Hiber Radio: አሜሪካ ሶማሊያ ለሚገኘው የኢሕአዴግ እና የጅቡቲ ጦር የመረጃና የስለላ ስልጠና እየሰጠች መሆኗ ታወቀ – ሕንድ ከኢትዮጵያና ከኤርትራ ማንን እንደምመርጥ ተቸግሬያለሁ አለች (ሌሎችም ዜናዎች አሉ)

/

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ ጳጉሜ 1 ቀን 2007 ፕሮግራም

<...ሌብነትና ሙስና የስርዓቱ ችግር ነው።ራሳቸው ጠ/ሚ/ሩ የመንግስት ሌባ የግል ሌባ ብለዋል። ችግሩ ማን ነው ማንን የሚያጋልጠው ነው... አሁን በጀመሩት መንገድ ወደ ሁዋላ እንጂ ወደፊት አይሄዱም ። አለመረጋጋቱማ አሁንም አለ ሚሊዮኖች የተከፉባት አገር አለመረጋጋት አለ። ያው ከሶማሊያ ይሻላል ለማለት ካልሆነ ኢትዮጵያ የተረጋጋች አገር አይደለችም።...> ዶ/ር መረራ ጉዲና የመድረክ ም/ሊቀመንበር በወቅቱ የስርዓቱ የ<ኪራይ> ሰብሳቢነት ፕሮፖጋንዳና ለአዲሱ ኣመት የተቃዋሚዎችን ሚና በተመለከተ አነጋግረናቸው ከሰጡን ቃለ ምልልስ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)

<...ከዚህ ወጥተህ አርፈህ የማትቀመጥ ከሆነ አንተን አስረን የሚዲያ ፍጆታ አናደርግም በማንኛውም ሰዓት እናስወግድሃለን ብለዋል። ሊአስሩኝም ሆነ ሊገሉኝ ይችላሉ።የጀመርኩትን ሰላማዊ ትግል ግን አላቆምም። መታገሉን እቀጥላለሁ...በፍርድ ቤት ቀደም ሲልና አሁን በመጨረሻም በሀሰት የመሰከሩብኝን ጨምሮ ሌሎችም ሆነው አሁን ባለሁበት ቤት አካባቢ ክትትል እያደረጉ ነው።እኔ ግን ...> አቶ ማሙሸት አማረ ሕጋዊው የመኢአድ ፕሬዝዳንት ከእስር ቤት መልስ ከሰጡን ቃለ ምልልስ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

በምንሸኘው 2007 ዓመት የተከናወኑና 21 ዋና ዋና ክንውኖች (የህብር አዘጋጆች ምልከታ)

በቬጋስ ባህታዊው የተገኙበት መንፈሳዊ የአደባባይ የጸሎትና የፈውስ ስርዓት አዘጋጆች አንዱ ጋር ቆይታ ( ሙሉውን ያዳምጡ )

በቬጋስ የሚከበረው የኢትዮጵያ ቀን ዝግጅትን በተመለከተ ቆይታ ከአዘጋጆቹ ጋር(ቃለ መጠይቅ)

በደቡብ ኦሞ ወንዝ ዙሪአ ለተገነባው የሀይል ማመንጫ ፣ የግዳጅ የሰፈራ ፕሮግራም እኛ ስለታቀደው መጠነ ሰፊ የሸንኮራ እርሻ በተመለከተ የእንግሊዝን መንግስት መሰሪነት ያጋለጠው እና የአውሮፓ ህብረት ያወጣው የመስክ ዳሰሳ ሪፖርት(ልዩ ጥንቅር)

ኢትዮጵያ (ግጥም)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

– አሜሪካ ሶማሊያ ለሚገኘው የኢሕአዴግ እና የጅቡቲ ጦር የመረጃና የስለላ ስልጠና እየሰጠች መሆኗ ታወቀ

– ሕንድ ከኢትዮጵያና ከኤርትራ ማንን እንደምመርጥ ተቸግሬያለሁ አለች

– አልበሽር ከእስር ወዳመለጡባት ደቡብ አፍሪካ ተመልሰው ሊሄዱ ነው

– ጦማሪያኑ ከእስር ይፈታሉ ብለው ብዙዎች እየጠበቁ ነው

– ኢትዮጵያ ለውጭ ዜጎች የተመቸችና ለራሷ ዜጎች አስቸጋሪ ስርዓት ያለባት መሆኗ ተገለጸ

– አቶ ማሙሸት አማረ በደህነቶች ክትትል ውስጥ መሆናቸውን ገለጹ

– የሕወሃት ከፍተኛ ባለስልጣናት የሙስና ፋይላቸው እንዳይገለጥ ተፈራርተው አሳለፉ

– በኢትዮጵያ ከሞቱ ሰዎች ለታማሚዎች ተለዋጭ ዐይን ማግኘት ከባድ መሆኑን የቀድሞው ፕሬዝዳንት ገለጹ

– ሊፍት በኔቫዳ ከሁበር ያነሰ ተሽከርካሪዎችን ለማሰማራት መወሰኑን ገለጸ

ተጨማሪ ያንብቡ:  Men Yedereg by - Genet Abate

– በአዲስ አበባ የውጭ ዜጋው የሒልተን ሆቴል ስራ አስኪያጅ ታስረው ተፈቱ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Share