ኣብራሃ ደስታ – ከቅሊንጦ…!

ህወሓት ከኒኩለር በላይ የሚያስፈራት ብእርን እንደ ጉድ የሚያናግራት ጀግናው ኣብራሃ ደስታ በህወሓት ከታሰረ ወራቶች ኣለፉ።
በ”ሽብር” ክስ ተከሶ ቅሊንጦ ወህኒ ቤት የሚገኘው የዘመናችን ጀግና ኣብራሃ ደስታ እስር ቤት ሁኖም ህወሓቶችን እያስጨነቃቸው ይገኛል። ምክንያቱም እነሱ እንዳሰቡት የኢትዮዽያ ህዝብ “ኣብራሃ ኣሸባሪ ነው” ብሎ የሚያምን ሁኖ ኣላገኙትም። ባይሆን ሃሳብህን በነፃነት የመግለፅ መብት በኣግባቡ ከተጠቀምክበት እንደሚያሳስር ሊረዳ ችለዋል።
ይህ ኪሳራ የተረዱት ህወሓቶች ኣንድ መላ ይዘው ወደ ኣብራሃ ደስታ ሂደው “..ኣብራሃ ደስታ ኣሁኑኑ ከእስር ብንፈታህ መፃፍህን ታቋርጣለህንን…? የሚል የጭንቅ ጥያቄ ጠየቁት።
ጀግናው የመለሰው መልስ “…እንኳን ከእስር ተለቂቄ ላፕቶፔ ብታቀብለኝ እዚሁም እፅፍ ነበር…” በማለት ቅስማቸው ስብርብር ኣድርጎ ጣለው።
እንደነሱ ግምት ይሄ ሁሉ ግፍ እያወረድንበት እያለን ግፉን መሸከም ኣቅቶት “..ልቀቁኝ እንጂ ካሁን በሗላ እጄ ከእስኪርቢቶና ከላፕቶፕ ጋር ኣላገኛኝም..” እንዲላቸው ነበር።
ጀግናው ኣብራሃ ደስታ ያኔ ስንት የሚፃፍ ሃሳብ ፍንትው ብሎ ታይቶት ኖሮ ይሆናል…!
ኣብራሃ ደስታ ገዢዎች ሲረግጡት የሚረገጥ ቄጠማ(ጉዝጓዝ) ኣይደለም ሲረግጡት መለሶ የሚወኣጋ ጀግና ነው።
ነፃነታችን በእጃችን ነው..!
IT IS SO..!

ተጨማሪ ያንብቡ:  ባህርዳር ዙሪያ ጭስ አባይፓትሮል ተማረከ"ከ30 በለይ ተገደለ"!!
Share