Sport: “ራሴን የምመለከተው እንደ ቼልሲ አሰልጣኝ ብቻ አይደለም፤ ክለቡን ከልቤ እወደዋለሁ” ሞሪንሆ

June 28, 2013

ጆዜ ሞውሪንሆ ወደስታምፎርድ ብሪጅ ከተመለሱ በኋላ ከቼልሲ ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ ይህን ይመስላል፡፡
ጥያቄ፡- በመመለስህ ደስ ብሎናል፡፡ ደህና ቆየህ?
መልስ፡- እኔም ተደስቻለሁ፡፡ ስሜቴ ገደቡን እንዳያልፍ ልቆጣጠረው ሞክሬያለሁ፡፡ ሆኖም እጅግ መደሰቴ እውነት ነው፡፡
ጥያቄ፡- ውሳኔው ምን ያህል ከባድ ነበር? ወደ ቀድሞ ክለብ መመለስ ብዙም ያልተለመደ…
መልስ፡- በጣም ቀላል ውሳኔ ነበር፡፡ ባለቤቱን አገኘኋቸው፡፡ በአምስት ደቂቃ ውስጥ ጥቂት ቀጥተኛ ጥያቄዎችን ተለዋውጠን በቶሎ ወሰንን፡፡ ወደ ቼልሲ እንድመለስ ይፈልግ እንደሆነ ጠየቅኩት፡፡ እርሱም አንተስ መመለስ ትፈልጋለህ? ብሎ ጠየቀኝ፡፡ በሁለት ደቂቃዎች ውስጥ ወሰንን፡፡
ጥያቄ፡- ቼልሲን ስትሰናበት በሌሎች ቦታዎች የምትፈልገውን አድርገሀል፡፡ ቼልሲም እንደዚሁ አንተ በጀርከው ላይ ቀጥሎ ውጤታማ…?
መልስ፡- በሴፕቴምበር 2007 ስታምፎርድ ብሪጅን ስለቅ አጋጣሚው ከባድ ነበር፡፡ ምክንያቱም እዚህ ሁሉንም ነገር ከልቤ አፈቅር ነበር፡፡ ከክለቡ ጋር የነበረኝ ጥምረትም የጠነከረ ነው፡፡ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ሁኔታው ለክለቡም አስቸጋሪ ነበር፡፡ ሆኖም ስሜታዊ የሆነውን ክስተት ወደ ጎን ካደረግን የተቀረው ነገር መልካም ነበር፡፡ ምክንያቱም ከዚያ በኋላ በአሰልጣኝነት ህይወቴ የተመኘኋቸውን ነገሮች አግኝቻለሁ፡፡ ከባዱን እና በየሳምንቱ ትኩረት የሚጠይቀውን የሊግ ውድድር በእንግሊዝ፣ በስፔን እና ጣልያን ማሸነፍ እፈልግ ነበር፡፡ ተሳክቶልኛል፡፡ በሶስቱም ሀገሮች ሁሉንም ዋንጫዎች አግኝቻለሁ፡፡ በተጨማሪም ሁለተኛውን የቻምፒየንስ ሊግ ክብር አሸንፌያለሁ፡፡
በሌሎች ሀገሮች መስራቴ አስደስቶኛል፡፡ የተለያዩ ሀገሮችን የእግርኳስ ባህል እንዳውቅም አድርጎኛል፡፡ ያሳለፍኩት ሁሉ ሁልጊዜ ከዘመኑ ጋር እየተለወጠ እንደሚሄድ ለማወቅ የእግርኳስ አሰልጣኝ በጣም ጠቅሞኛል፡፡ ቼልሲም ከዚያ በኋላ ትላልቅ ዋንጫዎች አግኝቷል፡፡ አሁን ሁለታችን በድጋሚ ተገናኝተናል፡፡ በጋራ የተሻለ አጋጣሚ ለመፍጠር በድጋሚ ተዋህደናል፡፡ በድጋሚ ለመዋሀድ እና ደስተኛ እንዲሁም ስኬታማ ለመሆን ተዘጋጅተናል፡፡
ጥያቄ፡- አሁን እቅድህ ምንድነው?
