በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ በወረዳው አመራር ላይ በተወረወረው ቦምብ 2 ልጆች ሞቱ * አመራሩና ባለቤታቸው ቆስለዋል

የደህሚት ድምጽ እንዘገበው በደቡብ ወሎ ዞን፤ ቦረና ወረዳ ውስጥ ሓምሌ 4/2007 ዓ/ም ወደ ወረዳው አመራሩ በተወረወረው ቦምብ ምክንያት 2 ልጆች መገደላቸው ተገለፀ።

በአማራ ክልል፤ ደቡብ ወሎ ዞን፤ ቦረና ወረዳ ውስጥ ሓምሌ 4/2007 ዓ/ም ከሌሊቱ 5 ሰዓት ላይ በወረዳው አመራር በአቶ መሓመድ ረሽድ ላይ በተወረወረው ቦምብ 2 ልጆች መሞታቸውና ራሱና ባለቤቱም ጭምር ክፉኛ በመቁሰላቸው ምክንያት ደሴ ሆስፒታል እያተካሙ መሆናቸውና እስካሁን ድረስም ድርጊቱ የፈፀመው አካል እንዳልተያዘ ለማወቅ ተችሏል።

በአሁኑ ግዜ በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች የስርዓቱ ባለስልጣናት በህዝቡ ላይ በሚያደርሱት ከፍተኛ ችግር ምክንያት ህዝቡ በአስተዳድሪዎቹ ላይ የበቀል እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ይታወቃል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የመከላከያ ሠራዊቱ የጀመረውን ሃገርን ህልውና የማዳን ዘመቻ ዘራፊውን የህወሓት ቡድን ለህግ እስኪያቀርበው ድረስ እንደሚቀጥል ተገለፀ|
Share