በሽብርተኝነት የተከሰሱት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ወደ ማዕከላዊ ተዛወሩ

በሽብርተኝነት ተከሰው አርባምንጭ ታስረው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞ ጎፋ ዞን አመራሮች ከነበሩበት የአርባ ምንጭ እስር ቤት አዲስ አበባ ወደሚገኘው የፌደራል ወንጀል ምርመራ መዘዋወራቸው ታወቀ፡፡

ከዞኑ አመራሮች መካከል የአርባ ምንጭ ምክትል ሰብሰቢ አቶ በፍቃዱ አበበ እና ደርጅት ጉዳይ ኃላፊው ኢንጅነር ጌታሁን በየነ ጱግሜ 5 ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ ወደ ማዕከላዊ የተዘዋወሩ ሲሆን ቀሪዎቹ አሁንም አርባምንጭ ውስጥ ታስረው ይገኛሉ፡፡

ወደ ማዕከላዊ የተዘዋዋሩትን የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞጎፋ አመራሮች ምግብና ልብስ ከማቀበል ውጭ መጠየቅ እንደማይቻል የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio: ኬኔያ ባለሃብቶቼ መሬት ለመቀራመት ሲሉ ወደ ኢትዮጵያ እየተሰደዱብኝ ነው አለች | በጋምቤላ የጎሳ ግጭት ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር መሪ በሀሰት ስማቸው እንደተነሳ ገለፁ | የኦሮሚያ ሰሌዳ የለጠፉ ላይ አገዛዙ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ የጣለውን እገዳ በተጠናከረ ተቃውሞ ለመለወጥ ተገደደ | በኢጣሊያው የ ላምባዱሳ ደሴት አቅራቢያ ለሞቱ ወገኖቻችን ተጠያቂዎች የሆኑ 6 ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ
Share