መልስ፡- እቅዴ ሁልጊዜም ተመሳሳይ ነው፡፡ ክለቡን በትልቅ ደረጃ እንዲደላደል ማድረግ እፈልጋለሁ፡፡ በ2007 ቼልሲን ከለቀቅኩ በኋላ በተለያዩ አጋጣሚዎች ስለክለቡ እናገር ነበር፡፡ በተለይ በግል ከሰዎች ጋር ብዙ ተነጋግሬያለሁ፡፡ በ2004 ለቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት ወደ አሜሪካ የሄድንበትን ወቅት አስታውሳለሁ፡፡ በጊዜው ከተመልካች ክፍት በሆነ ቦታ ዝግጅት እያደረግን ሲመለከቱን የነበሩት ግን ሁለት ህፃናት ብቻ ነበሩ፡፡ ማንም ሰው አይከታተለንም ነበር፡፡ ሁሉም ነገር ገና ነበር፡፡ ለሮማን የመጀመሪያቸው ቢሆንም ሁለተኛው የውድድር ዘመናቸው ለቼልሲ ገና መነሻው የነበረ ይመስለኛል፡፡ ከዚያ በኋላ ቼልሲ ፕሪሚየር ሊግ ማሸነፍ ጀመረ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሁለተኛ ጊዜ እያለ ቀጠለ፡፡ ከዚያ በኋላ ደግመን ወደ አሜሪካ ስንሄድ የገጠመን ድባብ የክለቡ ሁሉ ነገር እንደተለወጠ ጠቋሚ ነበር፡፡
ጥያቄ፡- ለክለቡ በታሪኩ ትልቁ አጋጣሚ ቻምፒየንስ ሊግን ያሸነፈበት ይመስለኛል፡፡ አሁን ቼልሲ ይበልጥ ገዝፏል፡፡ በዙሪያው ያሉ ደጋፊዎቹም በርክተዋል…
መልስ፡- እኔ አልተወጥኩም፡፡ በተክለ ሰውነቴ ያው ነኝ፡፡ ሆኖም በየቀኑ ስለራስህ ማሰብ አለብህ፡፡ ስለለውጥ ማሰብ ይኖርብሃል፡፡ ተፈጥሮዬ አልተለወጠም፡፡ ሆኖም አሁን ይበልጥ በስያለሁ፡፡ የተለያዩ ብልሃቶችንም ተምሬያለሁ፡፡ ፈተናዎቼን እንዴት መጋፈጥ እንዳለብኝ ተገንዝቤያለሁ፡፡ አሁን በክለቡ ለመስራት እና ለረጅም ጊዜ ለመቆየትም ዝግጁ ነኝ፡፡
ጥያቄ፡- በተለምዶ በአንድ ክለብ ከሶስት ዓመት በላይ ቆይተህ አታውቅም፡፡ አሁን ከዚህ በላይ ጊዜ ቆይቼ ቡድኑን እገነባለሁ ማለትህ ነው?
መልስ፡- ተስፋ የማደርገው እንደዚያ ነው፡፡ የአሁኑን የቡድኑን ስብስብ ስትመለከት አስፈላጊው ነገር ተሟልቷል፡፡ ከቀድሞው ጋር ስታነፃፅረው በአሁኑ ቡድን ያሉት የእኔ ጊዜ ተጨዋቾች አራት ወይም አምስት ናቸው፡፡ ይህ ለክለቡም ሆነ ለቡድኑ ሚዛን ጠቃሚ ነው፡፡ ሆኖም በጣም ባለተሰጥኦ የሆኑ ወጣቶች በብዛት እንደመኖራቸው መደላደል እና ወደ እግርኳስ ዘመናቸው ከፍታ መጓዝ አለባቸው፡፡ የተረጋጋ ሁኔታ ላይ ለመገኘት መስራት አለባቸው፡፡ እነርሱን ለማደላደል የሚሰራው ስራ በእነርሱ፣ በእኔ፣ በክለቡ ባለቤት እና በራሱ በክለቡ መካከል መጠናከር ይኖርበታል፡፡ ምን መስራት እንዳለብን እና እንዴት መስራት እንዳለብን ግራ መጋባት ወይም ጥርጣሬ አያስፈልግም፡፡ እኔ በግሌ ቡድኑን መርዳት እና ተጨዋቾቹን ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ እንደምችል እርግጠኛ ነኝ፡፡ ራሴን የምመለከተው እንደ ቼልሲ አሰልጣኝ ብቻ አይደለም፡፡ ምክንያቱም አፈቅረው ወደነበር ክለብ ስሄድ ያሁኑ የመጀመሪያዬ ነው፡፡ ክለቡን ከልቤ እወደዋለሁ፡፡ ማሊያውን እና አርማውን የምለብሰው ከልቤ ነው፡፡ ለዚህ ክለብ የምሰስተው ነገር የለኝም፡፡ የክለቡ አፍቃሪ ሆኜ በተጨማሪ ደግሞ አሰልጣኝ ስሆን ይህ በህይወቴ የተሰማኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ ሆኖም ስሜቱ ግሩም ነው፡፡
