Hiber Radio: ኢትዮጵያ መንግስቴን ለመገልበጥ የታጠቁ ሀይሎችን ወደ ግዛቴ ሰርገው እንዲገቡ እያደረገች ነው ስትል ኤርትራ ከሰሰች፣ኢትዮጵያ በያዘችው ያልተስተካከለ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ፖሊሲ የተባበሩት መንግስታትን የምዕተ ዓመቱን እቅድ ማሳካት እንደማትችል ተገለጸ፣አንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ በድንገት አረፈ፣በየመን የሚገኘው ጋዜጠኛ ግሩም ተጨማሪ የእስር ስጋት እንደተደቀነበት ገለጸ፣በግልገል ግቤ ሶስት ግንባታ ላይ ኢትዮጵያ ለቀረበባት ወቀሳ ጠንካራ ምልሽ ሰጠች እና ሌሎችም

/

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ መስከረም 23 ቀን 2008 ፕሮግራም

<… አንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌን ማጣት ለኢትዮጵያ ትልቅ ጉዳት ነው …ጋሽ ሙሉጌታ ትሁት፣አዳማጭ፣የማስታወስ ችሎታው የሚያስገርም ነው። ተንቀሳቃሽ ቤተ መጽሐፍት ማለት ይቻላል > የጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌን ድንገተኛ ሕልፈት ተከትሎ የቀድሞ የጦቢያ መጽሔትና ጋዜጣ አዘጋጅ አንተነህ መርድ ከህብር አዘጋጆች ጋር ባካሄደው ውይይት ከተናገረው (ሙሉውን ያዳምጡ)

<…ዕውቁ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ መምህርም ነበር ካስተማራቸው መካከል ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ይገኙበታል ፣ለኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ፈር ቀዳጅ ፣ ዲፕሎማት ጭምር ነበር። ለ18 ጊዜያት በዚህ ስርዓት ተከሷል ተገፍቶ ተሰዷል እስከ መጨረሻ ግን ለሙያው እና ለዕውነት ታማኝ እንደሆነ ያለፈ ታላቅ ሰው ነው..> በውይይቱ ላይ ስለ አንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ከተነሱ ጉዳዮች (ሙሉውይ ውይይት ያዳምጡ)

<…የተባበሩት መንግስታት የልማት ግቦችን ይሄ ስርዓት እያሳካ አይደለም። በኢትዮጵያ በአስከፊ ድህነት ውስጥ የሚኖረው ሕዝብ ቁጥር ጨምሯል፣ ንጹ ውሃ የሚያገኘው ጥቂት ነው። ከአፍሪካ ከፍተኛ ዕርዳታ የሚያገኝ ስርዓት የሰራቸውን ትንሽ ስራዎች ከተገኘው ገንዘብ ጋር አይመጥንም ። አገሪቱ ካለችበት አጣብቂኝ ለማውጣት የተስተካለ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ፖሊሲ የአረንጓዴ አብዩት ያስፈልጋታል ….>

ዶ/ር አክሎግ ቢራራ የዓለም ባንክ የቀድሞ አማካሪ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ(ክፍል አንድ)

<…የቀረበብኝ የሀሰት ክስ በስደተኞች ስም ገንዘብ ይሰበስባል፣ድብቅ ካሜራ አለው ለእስራኤልና ለሳውዲ ይሰልላል መረጃ ያስተላልፋል የሚል ነበር። እቅዱ ሕይወቴን አደጋ ውስጥ ለመክተት ጭምር ከዚህ በፊት በረዳሁት ግለሰብና ኤምባሲ በሚሰራ ሰው አማካይነት የተቀነባበረ ነበር…ዛሬም ሌላ የፈጠራ ክስ ቀርቦብኛል ሕይወቴ አደጋ ውስጥ ነው ሰላም ወዳለበት ወደ ማንኛውም የአፍሪካ አገርም ቢያሻግሩኝ እመርጣለሁ…> ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት ከየመን ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

የአሜሪካና የሩሲያ ፍጥጫ በሶሪያ ጉዳይ ቀጥላል፤ ሩሲያ አላሳድን ለማዳን አይሲስን ማጥፋት

አሜሪካ አይ.ሲስና አላሳድንም ማስወገድ ዕቅድ –የዓለም መገናኛ ብዙሃን ሰፊ መነጋገሪያ (ልዩ ጥንቅር)

አገራችን ኢትዮጵያን ከወራሪው የሶማሊያ ጦር ከታደጓት ባለታሪክ እና ብርቅዬ ጀግኖቿ መካከል አንዱ የሆነው ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ አጭር የሕይወት ታሪክ እና የጀግንነት ትውስታ (ልዩ ዘገባ የኮ/ል ባጫ ሁንዴን ሕልፈተ ሕይወት ተከትሎ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በኢትዮጵያ ያንጃበበው የድርቅ አደጋ ከ15 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን እንዳያዠጠቃ ተሰግቷል

የዓለም መሪዎች በድርቁ ላይ ፓሪስ ውስጥ ሊመክሩ ነው

በኢትዮጵያ የተስተካከለ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ስርዓት ስለሌለ የተመድ የምዕተ ዓመቱ ግብ እንዳልተሳካ ታዋቂው የቀድሞ የዓለም ባንክ የኢኮኖሚ አማካሪ ገለጹ

አናጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ኢትዮጵያ መንግስቴን ለመገልበጥ የታጠቁ ሀይሎች ወደ ግዛቴ እንዲገቡ አደረገች ስትል ኤርታራ ከሰሰች

የሱዳኑ ፕ/ት አልበሽር ከአቶ ሞላ አስግዶም ከአስመራ መኮብለል በሁዋላ የኤርትራ ባለስልጣንን ተቀበሉ

በደቡብ ሱዳን የሶስት ኤርትራውያን መገደል ቁጣ ቀሰቀሰ

ኢትዮጵያ በግልገል ጊቤ ሶስት ላይ ለቀረበባት ወቀሳ ጠንካራ ምላሽ ሰጠች

ተጨማሪ ያንብቡ:  ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ ከአል ቡርሃን ጋራ መሥራትን እንደሚመርጡ አስታወቁ

ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት ተጨማሪ የፈጠራ ክስ እንደቀረበበትና አደጋ ውስት እንዳለ ገለጸ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Share