ከአዲስ አበባ ፕላን ተማሪዎቹ አይቀድሙም?

ዳዊት ሰሎሞን

በዛ ካሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየሰማናቸው የምንገኛቸው ዜናዎች አስደንጋጭ ናቸው፡፡ለነገሩ ገዢው ፓርቲ የሚከተለው ሩሲያን ከመፈረካከስ ያላደነ የፖለቲካ መስመር እንዲህ አይነት ፍሬ ማፍራቱ የማይጠበቅ አልነበረም፡፡እናም የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ተማሪዎች የአዲስ አበባ አካባቢዎችን ወደ አዲስ አበባ ይጠቀልላል የሚል ስጋት ባሳደረባቸው የከተማይቱ ማስተር ፕላን ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ለመግለጽ የተቃውሞ ሰልፎችን ለማድረግ ዝግጅት አጠናቅቀው ወደ ትገበራው ሲያመሩ ግጭት ተፈጥሮ በዛ ያሉ ተማሪዎች መጎዳታቸውን ሰምቼያለሁ፡፡


በእኔ እምነት ማስተር ፕላኑን ያዘጋጀ አካል ፊት ለፊት ቀርቦ ለመነጋገር ስህተት ከተሰራም እርማት ለመውሰድ ለምን እንደማይደፍር አይገባኝም፡፡መቼም ተማሪዎቹ ተቃውሞ ያቀረቡት መሬታችን ተቆርሶ ለባዕድ አገር ሊሰጥብን ነው በማለት አይመስለኝም፡፡ስጋታቸው ቤተሰቦቻቸው ከያዟት ኩርማን መሬት ጋር የሚጋመድ ይመስለኛል፡፡ ነገ ቤተሰቦቻቸቸው የያዟትን ኩርማን መሬት በሊዝ ለአንዱ ባለ ጊዜ ተሰጥታ ፎሪ እንዳይወጡ ሳይሰጉ አልቀሩም፡፡ይህንን ስጋት በፖሊስ ቆመጥና በፌደራል መሳሪያ ማስወገድ ይቻላል እስካልተባለ ድረስ መነጋገር መቅደም ይኖርበታል፡፡


እባካችሁ ለንግግር ዕድል ስጡ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወንጀለኛው የሕወሓት ጁንታ ቡድን ደብረጺዮን መሪ ለሲኤንኤን ጠየቀ
Share