ጥያቄ፡- በደጋፊዎቹ ዘንድ ከወዲሁ ተወዳጅ ነህ?
መልስ፡- አዎን! እንደሚወዱኝ አውቃለሁ፡፡ በቼልሲ ለሰዎች ታማኝ የመሆን አኩሪ ባህል መኖሩን አውቃለሁ፡፡ የቼልሲን ጨዋታ በቴሌቪዥን ስመለከት ለምሳሌ በጨርቅ ላይ የተፃፈ ዲዲዬ ድሮግባ የሚል ፅሑፍ አነባለሁ፡፡ ይህ ድንቅ ነገር ነው፡፡ ቼልሲንም ልዩ ክለብ ያደርገዋል፡፡
ደጋፊዎቹ ለእኔ የተለየ ስሜት እንዳላቸው አውቃለሁ፡፡ የኢንተር አሰልጣኝ ሆኜ ቼልሲን ስገጥም ስሜቱ ከባድ ነበር፡፡ ተመልካቹም ለእኔ እንደዚያ አይነት ስሜት ውስጥ ነበር፡፡ ምክንያቱም እኔ የእነርሱ ነኝ፡፡ እነርሱም የእኔ ናቸው፡፡ እንደማስበው ተፈጥሮዬን ያውቁታል፡፡ እዚህ ቀድሞ በሰራሁት መልካም ነገር ላይ እንደማላንቀላፋ ይረዳሉ፡፡ የተለየ ቀረቤታ አለን፡፡ በድጋሚ ወደ ብሪጅ ስገባ ስሜን እያነሱ ይዘምሩልኝ ይሆናል፡፡ ሆኖም እኔ ፕሮፌሽናል ነኝ፡፡ ስራዬን ከዜሮ እጀምራለሁ፡፡ ጠንክሬ መስራት እና ከቀድሞው ቡድኔ የተለየ ቡድን መገንባት አለብኝ፡፡ ያለኝን ሁሉ ለክለቡ፣ ለደጋፊዎቹ እና ለባለቤቱ መስጠት እፈልጋለሁ፡፡ ቀደም ሲል እዚህ ሻምፒዮን ነበርኩ፡፡ ራሴ ላይ ይህንን ጫና ፈጥሬ እንደቀድሞው እንዲደሰቱ ማድረግ እሻለሁ፡፡
ጥያቄ፡- ለከርሞ ሶስቱ የፕሪሚየር ሊጉ ትልልቅ ክለቦች በአዳዲስ አሰልጣኞች ይቀርባሉ፡፡ በጣም አስደሳች ጊዜ…
መልስ፡- ፕሪሚየር ሊጉ ሁል ጊዜም ፕሪሚየር ሊግ ነው፡፡ ዘንድሮ በቻምፒየንስ ሊግ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በቶሎ ተሰናብተዋል፡፡ ቻምፒየንስ ሊግ ደግሞ እንደ ዓለም እግርኳስ ቴርሞ ሜትር ይታያል፡፡ ሰዎች ፕሪሚየር ሊጉ ከሌሎች ሀገሮች አንፃር በደረጃው መውረዱን ይናገራሉ፡፡ በዚህ አላምንም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ያለተጨባጭ ምክንያት የሚፈጠሩ ነገሮች ይኖራሉ፡፡ አሁንም ፕሪሚየር ሊግ ድንቅ ሊግ ነው፡፡ አሁን ምናልባትም አምስት ወይም ስድስት በጣም ጠንካራ ክለቦች አሉ፡፡ በ2004 ተፎካካሪዎቹ እኛ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ እና አርሰናል ብቻ ነበርን፡፡ በተረፈ ከሌሎቹ ክለቦች ጋር ሰፊ ልዩነት ነበር፡፡ አሁን ግን በተመሳሳይ እቅድ የሚነሱ አምስት ወይም ስድስት ክለቦች ይኖራሉ፡፡ ለቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ደረጃ ይዞ መጨረስ እንኳን ፈተና ነው፡፡ ስለዚህ ሊጉን ማሸነፍ ይበልጥ አስቸጋሪ ነው፡፡ ሆኖም በድጋሚ ውድድሩን እንደማሸንፍ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ጥያቄ፡- የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ዋነኛ ትኩረትህ ነው?
