May 23, 2014
3 mins read

አንድነት በአዳማ ከተማ የጠራው ሰልፍ ለሰኔ አንድ መተላለፉን አስታወቀ

አንድነት ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በአዳማ ከተማ ለማድረግ አቅዶት የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ለሰኔ አንድ መተላለፉን ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ አስታወቀ።
የድርጅቱ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚከተለው ነው፦

የአንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የመሀል ቀጠና ፅ/ቤት ለግንቦት 10 ጠይቆት የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በገዢው ፓርቲ የተለያዩ ሰበቦችና ምክንያቶች ሲድበሰበስ ከርሞ ለሰኔ1ቀን2006 ዓ.ም መተላለፉን የመሀል ቀጠና ጽ/ቤቱ በጠራው የአስቸኳይ ስብሰባ መወሰኑንና ይህንኑ ውሳኔውንም በቀን መወሰኛ ደብዳቤው ላይ ገልጾ ለአዳማ መስተዳድር ከንቲባ አቶ አብረሐም ማስረከቡን በመረጃ አያይዞ ገልጧል፡፡ በመሆኑም ሰኔ አንድ የአንድነት ደጋፊዎችና አባላት እንዲሁም የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች የሆናችሁ ነጋዴዎች፣ተማሪዎችና ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል በሰልፋችን ላይ በመገኘት በገዢው ፓርቲ ላይ የተባበረ የተቃውሞ ድምጻችንን በሰላማዊ የትግል ስልት መንፈስ እንድናሰማ ጋብዘናችኋል፡፡ ሰኔ አንድ አይቀርም!

መነሻችን 4፡00ሰዓት ፣አዳማ ራስ ሆቴል (የቀድሞው መነን ሆቴል) ሆኖ፣ በፍራንኮ ሆቴል አርገን ወደ ምንጃር ጎዳና እንወጣና፤ ከሳር ተራ በአዲሱ ግንብ ገበያ ወደ መብራት ሐይል አቅንተን፤ ቁልቁል በአንደኛ መንገድ (ግርማሜ ነዋይ ጎዳና) ከደራርቱ አደባባይ ፊት ለፊት ካለው የፖስታ ቤት ሜዳ ላይ ማሳረጊያ እናደርጋለን፡፡ በጳጉሜ ሶስት የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት የሁለተኛ ዙር ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ የሚሊየኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መሪ ቃል ላይ ተመስርተን በሀገሪቱ ስላለው ኢፍሀዊ የመሬት ስሪት እንጮሀለን! በመልካም አስተዳደር ዕጦት ስለሚደረጉ የሙስና ወንጀሎች የተቃውሞ ድምጽ እናሰማለን!-ኑ ኑና አብረን ድምጻችንን እናሰማ!!

ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እንጠይቃለን!
ብሎገሮች እንዲፈቱ እንጠይቃለን!
የኦሮሞ ተማሪዎች ጥያቄ ፍትሀዊ ምላሽ እንዲሰጠው እንጠይቃለን!
ኑና አብረን ድምጻችንን እናሰማ!!

አንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ (አዳማ)

Previous Story

የአረና አመራሮች በሐውዜን ከተማ አዳራሽ ውስጥ ታግተዋል

10262
Next Story

የዕንቁ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ማዕከላዊ እንዲቀርብ ታዘዘ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop