የሕወሓት አስተዳደር የመከላከያ ሰራዊት ለአባይ ግድብ መስሪያ ገንዘብ አናዋጣም አሉ

የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት መከላከያ ሰራዊት ለአባይ ግድብ መስሪያ ገንዘብ እንዲያዋጡ ለቀረበላቸው ጥሪ እንዳልተቀበሉት የትህዴን ድምጽ ምንጮች ከመከላከያ ውስጥ ገለፁ::
Photo File
በምንጮቹ መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንደ አዲስ ለአባይ ግድብ መስሪያ የሚሆን በሚል ገንዘብ እንዲያዋጡ በአመራሮቻቸው ለቀረበላቸው ጥሪ አንቀበልም ማለታቸውን የገለፀው መረጃው ለቀረበው ጥሪ ሳይቀበሉት የቀሩበት ምክንያትም “ ባለፉት ጊዚያት በተደጋጋሚ የከፈልነውን ገንዘብ ቦንድ ይሰጣቸኋል ተብለን እስከ አሁን ድረስ ግን ሳይተገበር አንከፍልም” እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል::

መረጃው በማከል።- የሰራዊቱ ከፍተኛ አዛዦች በሰራዊቱ ውስጥ አጋጥሞ ያለውን ለአባይ ግድብ ገንዘብ አንከፍልም የማለቱ የመበታተን አደጋ። እንዴት አድርገን ለሰራዊቱ እናሳምነው በሚል በከባድ ውጥረት እንደሚገኙ የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል ሲል የትህዴን ድምጽ ዜናውን ቋጭቷል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢሕአፓ ወጣት ክንድ በክርሥትና እና በእሥልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ የሚደረገው አፈናና የመብት እረገጣ እንዲቆም ጠየቀ »
Share