መልስ፡- ቡድኑን ማሻሻል ይኖርብናል፡፡ ቡድኑን ስለማሻሻል ስናገር ብዙ ሰዎች የሚያስቡት ቼልሲ ለዝውውር ሚሊዮች ፓውንዶችን እንደሚያፈስስ ነው፡፡ እኔ ቡድኑን ማሻሻል ስል የምናገረው በስራዬ ስለማሻሻል ነው፡፡ ስራዬ ተጨዋቾቹን እና ብሎም ቡድኑን ማሻሻል መቻል አለበት፡፡ ይህንን ስናደርግ ምናልባት ሁለት ተጨዋቾች መጨመር ከቻልን ጥሩ ይሆናል፡፡ ተጨዋቾቹን እና ቡድኑን ማሻሻል ዋናው አላማዬ ነው፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት በፕሪሚየር ሊጉ መቸገራችን ታይቷል፡፡ ቻምፒየንስ ሊጉን ባታሸንፉ ኖሮ በውድድሩ አትሳተፉም ነበር፡፡ ለከርሞ በቻምፒየንስ ሊጉ ተሳታፊ ለመሆን ዘንድሮም ክለቡ መታገል ነበረበት፡፡ ይህንን ቡድን ማሻሻል አለብን፡፡ የክለቡ ዋና አላማም ይህ ነው፡፡ በግለሰብ ደረጃ መሻሻል፣ በቡድን መሻሻል፣ የቡድኑን አደረጃጀት ማሻሻል እና ቀጣይ ጨዋታዎችን ለማሸነፍ መጣር፡፡ ቀጣዩ ጨዋታ የትኛው ነው? ፕሪሚየር ሊግ? አዎን ፕሪሚየር ሊጉን ለማሸነፍ መጓዝ አለብን፡፡ ቀጣዩ ጨዋታ የኤፍኤ ካፕ ከሆነም ኤፍኤ ካፕን ማሸነፍ አለብን፡፡ ስለዚህ ዋና ትኩረቴ ይህ ነው ማለት አልችም፡፡ ትኩረቴ ጠንክሮ መስራት እንደ ፕሮፌሽናል መስራት እና ቡድኑን ማሻሻል ነው፡፡
ጥያቄ፡- ስለ ቡድኑ አጨዋወት ምን እያሰብክ ነው?
መልስ፡- አሁን የምፈልገው አብሬ መስራት ነው፡፡ ከቀድሞው ቡድኑ ሶስት፣ አራት ወይም አምስት ተጨዋቾች አሁንም መኖራቸው ደስተኛ ያደርገኛል፡፡ እነርሱ ሁልጊዜም የቼልሲ አካል ናቸው፡፡ ገና ለመሻሻል በቂ ጊዜ ያላቸው ወጣቶች መኖራቸው ያስደስተኛል፡፡ የአራት ዓመት ኮንትራት ፈርሜያለሁ፡፡ የ(ኤደን) ሀዛርድ፣ ኦስካር፣ ዴቪድ ሉዊዝ እና የሌሎቹን ዕድሜ ስመለከት ከእነርሱ ጋር በመስራቴ እደሰታለሁ፡፡ እነርሱም ከእኔ ጋር በመስራታቸው ይጠቀማሉ፡፡ በጋራ ከአሁን የተሻለ ቡድን እንዲኖረን እናደርጋለን፡፡
ጥያቄ፡- አብረውህ ሊሰሩ የሚመጡ ባልደረቦችህን ልትነግረን ትችላለህ?
መልስ፡- እንደምታውቁት ሩይ የእኔን አሰለጣጠን የሚያውቅ ቀኝ እጄ ነው፡፡ ከመጀመሪያ አንስቶ አብሮኝ ነበር፡፡ ሲልቪኖም እንደዚያው ነው፡፡ ጆዜ ሞራይስ አብሮኝ መስራት የጀመረው በኢንተር ሚላን እያለሁ አንድሬ ቪያስ ቦአስን ተክቶ ነው፡፡ ሞራይስ አሁን የሚሰራው በትክክል አንድሬ ይሰራው የነበረውን ነው፡፡ ከምልመላ፣ ከትንተና በተጨማሪ ከጀምስ ሜልበርን ጋር እጅ እና ጓንት በመሆን ይሰራሉ፡፡ የረጅም ጊዜ ጓደኛዬ ከመሆኑም በላይ በሳዑዲ አረቢያ፣ ዱባይ፣ ቱኒዚያ፣ ስዊድን እና ሞሮኮ አሰልጥኗል፡፡ በጣምም ልምድ አለው፡፡
ጥያቄ፡- እረፍት ያስፈልግሃል ብለን እናስብ?
