ረዳት ፓይለቱ ኃይለመድህን አበራን በመደገፍ በስዊዘርላንድ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠራ

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላንን ወደ ስዊዘርላንድ አቅጣጫ አስቀይሮ የዓለም መነጋገሪያ የሆነው ረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራን በመደገፍ፤ የስዊዘርላንድ መንግስት አብራሪው የጠየቀውን የጥገኝነት ጥያቄ እንዲቀበለው ለመጠየቅ በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ። አርብ ፌብሩዋሪ 28 ቀን 2014 በበርን  ከ12 ሰዓት ከ30 ጀምሮ ይደረጋል በተባለው በዚሁ ሰልፍ ላይ “የሃይለመድህን ድምጽ የኔም ድምድ ነው” በሚል መርህ እንደሚደረግ የሰልፉ አስተባባሪዎች ለዘ-ሐበሻ በላኩት በራሪ ወረቀት ላይ አስታውቀዋል። በዚህ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንዲገኙም ጥሪ ቀርቧል።
ሃይለመድህን አውሮፕላኑን ወደ ስዊዘርላንድ ጠልፎ ካሳረፈው በኋላ ይህን ዜና የዘገቡ የውጭ ሚዲያዎች በአብዛኛው በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት አብረው ዘግበዋል። የአውሮፕላን ጠለፋውንም ከዚሁ የሰብአዊ መብት አለመከበር ጋር አያይዘው ብዙ መዘገባቸው ይታወሳል።

የሰልፉ በራሪ ወረቀት (ፍላየር) የሚከተለው ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio: ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ አሜሪካ ለአንባገነኑ ስርዓት ድጋፍ እየሰጠች መሆኗ እንዳስገረማቸው ገለጹ * በርሃብ ሳቢያ ከሰንኣ እስር ቤት ሊያመልጡ የሞከሩ ሁለት ኢትዮጵያውያን ሞቱ የቆሰሉም አሉ * ሁለት ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የዘረኝነት ጥቃት ደረሰባቸው * የአውዳመት ገበያ ትንታኔ እና ሌሎችም....
Share