አስር አለቃ ጫላ ጋዲሳ ራሱን አጠፋ

ትህዴን ባሰራጨው ዘገባ ለሃምሌ ወር 2007 ዓ/ም የቆይታ ጊዜአቸውን ጨርሰው በሚገኙ የሰራዊት አባላት ላይ እየተካሄደ ባለው የከፋ የዘረኝነት ምልመላ ምክንያት አንድ የኦሮሞ ተወላጅ የሆነ የአስር አለቃ ማዓረግ አይገባህም በመባሉ የተነስ እራሱን እንዳጠፋ ተገለፀ።

ለትህዴን በደረሰው መረጃ መሰረት- የ23ኛ ክፍለ ጦር የ2ኛ ሬጅመንት በ3ኛ ሃይል ውስጥ የቲም ምክትል አዛዥ የነበረ አስር አለቃ ጫላ ጋዲሳ የተባለው ወታደር በተለያዩ መድረኮች ላይ ተቃራኒ የሆነ ሃሳቦችን ያቀርባል ለህገ መንግስቱ ታማኝ አይደለም መንግስትን ያማርራል የሚሉ ነጥቦችን አስቀምጠው ማዕረግ አይገባህም ተብሎ ከሃይል አመራር በላይ ያሉ አዛዦች ውሳኔውን በማስተላለፋቸው ምክንያት ስሜቱ የተጎዳው ይህ ወታደር ስብሰባው እንዳለቀ ዋርዲያ ነኝ በሎ በመውጣት እራሱን እንዳጠፋ ከእዙ የደረሰን መረጃ አመለከተ።

በአሁኑ ጊዜ በኢህአዴግ የሰራዊት አባላት ውስጥ ያለው የከፋ የዘረኝነት አድሎዎ ለማዕረግ እድገትና ለተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ሲባል በሚደረጉ ምልመላዎች ላይ የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች በሰራዊት ውስጥ ኢ- ፍትሃዊ የሆነ አሰራር እየሰሩ መሆናቸውን በተለያዩ የሰራዊት እዞች ውስጥ የሚገኙ ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ ያስረዳል ሲል ትህዴን መረጃውን ቋጭቷል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio: መምህር ግርማ ወደ አሜሪካ ሊመጡ ነው ተባለ፤ ኢትዮጵያ በኢቦላ ይጠቃሉ ከተባሉ አስር አገሮች ተርታ መሰለፉዋ ተገለጸ
Share