መልስ፡- ይቅርታችሁን ልምምድ የምንጀምረው ነገ አይደለም፡፡ አንዳንድ ጊዜ በውድድር ዘመኑ መካከል ተጨዋቾቼ የተዳከሙ ሲመስለኝ የምነግራቸው ነገር አለ፡፡ ‹‹ድል ተአምር ያደርጋል›› እላቸዋለሁ፡፡ ስታሸንፍ፣ ስታሸንፍ፣ ስታሸንፍ አይደክህም፡፡ ለእኔ ድል ማድረግ ማለት ማሸነፍ ሳይሆን መጓዝ ነው፡፡ እኔ በመመለሴ ብቻ እየተደሰትኩ ነው፡፡ ተጫዋቾቹ እረፍት ያሻቸዋል፡፡ እኔ አያስፈልገኝም፡፡ እነርሱን እጠብቃቸዋለሁ›› ሲመጡ የተነቃቃ ሰው ይጠብቃቸዋል፡፡ እንደ ቀድሞ ነኝ፡፡ ከፀጉሬ መንጣት በስተቀር፡፡
ጥያቄ፡- እስያ ትሄዳላችሁ፣ ከዚያም ወደ አሜሪካ ታቀናላችሁ፡፡ ቀጥሎ ደግሞ ሱፐር ካፑ ይመጣል፡፡ ከፔፕ ጋርዲዮላ ጋር ትፋለማላችሁ፡፡ አስደሳች ጅማሮ ነው…
መልስ፡- እንደሱ አይደለም፡፡ ሞውሪንሆ ከጋርዲዮላ ሳይሆን ቼልሲ ከባየርን ነው፡፡ ሞውሪንሆ እዚህ ግጥሚያ ላይ ለመድረስ ምንም አልሰራም፡፡ ጋርዲዮላም ምንም አስተዋፅኦ አላደረገም፡፡ ሁሉንም የሰሩት ተጨዋቾቹ ናቸው፡፡ ስለዚህ ወደ ጨዋታው የምሄው ቡድኔን ለመርዳት ነው፡፡ ተጨዋቾቼ ዋንጫውን እንዲያነሱ ለማድረግ እሄዳለሁ፡፡ ሌላ ምንም ነገር የለም፡፡ ጨዋታው ለውድድር ዘመናችን ወሳኝ አይደለም፡፡ ባይሆን ለቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት መጓዝ እና ጠንክረን መስራት ውድድር ዘመን ዝግጅት መጓዝ እና ጠንክረን መስራት ይኖርብናል፡፡ ለክለቡ ራሳችንን መስጠት ያስፈልገናል፡፡ ወደ እስያ እና አሜሪካ የተለያዩ ቦታዎች መሄድ መልካም ነው፡፡ ሆኖም ጠንክረን መስራት አለብን፡፡
ጥያቄ፡- ከዘጠኝ ዓመት በፊት በቼልሲ ቴሌቪዥን የመጀመሪያ ቃለ ምልልስ ስታደርግ ወደ ካሜራው ዞረህ ጥራት ያለው ቡድን ለመስራት፣ ለማገልገል፣ ፍቅርን ለመፍጠር እና ስኬትን ለክለቡ ለማምጣት ቃል እገባለሁ ብለህ ነበር፡፡ ዛሬም ተመሳሳይ መልዕክት ታስተላልፋለህ?
መልስ፡- አዎን አሁንም መልዕክቴ ፍፁም ተመሳሳይ ነው፡፡ ሆኖም አሁን ከእናንተ እንደ አንዱ ነኝ ማለት እችላለሁ፡፡ ልዩነቱ ይህ ነው፡፡ በእግር ኳስ ህይወቴ እንዲህ አይነት ስሜት ኖሮኝ አያውቅም፡፡ በእግርኳስ ዘመን ከልቤ የወደድኳቸው ኢንተር ሚላን እና ቼልሲ ናቸው፡፡ የቼልሲ ግን የላቀ ነው፡፡ ቼልሲን በተቃራኒነት መግጠም እጅግ ይከብዳል፡፡ ሁለት ጊዜ ብቻ ስላደረግኩት መጥፎ አይደለም፡፡ ስለዚህ አሁንም እንደቀድሞው ቃል እገባለሁ፡፡ በ2004 ከገባሁት ቃል የአሁኑ ልዩነቱ አሁን ከእናንተ እንደ አንዱ መሆኔ ነው፡፡ ምክንያቱም ለዝውውር የሚቀርበውን ሂሳብ እጥፍ አድርገው ያቀርባሉ፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ አዲስ ህግ ስለወጣ የሚፈጠረውን እንመለከታለን፡፡ ለምሳሌ አዲሱን የቴሌቪዝን ስርጭት ገቢን በመጠቀም ከአምና በላይ ለደመወዝ ማውጣት አይችሉም፡፡ ይህን ማድረግ የሚችሉት ከኮሜርሺያል ገቢና ሌሎች ምንጮችን በመጠቀም ይሆናል፡፡
