የዘ-ሐበሻ 6ኛ ዓመት ጁን 15 አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ በሚገኝበት ይከበራል

የሚኒሶታ ምርጥ ሰው ይሸለማል ከተመሠረተች 6ኛ ዓመቷን የምትይዘው ዘ-ሐበሻ በደመቀ ሁኔታ በዓሉን በሚኒሶታ እሁድ ጁን 15 ቀን 2014 ዓ.ም እንደምታከብር የzehabesha LLC መስራችና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሔኖክ ዓለማየሁ አስታወቀ። ዘ-ሐበሻ በጋዜጣ መልክ በሚኒስታና በአካባቢዋ የምትሰራጭ ሲሆን በድረገጽ ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ አድጋ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያውያን ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ መሆኗን የሚገልጸው ሔኖክ “ድረገጹ በየቀኑ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ወገኖች እንደሚጎበኝ ከጎግል የምናገኘው መረጃ ያሳያል፤ ከዚህም በተጨማሪ የሰርቨር ወጪያችን እንዲጨምር ምክንያት ሆኖናል” ይላል። አንድ ድረገጽ ከፍተኛ ተመልካች ሲኖረው ያን ማስተናገድ የሚችል ትላልቅ ሰርቨር ያስፈልገዋል የሚለው ጋዜጠኛው ድረገጹ አንዳንድ ጊዜ በከፍተኛ ተመልካች ብዛት ሰርቨሩ እየተጨናነቀ የመጓተትና አንዳንዴም ሰዎችን አላስገባ እንደሚል ገልጾ ይህን ችግር ለመፍታት አንባቢዎች የዘ-ሐበሻን ወጪዎች እንዲጋራ በድረገጹ ላይ ጥሪ አቅርቦ እንደነበር አስታውሷል። “በድረገጻችን ላይ ባደረግነው የድጋፍ ጥሪ ኢትዮጵያውያን በገንዘብ በኩል ያሳዩን ድጋፍ አነስተኛ ነበር” የሚለው ጋዜጠኛው በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ጊዜያት ድረገጹን ለመረዳትና ብዙ ሰዎችን ካለምንም ችግር ማስተናገድ እንዲችል የገንዘብ ድጋፍ አድርገው እንደነበርና እነርሱንም በዚህ አጋጣሚ እንደሚያመሰግን ገልጿል። የዘ-ሐበሻ በተለይ የሚኒሶታ ወዳጆች ላለፉት 6 ዓመታት ዘ-ሐበሻን እንዴት መርዳት እንችላለን? ጋዜጣውን በሽያጭ ለምን አታደርጉትም ሲሉ የተለያዩ ወገኖች ሲጠይቁን ነበር የሚለው ጋዜጠኛ ሔኖክ ዓለማየሁ ያንን ለማድረግ ሳይቻል ቀርቶ ነበር። ሆኖም ግን አሁን ጁን 15 ቀን 2014 ዓ.ም በኬሊ ኢን ሆቴል አክቲቪስት ታማኝ በየነን በመጋበዝ የሚኒሶታ ወዳጆቻችን ዘ-ሀበሻን የሚያጠናክሩበት ምሽት አዘጋጅተናል ብሏል። በዚህ የዘ-ሐበሻ 6ኛ ዓመት በዓል ላይ ሁሉም የዘ-ሐበሻና የነፃ ሚድያ ደጋፊዎች እንዲገኙ ጥሪ ያቀረበው ሔኖክ አርቲስት ታማኝ በየነም ዘ-ሐበሻ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያከናወነችው የመረጃ መጋቢነት ተግባርን በማድነቅ ሌሎች ፕሮግራሞችን በመሠረዝ ለዘ-ሐበሻ አጋርነቱን በማሳየቱና ወደሚኒሶታ ለመምጣት መወሰኑን በማድነቅ ምስጋና አቅርቧል። በዘ-ሐበሻ 6ኛ ዓመት በዓል ላይ የሚኒሶታ የዓመቱ ምርጥ ኢትዮጵያዊ እንደሚሸለም ያስታወቀው ጋዜጠኛው ይህ ሽልማት ወደፊትም እንደሚቀጥል ገልጾ የዘ-ሐበሻ ወዳጆች ጁን 15 በኬሊ ኢን ሆቴል በመገኘት የበዓሉ ተካፋይ እንዲሆኑ ተጠርተዋል። የዘ-ሐበሻ በዓል የሚከበርበት አድራሻ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይህች ኮሜዲያን እንደ ርዕዮት ዓለሙ ወይም እንደቴዲ አፍሮ?

Best Western Plus Kelly Inn Address:
161 St Anthony Ave,
St Paul,
MN 55103

ዝግጅቱን ለማገዝና እንዴት ዘ-ሐበሻን ማገዝ እንደምትችሉ ለመጠየቅ የበዓሉን ዋና አስተባባሪ አቶ አልዩ ተበጀን በስልክ ቁጥር 612-986-0557  ያነጋግሩ።

ለዘ-ሐበሻ በቼክ እገዛችሁን ለመላክ
Zehabesha LCC
6938 Portland Ave S
Richfiled
MN 55423

መጠቀም ትችላላችሁ።

ዘ-ሐበሻን በፔይፓል በኩል ማገዝ ለምትፈልጉ የሚከተለውን ሊንክ ላይ ይክፈሉ

እውነት ያሸንፋል!

Share