የስብሰባ ጥሪ- የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የጋራ ግብረሃይል የፊታችን ጁን 15, 2014 ህዝባዊ ውይይት አዘጋጅቷል

የስብሰባ ጥሪ

በአገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት 23 አመታት በተለያየ መልኩ በጋራ እንዳንቆም ሲያጋጨን የቆየው የወያኔ አገዛዝ የመጨረሻ ካርዱን በመሳብ የቋንቋ እና የሀይማኖት ልዩነቶቻችን ጌጣችን መሆናቸው ቀርቶ እርስ በርስ የምንጋጭባቸው አጀንዳዎች እንዲሆኑ ሌት ከቀን እየሰራ ይገኛል:: አገራችን ኢትዮጵያ አሁን የምትገኝበትን ተጨባጭ ሁኔታ ለተመለከተውና ለተገነዘበው ሁሉ፤ መጪው ጊዜ እንቅልፍ የሚነሳና የአገራችን ሰላምና ህልውና ፈተና ላይ መውደቁን ያስገነዝበናል።

ይሄንን ወያኔ የቀበረውን የጥፋት ፈንጂ በአገርና በወገን ፍቅር እንዲሁም በብልሀትና በዘዴ ካላመከነው በስተቀር፣ የአገራችን የወደፊት እጣ ፈንታ አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱ አይቀሬ ነው:: ስለዚህ በውጭ የምንገኝ ወገኖች የመፍትሄው አካል ነንና ልናደርገው የምንችለውን ነገር ለማድረግ እንድንችል የመጀመሪያው መፍትሄ ግልጽ ውይይት ማድረግ ነው ብለን እናምናለን።

ስለዚህ ይህን በጎሳ እና በሀይማኖት ስም የተደገሰልንን የእልቂት ድግስ በዘዴ እንድንወጣው የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የጋራ ግብረሃይል የፊታችን ጁን 15, 2014 ህዝባዊ ውይይት አዘጋጅቷል።

በዚህ እና ተዛማጅ ወቅታዊ ችግሮቻችንን ላይ በግልፅና በጥልቀት ለመወያዬት የመፍትሄ ሃሳቦችን እንዲጠቁሙን የተለየዩ ምሁራንን እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦችን ለውይይት ጋብዘናል፤ እርሰዎም ከተጋባዦቹ ጋር በጋራ እንዲመክሩና እንዲሁም የሚሰማዎትን ጥያቄ እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል።
ተጋባዥ እንግዶች፥

ፕሮፈሰር ቲዮዶር ቨስታል
አቶ ኤፍሬም ማዴቦ
ዶክተር ኑሩ ደደፎ
ዶክተር አልማዝ ዘውዴ
ጋዜጠኛና አክቲቪስት አበበ ገላው

ቀን: እሁድ ጁን 15, 2014
ቦታ: 7701 16th Street, NW Washington, DC. 20012
ሰአት: 3PM
አዘጋጅ: የዋሽንግቶን ዲሲ የጋራ ግብረ ሀይል
ለበለጠ መረጃ: ስልክ (202) 556-3078 ኢሜል dcjointtaskforce@gmail.com

ተጨማሪ ያንብቡ:  በሐረር ከተማ ባሉ ነጋዴዎች ላይ እየተደረገ ያለው ጫና ተጠናክሮ ቀጥሏል
Share