የታዘዘለትን ማስታገሻ ህመሙ ስለበረታበት ቶሎ ቶሎ በመውሰዱ የህመሙ ማስታገሻ መድኃኒት አልቋል። ጓደኞቹ ማስታገሻ መድኃኒት ይዘውለት ቢሄዱም ማረሚያ ቤቱ ለማስገባት ፈቃደኛ አልሆነም።እናም ገብርዬ ያለ ማስታገሻ እየተሰቃዬ ይገኛል።
ሰሞኑን ቀዶ ጥገና ሲደረግለት ቀዶ ጥገናው ሙሉ በሙሉ አልተሰራም። የወጣለት እባጭም የተወሰነ ነው። ምክንያቱም እባጩን ሙሉ በሙሉ ለማውጣት ተኝቶ መታከም እንዳለበት ሀኪሞች በመናገራቸው ። ብልጽግና ደግሞ ተኝቶ እንዲታከም አልፈቀደም። አሳሳቢው ነገር ግን ዛሬ ከፍተኛ ደም እየፈሰሰው ነው። የድካም ስሜት አለው መቆም አይችልም ብዙ ማውራትም አይችልም። ከፈሳሽ ውጭ ምንም አይነት ምግብ አይወስድም።
ከምንም በላይ አሳሳቢው ነገር በእዚህ የህመም ስቃይ ውስጥ ወደ የት እንደሚወስዷቸው ባይታወቅም እቃችሁን ሸክፉ ተብለዋል።
አስገራሚው ነገር የክርስቲያን እና ዮሀንስ ህመም ተመሳሳይ መሆኑ ብዙ ጥያቄ ያስነሳል።
ፍትህ ልጠይቅ አልመጣሁም ። ስርዓቱ ተጠይቆ ፍትህ ስለማያሰፍን። ነገር ግን የዐብይ ጀምበር መጥለቂያዋ ስለተቃረበ ጉዳዩ ለታሪክ እዚሁ ገጽ ለማስቀመጥ እንጅ ።
Telegram ላይ እንወዳጅ 👇👇👇
https://t.me/TesfayeWoldesilassie