ቡድኖች በእነዚህ ገደቦች ለመወሰን ይገደዳሉ፡፡ አሁን ላይ ሆኜ የክረምቱ ዝውውር ምን ሊመስል እንደሚችል መገመት አልችልም፡፡ መናገር የምችለው ግን በሚቀጥለው የውድድር ዘመን የበለጠ ጠንካራ የሆነ ቡድን ይዘን እንደምንቀርብ ነው፡፡ ወጣት ተጨዋቾችንም ዕድገት ያሳያሉ፡፡ ይህን በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ተመልክተናል፡፡ ቡድናችን ጥቂት አዳዲስ ተጨዋቾች ያሉት ሲሆን የእንግሊዝ እግር ኳስን መላመድ ይኖርባቸዋል፡፡ በክረምቱም አዳዲስ ፈራሚዎች ይኖራሉ፡፡ በእነዚህ ጉዳዮች የተነሳ በቀጣይ ለዋንጫ የሚፎካከር ቡድን እንዳለን ይሰማኛል፡፡
ጥያቄ፡- የደመወዝ ፖሊሲውን ስላወጡት ባለሙያዎች፡-
መልስ፡- የደመወዝ ፖሊሲውን ቀርፀዋል አላልኩም፡፡ በዚህ ቦታ እኔና ቬንገር ትልቅ ልምድ አለን፡፡ የምንፈልጋቸውን ተጨዋቾች የሚወስኑት ቬንገር ናቸው፡፡ በዚህ በኩል የሚረዱን ሰዎችም አሉ፡፡
ጥያቄ፡- አንድ ደጋፊን ለስኪላቺ፣ ሻማክና ዢሩ በሳምንት 60 ሺ ፓውንድ መክፈል ወይስ ለጥሩ ፈራሚ ሳምንታዊ 180 ሺ ፓውንድ መክፈል ይሻላል? ብትሉት ድንቅ ተጨዋች አስፈርሞ ሳምንታዊ 180 ሺ ፓውንድ መክፈል የሚል ምርጫው ነው፡፡ እናንተም ለምን ይህን አታደርጉም?
መልስ፡- በተጨዋቾች ዙሪያ መግባት አልፈልግም፡፡ አሁንም ቀድሞ ወደ ተናገርኩት ነገር እመለሳለሁ፡፡
ጥያቄ፡- ግን እኮ ሳምንታዊ 60 ሺ ፓውንድ የሚከፈለው የዋናው ቡድን ተጨዋች ማግኘት ይከብዳል?
መልስ፡- የምታወጣውን ወጪ ከሜዳ ላይ ውጤት ጋር በማነፃፀር ልትለካው ትችላለህ፡፡ እኛ ይህን ስናደርግ በየዓመቱ ያስፈረምናቸው ተጨዋቾች ጥሩ አቋም አሳይተው እናገኛለን፡፡ በዝውውር በተደጋጋሚ ጊዜ ስኬታማ መሆን ግን ከባድ ነው፡፡ ተጨዋቾችን በአጋጣሚ አታስፈርምም፡፡ በምናስፈርማቸው ተጨዋቾች ብዙ ጊዜያት ትችት አሰተናግደናል፡፡ ይህን ተገቢ ትችት አድርጌ አላየውም፡፡ ውሳኔያችንን የምናስተላልፈው ለመሻሻል ነው፡፡ በየትኛወም መለኪያ በዝውውር ላይ መልካም ስራ እንደሰራን አስባለሁ፡፡
ጥያቄ፡- በዝውውር የበለጠ ገንዘብ ካወጣችሁ ልታመጡ የምትችሉትን ሰኬት አስቡ…
መልስ፡- የመጪውን ጊዜ ሳስብ ደስታ ይሰማኛል፡፡ ምክንያቱም ከፍተኛ ገንዘብ የማውጣት አቅማችን ይዳከማል ብዬ አላስብም፡፡ ትልቅ ስህተት ካልፈፀምን በሚቀጥሉት የውድድር ዘመናት የተሻሻለውን አርሰናል በእርግጠኝነት ትመለከቱታላችሁ፡፡ ይህን ለመፈፀም ደግሞ ለረጅም ጊዜ ድንቅ ስራ የሰሩትን አሰልጣኝ ይዘናል፡፡ ቬንገር በፋይናንሱ በኩል ከፍተኛ ድጋፍ ቢሰጣቸውም አሁንም ለወጣቶች እድል እንደሚሰጡ አምናለሁ፡፡ ይህ ግን ታላላቅ ባለተሰጥኦዎች አይፈልጉም ማለት አይደለም፡፡
