት ቅልቦች ናቸው ከእነዚህ ይልቅ ወሳኝ መፍትሄ ማምጣት የሚችሉት እውነተኞቹ ተቃዋሚዎች ከኢህአፓና መኢሶን ጀምሮ ባለፉት አርባ ዓመታት ያላለፉት ፈተና ተባብሮ መቆም ላይ ነው።ዛሬም…>

ዶ/ር መረራ ጉዲና የኦፌኮ ሊቀመንበር በአቶ ሀይለማሪያም በኦሮሚያ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ለፓርላማ ላቀረቡት አስተያየት ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…ስርዓቱ የሚፈልገው ተነጣጥለን ቆመን ለመምታት ነው። ያ አሁን እየተሳካለት አይመስለኝም። በአገር ውስጥም በውጭም ኢትዮጵያውያን በጋራ አንድ ላይ እየቆሙ ነው። በሲያትል በአገር ቤት በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የተወሰደውን ግፍ በመቃወም የተጠራው ሰልፍ ላይ ኢትዮጵያውያን በአንድ መቆማችን በአንድ ላይ መጮሃችን ነው የታየው እኔም በወቅቱ ያደረኩት ንግግር ይሄንን ስርጫት ተነጣጥለን ሳይሆን በአንድ ላይ እንድንጥለው በአንድ ላይ እንነሳ የሚል ጥሪ ነው ።ጥሪውን …እኛ ያደረግነው በአንድ ላይ ሁላችንም ተወያይተን በጋራ ድምጻችንን ለማሰማት ነበር። ያን አድርገናል ትብብራችን በአንድ ላይ መቆማችን በዚህ አያበቃም ሕዝባችንን እየገደለ እያጠፋ ያለውን ስርዓት በጋራ መጣል ያስፈልጋል …>>

አክቲቪስትና የኢትዮጵያ የድንበር ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል ሙሉነህ ዮሐንስ በሲያትል ባለፈው አርብ በአገር ቤት በኦሮሞ ወገኖቻችን እና በሌሎቹም ላይ የሚደረገውን ግድያ በመቃወም የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ያደረገውን ንግግር መሰረት አድርገን ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ ( ሙሉውን ያዳምጡት)

<…በሙርሲ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው አስነዋሪ አያያዝ፣ግድያ፣አፈና ላይ ሕዝቡ ከዳር እስከዳር ተቃውሞውን በልዩ ልዩ መንገድ መግለጹ አስደሳች ነው።እነዚህ ሰዎች በሁሉም ቦታዎች ለሚፈጹሙት ግፍ ግድያ ተጠያቂ መሆን አለባቸው። ይህን ለማድረግ ተባብረን ጠንካራ ስራ መስራት አለብን…የኢህአዴግ ኤምባሲ አምባሳደር ግርማ ብሩ ወረቀት ጽፎ፣የጉዞ ይለፍ አዘጋጅቶ ከዚህ አሜሪካ ከታሰሩበት ወደ አገር ቤት እንዲገቡ ያደረጋቸውን ዘጠኙን ኢትዮጵአውያን ልንደርስላቸው አልቻልንም።እናዝናለን ግን አሁን የቀሩ አራት አሉ እነሱንም ሆነ ወደፊት ሌሎቹ እንዳይላኩ ማድረግ አለብን የጋራ ስራ አለ አንን ጀምረናል ሁሉም የራሱን አስተዋጽዎ ማድረግ አለበት…>

አቶኦባንግ ሜቶ የትብብር ለአዲሲቱ ኢትዮጵአ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር ከአሜሪካ የህወሃት ኤምባሲ ጽፎ ወደ አገር ቤት ስለወሰዳቸው ስደተኞችና በሙርሲዎች ላይ የስኳር ልማት በሚል ስለሚደርሰው የሰብኣዊ መብት ጥሰት ተጠይቆ ከሰተው ምላሽ(ሙሉውን ያድምጡ)

ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግስትን በአለማ ቀፍ የፍትህ አደባባይ የረታቸው እና ትምህርት የሰጠችው የወሲብ ተጠቂዋ ወይንሸት ዘበነ ሰሞነኛ ውሎ ሲዳሰስ ( ልዩ ጥንቅር) ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ኢትዮጵያ የአሰብ እና የ ምጽዋ ወደብን ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ማጓጓዣ እንድትጠቀም ጥሪ ቀረበላት

ዶ/ር መረራ ጉዲና ኢህአዴግ የቃላት ጨዋታውን ትቶ በኦሮሚያ የሕዝቡን ሰላማዊ ጥያቄ ተከትሎ የገደሉትን ለፍርድ እንዲያቀርብ የታሰሩትን እንዲፈታጠየቁ

ተቃዋሚዎች ተባብረው መቆም አለባቸው ወሳኝ ወቅት መሆኑን ገለጹ

በኦሮሚያ ተቃውሞው ቀጥሏል በመላው ኣለም በሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች የአገዛዙ አፈና ላይ ጠንካራ ተቃውሞ ቀረበ

በኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ላይ የሚማቅቀው “የሙስሊሞች ጉዳይ” መጽሄት አዘጋጅ የእስራት ቅጣት ተበየነበት

በመርካቶ በርካታ ሱቆች ሕገ ወጥ ሞባይልና ዕቃ አስገብታችሁዋል በሚል በዘመቻ ታሸጉ

ሶማሊያ ውስጥ ስልጠና ወስደዋል የተባሉ በርካታ ሰዎች ሰሞኑን በጸረ-ሽብሩ ህግ ሽፋን አ/አ ውስጥ የከባድ ቅጣት ሰለባዎች ሆኑ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከአሶሳ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዝ አውቶቡስ ተገልብጦ 6 ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ

በኦጋዴን ውስጥ በኢሕአዲግ፣ በቻይና እና በጅቡቲ መካከል የተፈረመው ግዙፍ የነዳጅ ፕሮጀክት ከአካባቢው ተቆርቋሪዎች ዘንድ ከፈተኛ ተቃውሞ ገጠመው

“የቻይና እና ጅቡቲ መንግስታት እጆቻቸውን ከኦጋዴን ሕዝብ ሃብት ላይ ባሰቸኳይ ያንሱ”ተቆርቋሪ ድርጅቶች

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Share