ኢትዮጵያውያን አድዋ ላይ ያሸነፉት የአለምን ህግ ነበር – ይርጋ ገላው

የሃገራችን ህዝቦች መልካቸውም፣ ባህላቸውም፣ ሃይማኖታቸውም፣ ቋንቋቸውም፣  ታሪካቸውም፣ ፍላጎታቸውም፣ ስነልቦናቸውም….  ተመሳሳይ ነው።  ተመሳሳይ ማለት “አንድ” ማለት አይደለም። ልክ ከአንድ ምድር ላይ እንደሚበቅሉ ልዩ ልዩ እጽዋት፣  ልክ ከአንድ የቤተሰብ ግንድ እንደሚመዘዙ የተለያዩ ልጆች፣ ምንጫቸው ላይ፣ የማንነታቸው ንጥረነገር ውስጥ አንድ የሚያደርጋቸው መሰረት አለ።  አድዋ የዚህ የአንድነት መሰረት ገሃዳዊ መገለጫ ነው። አድዋ የሃገራችንን ልዩ ልዩ ህዝቦች አንድነት ያስመሰከረ ብቻ ሳይሆን፣ ሃገራችን ኢትዮጵያ ከወራሪ ቅኝ ገዢዎች ጋር ያላትን ልዩነት አንጥሮ ያወጣ የድል ቀን ነው። የአድዋ ጦርነት አይቀሬ ነበር። ምክንያቱም የሃገራችን ህዝቦች ያላቸው ስነልቦና፣ ቋንቋ፣ አስተሳሰብ፣ እምነት፣ ባህል፣ ፍላጎት ሁሉ ጣልያን ከአውሮፓ ይዞት ከመጣው የተለየና ተቃራኒ  ስለነበረ ነው። በመላው አለም “አውሮፓን የሚቃረን ማንነት ሁሉ ለአውሮፓ መገዛት … Continue reading ኢትዮጵያውያን አድዋ ላይ ያሸነፉት የአለምን ህግ ነበር – ይርጋ ገላው