ጥያቄ፡- በማንቸስተር ዩናይትድ ከሰር አሌክስ ፈርጉሰን በኋላ ምን ይከሰታል ብለው ያስባሉ? እንደቀድሞው በሃያልነታቸው መዝለቅ ይችላሉ?
መልስ፡- ማን ያውቃል? ማንቸስተር ዩናይትድ ድንቅ ክለብ ነው፡፡ ሊዳከሙ እንደሚችሉ የሚያስብ ይኖራል፡፡ እኛ ግን በሚቀጥለው የውድደር ዘመን ሁሉም የበለጠ ተፎካካሪ ሆኖ እንደሚቀርብ ስለምናስብ ተጠናክረን እንመጣለን፡፡ ክለባችን ግልፅነት የሰፈነበት ነው፡፡
ጥያቄ፡- በክረምቱ ምርጥ ተጨዋቾቻችሁ እንደማይለቁ እርግጠኞች ናችሁ?
መልስ፡- በተጠናቀቀው የውደድር ዘመን ጠቃሚ ተጨዋቾቻችንን የረጅም ጊዜ ኮንትራት አስፈርመናቸዋል፡፡ በዚህ ክረምት ብቻ ሳይሆን ለመጪው ጊዜም በኮንትራት ሁኔታ ላይ ጠንካራ ኃይል ይዘናል፡፡ በርካታ ተጨዋቾች በኮንትራት ሰለታሰሩ ጠንካራ የሆነበት ጊዜ ነው፡፡ ወሳኙ ነገር በምናስፈርማቸው ተጨዋቾች ላይ ትክክለኛ ውሳኔ ማስተላለፈ ነው፡፡ ጥያቄ፡- ባካሪ ሳኛ ይለቃል?
መልስ፡- በተጨዋቾች ሁኔታ ላይ ሀሳብ መስጠት አልፈልግም፡፡
ጥያቄ፡- በፋብሪጋዝ ላይ መልሶ የመግዛት አማራጭ ስለመኖሩ ያረጋግጡልኛል? መልሳቸሁ ለማስፈረም ፍላጎት አላችሁ?
መልስ፡- በዚሀ ጉዳይ ላይ መናገር አልፈልግም፡፡ በየትኛውም ተጨዋች ሆነ ጭምጭምታዎች ላይ መልስ መስጠት አልሻም፡፡
ጥያቄ፡- አሁን ‹‹ትክክለኛ›› ተጨዋቾችን ለማግኘት ከፍተኛ ፍላጎት አለ?
መልስ፡- ጥሩ ዕድል ተፈጥሮልናል፡፡ በዝውውር ጉዳዮች ላይ ውሳኔ የሚያስተላልፉ ሰዎች ቢኖሩም በእግርኳሱ በፈለገው መልኩ ሁኔታዎቸ እንደሚጓዙልህ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡
ጥያቄ፡- በሚቀጥለው የውድድር ዘመን የሊጉ ሻመፒዮን መሆን ትችላላችሁ?
መልስ፡- ይህን ለመናገር መሻሻል ይጠበቅብናል፡፡ ከክረምቱ ዝውውር በኋላ ሚዛናዊ ሃሳብ ሊኖረኝ ቢችልም ሊጉን ማሸነፍ እንደምንችል አስባለሁ፡፡ የሁላችንም ፍላጎትና አላማ ይኸው ነው፡፡
ጥያቄ፡- ስለ ቬንገር ቀጣይነት መልዕክቶ ግልፅ ነው፡፡ አሰልጣኙ፡- በክለቡ የሚኖራቸው ቆይታ እንደተጠናቀቀው የውድድር ዘመን አይነት ጉዞ ላይ የተንጠላጠለ ነው? 2013/14 ያለ ዋንጫ ቢጠናቀቅ ከቬንገር እና ከደጋፊዎች ፍላጎት የቱን ታስቀድማላችሁ?
መልስ፡- ስለሚቀጥለው የውድድር ዘመን በመላምት መናገር አልፈልግም፡፡ በአሁኑ ወቅት ትኩረታችን በ2013/14 ወደፊት እንድንራመድ መስራት ስላለብን ጉዳይ ነው፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ ቬንገርን ይዘናል፡፡ ደጋፊዎችን የሚያስደስት ነገር ለመስራት እየጣርን ነው፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ በቀጣዩ ዓመት ዋንጫ ለማንሳት የሚያስችለን ጠንካራ ቡድን ይዘን ለመቅረብ በዝግጀት ላይ ነን፡፡

