Hiber Radio: ባልቆመው የጋምቤላው ግጭት 521 ሰዎች ሞተዋል፤ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያንን ወደ አሜሪካ አስገባ የተባለው ግለሰብ ሊፈረድበት ነው

/

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ መስከረም 18 ቀን 2007 ፕሮግራም

ለክርስትና ዕምነት ተከታይ አድማጮቻችን እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!

<... በጋምቤላ እየተደረገ ባለው ጭፍጨፋ የአማራ ተወላጆች የጥቃት ሰለባ ሆነዋል በአጠቃላይ የሞቱስ ሰዎች ቁጥር ከአምስት መቶ በላይ ነው ድርጊቱም አብረው በኖሩት የመዠንገርና የአማራ፣የኦሮሞ ወይም በሌላ ብሄር መካከል የተፈጠረ ግጭት ሳይሆን በወያኔ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ የዘር ማጥፋት ነው...>

አቶ ተስፋሁን አለምነህ የመኢአድ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ በጋምቤላ እየተካሄደ ስላለው የዘር ማጥፋት ወንጀል በስፍራው ሄደው ያዩትን እማኝ በማድረግ ጠይቀናቸው ከሰጡን ቃለ ምልልስ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

<<...ኪንታሮት ብቻ ሳይሆን የፊንጢጣ ኪንታሮት መነሻው ....ዘመናዊ ሕክምና ከተደረገ ነሁዋላ ይተካል የሚባለው...>>

ዶ/ር ኤፍሬም መኮንን ከአትላንታ ስለ ኪንታሮት በሽታ መንስኤውና መፍትሄው ካደረግንላቸው ቃለ ምልልስ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

የአሜሪካው ፕ/ት ኦባማ የመንን አስመልክቶ የተናገሩትና ወደ ቀውስ እያመራች ያለችው የመን (ልዩ ዘገባ)

የብጽዕ አቡነ ዮሴፍ የኔቫዳ፣የአሪዞናና የዩታ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እናየሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ አባል የመስቀል በዓልን በማስመልከት የሰጡት ቡራኬ

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በጋምቤላ ግድያው አልቆመም የሟቾች ቁጥር 521 መድረሱ ተገለጸ

በአካባቢው የተነሳው ግጭት መንስዔ የወያኔ አገዛዝ የተቀነባበረ የዘር ማጥፋት ሴራ ውጤት መሆኑ ተመለከተ

መኢአድ በጋምቤላ በአማራው ላይ የተወሰደውን የዘር ማጥፋት እርምጃ በቀላሉ እንደማያልፈው ገለጸ

የግብጽ ሚ/ር የአባይን ግድብ መጎብኘታቸው ከኢትዮጵያ ጋር ተስማምተናል ማለት አይደለም አሉ

በዝዋይ እስር ላይ የሚገኘው አበበ ቀስቶ ጆሮው በከፍተኛ ሁኔታ ታሞ ሕክምና መከልከሉን ይፋ አደረገ

አቶ አሰገደ ገ/ስላሴን ጨምሮ ከአረና የተባረሩ አባላት አንድነትን መቀላቀላቸው ተሰማ

በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንን በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አሜሪካ አስገብቷል የተባለው ግለሰብ የመጨረሻ የፍ/ቤት ውሳኔ ሊሰጠው መሆኑ ተዘገበ

ሱዳን ውስጥ የክርስትና ዕምነትሽን ካልቀየርሽ በሚል የግርፋትና የስቅላት የፍ/ቤት ውሳኔን በጸጋ የተቀበለችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሽልማት አገኘች

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

ተጨማሪ ያንብቡ:  Meles Zenawi’s VOA blacklist unveiled
Share