ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ተሸለመ

June 9, 2014
እስክንድር ነጋ

ሰኔ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የ2014 “የጎልደን ፔን ኦፍ ፍሪደም” ሽልማት አሸናፊ የሆነው እስክንድርነጋ ዛሬ ሽልማቱን ተቀበለ።

በጣሊያን ቶሪኖ በተካሄደው የሽልማት ስነ-ስር ዓት ላይ እስክንድርን ወክሎ ሽልማቱን የተቀበለው በቃሊቲእስርላይየነበረው ስዊድናዊ ጋዜጠኛ ማርቲን ሽብዬ ነው።

“ምኞቴ ይህን ሽልማት እኔ እንድቀበለው አልነበረም” በማለት ንግግሩን የጀመረው ማርቲን፣ “ዛሬ ጠዋት ስነሳ ምናለ፦“ ተፈታሁኮ፤ ሽልማቱን እኔ ራሴ ልቀበል እመጣለሁ” የሚል ስልክ ከአዲስ አበባ በስልክ ብሰማ ብዬ ተመኝሁ” ብሎአል።

“ይህ ግን አልሆነም፤ ከሰ ዓታት በፊት እስክንድር ነጋ በዱላቸው የታሰሩባትን ክፍል ግድግዳ እየመቱ በማይክራፎን “ቆጠራ!ቆጠራ!” እያሉ በሚጮኹ የወህኒ ጠባቂዎች ድምጽ ነው ከመኝታው የተነሳው” ያለው ማርቲን፣ የሙያ ባልደረባውን ወክሎ ሽልማቱን ሊቀበል በስፍራው መገኘቱን ግልጾአል።

“ምንም እንኩዋን ከሲያ እስር ቤት ነጻ እንደሆንኩ ባስብም፤ ከትስታዎቹና ከእስር ቤቱ ድምጾች ፈጽሞ ነጻ ልሆን አልችልም”ሲልም ማርቲን ተናግሮአል።

ማርቲን በሲሁ ንግግሩ እስክንድር በእስር ቤት እየደረሰበት ያለውን ስቃይ እና የቃሊቲ እስር ቤትን አስከፊና አስቀያሚ ገጽታዎች በበቂ ሁኔታ ለታዳሚዎቹ አሳይቶአል።

እስክንድር ህግን ጥሰሀል ተብሎ ለእስር የተዳረገው መንግስትን በመተቸቱ እንደሆነ ያወሳው ማርቲን፤ “ይህ የሚያም ቀልድ ነው”ብሎ አል።

“ይህ የጎልደን ፔን ሽልማት፤ ከ1000 ቀናት በላይ በእስር ላሳለፈው ለእስክንድር ነጋ ብቻ ሳይሆን እስክንድርን ለእስር ለዳረገው ለጋዜጠኝነት ሙያ ጭምር የተሰጠ ክብር እንደሆነ ይሰማኛል” ሲልም ለሽልማቱ ያለውን አክብሮት ገልጾአል።

እስክንድር በአካል ከደረሰበት ቅጣት በላይ ከቤተሰቡ እና ከሚወደው ብቸኛ ልጁ በመለያዬት የደረሰባት የመንፈስ ቅጣት የከፋ እንደሆነም ማርቲን አመልክቱዋል።

እስክንድር የተማረ እና በሌላ ሙያ ሊሰማራ እየቻለ በጨቁዋኞች እጅ እየተሰቃየ የሚገኘው ለእውነት ባለው የጸና አቁዋም እና ለሀገሩ ባለው ፍቅር ምክንያት እንደሆነም ገልጾአል።

Source: Ethsat

Previous Story

በፓኪስታን- ካራች አውሮፕላን ማረፊያ ከባድ ጥቃት ተፈጸመ።

Blue Nile 2
Next Story

አባይን እነማን መቼ ይገድቡት?

Latest from Blog

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት

የኢካን ዓላማ በኔዘርላንድ የሚኖረውን ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እና ኢትዮጵያውያንን ኮምዩኒቲይ የማሰባሰብ ሳይሆን የመከፋፋልና የማዳከም ተልኮን ያነገበ ነው።

አገር ! ለየአንድ ሠው ቋንቋው፣ ልማዱ፣ ባሕሉ፣ እምነቱ፣ አስተሳሰቡ፣ ወጉና በአጠቃላይ እሱነቱና ማንነቱ የሚከበርበት ብቸኛ ሥፍራ ነው። ኢትዮጵያውያንም በስደት በሚኖሩባቸው አገራት ሁሉ እነኝህን በስደት ያጧቸውን የግልና የጋራ ማንነቶቻቸውን በአንድ ላይ ሆነው ለመዘከር

ፋኖ ምሽጉን ደረመሰው ድል ተሰማ | ” ስልጣን እለቃለሁ ” ፕረዚዳንቷ | ህዴድ ድብቅ ስብሰባ በአዲስ አበባ | “ተመስገንን በመዳፌ ስር አስገብቼዋለሁ” አብይ

-966+9-የኦህዴድ ድብቅ ስብሰባ በአዲስ አበባ “ተመስገንን በመዳፌ ስር አስገብቼዋለሁ” አብይ – ስልኩ ተጠለፈ “እኛ የምን’ዘጋጀው ለፋኖ ሳይሆን ለኤር-ትራ ነው” አበባው|”በጊዜ ቦታ አዘጋጁልኝ” አረጋ

አንድ በኢኮኖሚና በሌሎች ነገሮች ወደ ኋላ የቀረች አገር አንድን ኃያል መንግስት በመተማመንና ጥገኛ በመሆን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ማምጣትና የተሟላ ነፃነትን መቀዳጀት ትችላለች ወይ?

ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ሰኔ 4፣ 2016 (ሰኔ 11፣ 2024)   በዚህ አርዕስት ላይ እንድጽፍ የገፋፋኝ ዋናው ምክንያት ሰሞኑኑ ዶ/ር ዮናስ ብሩ የቻይንንም ሆነ የቬትናምን በኢኮኖሚ ማደግ አስመልክቶ ሁለቱ አገሮች እዚህ ዐይነቱ የዕድገት ደረጃ ላይ ሊደርሱ የቻሉት ከአሜሪካ ጋር

ፋኖ አንድ ሌሊት አያሳድረንም” የአማራ ብልፅግናየኢሳያስ ግዙፍ ጦር ወደ ወልቃይት

ፋኖ አንድ ሌሊት አያሳድረንም” የአማራ ብልፅግናየኢሳያስ ግዙፍ ጦር ወደ ወልቃይት አብይና ዳንኤል ክብረት ጉድ አሰሙ-|ጀነራሉ በቁ*ጣ ተናገሩ-‘ህዝቡ ጉድ ሰራን’-|“ብልፅግናን ራ*ቁቱን አስቀርተነዋል”-|ታዳሚው ባለስልጣናቱን አፋጠጠ
Go toTop