Pen 4
Previous Story

የኃይል መቋረጥ እያሰከተለ ያለው ቀውስ

dereje habteweled
Next Story

ኢሳት – በደረጀ ሀብተወልድ (ጋዜጠኛ)

Latest from Blog

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት

የኢካን ዓላማ በኔዘርላንድ የሚኖረውን ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እና ኢትዮጵያውያንን ኮምዩኒቲይ የማሰባሰብ ሳይሆን የመከፋፋልና የማዳከም ተልኮን ያነገበ ነው።

አገር ! ለየአንድ ሠው ቋንቋው፣ ልማዱ፣ ባሕሉ፣ እምነቱ፣ አስተሳሰቡ፣ ወጉና በአጠቃላይ እሱነቱና ማንነቱ የሚከበርበት ብቸኛ ሥፍራ ነው። ኢትዮጵያውያንም በስደት በሚኖሩባቸው አገራት ሁሉ እነኝህን በስደት ያጧቸውን የግልና የጋራ ማንነቶቻቸውን በአንድ ላይ ሆነው ለመዘከር

ፋኖ ምሽጉን ደረመሰው ድል ተሰማ | ” ስልጣን እለቃለሁ ” ፕረዚዳንቷ | ህዴድ ድብቅ ስብሰባ በአዲስ አበባ | “ተመስገንን በመዳፌ ስር አስገብቼዋለሁ” አብይ

-966+9-የኦህዴድ ድብቅ ስብሰባ በአዲስ አበባ “ተመስገንን በመዳፌ ስር አስገብቼዋለሁ” አብይ – ስልኩ ተጠለፈ “እኛ የምን’ዘጋጀው ለፋኖ ሳይሆን ለኤር-ትራ ነው” አበባው|”በጊዜ ቦታ አዘጋጁልኝ” አረጋ

አንድ በኢኮኖሚና በሌሎች ነገሮች ወደ ኋላ የቀረች አገር አንድን ኃያል መንግስት በመተማመንና ጥገኛ በመሆን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ማምጣትና የተሟላ ነፃነትን መቀዳጀት ትችላለች ወይ?

ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ሰኔ 4፣ 2016 (ሰኔ 11፣ 2024)   በዚህ አርዕስት ላይ እንድጽፍ የገፋፋኝ ዋናው ምክንያት ሰሞኑኑ ዶ/ር ዮናስ ብሩ የቻይንንም ሆነ የቬትናምን በኢኮኖሚ ማደግ አስመልክቶ ሁለቱ አገሮች እዚህ ዐይነቱ የዕድገት ደረጃ ላይ ሊደርሱ የቻሉት ከአሜሪካ ጋር

ፋኖ አንድ ሌሊት አያሳድረንም” የአማራ ብልፅግናየኢሳያስ ግዙፍ ጦር ወደ ወልቃይት

ፋኖ አንድ ሌሊት አያሳድረንም” የአማራ ብልፅግናየኢሳያስ ግዙፍ ጦር ወደ ወልቃይት አብይና ዳንኤል ክብረት ጉድ አሰሙ-|ጀነራሉ በቁ*ጣ ተናገሩ-‘ህዝቡ ጉድ ሰራን’-|“ብልፅግናን ራ*ቁቱን አስቀርተነዋል”-|ታዳሚው ባለስልጣናቱን አፋጠጠ
Go toTop