December 23, 2024
2 mins read

አፈትልኮ የወጣ መረጃ:- የማክሮን ጉብኝት ጉዞ ከአራት ሰአት በታች እንዲጠናቀቅ ሆነ

GfbGzQYWQAAzilz

የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ወደ ኢትዮጵያ ሲሄድ his original itinerary የሚያሳየው ቅዳሜ ማምሻውን ገብቶ እሁድ ውሎ ቤተ መንግስቱን መርቆ ላልይበላን ሳይቀር እጎበኛለሁ ብሎ አስቦ ነበር:: ነገር ግን ወደ ኢትዮጵያ እየበረረ ሳለ ብዙ የintelligence መረጃ ይደርሰዋል በጉብኝቱም ኢትዮጵያውያን እንደማይደሰቱም ተነገረው:: በዚህ መሰረት ጉዞውን rearrange ማድረግ አስፈለገው ለአንድ ቀን ተኩል ታቅዶ የነበረው ጉዞ ከአራት ሰአት በታች እንዲጠናቀቅ ሆነ::

ከምሽቱ አስራ አንድ ሰአት ገባ ማታ ሶስት ስአት ላይ ተጣድፎ ወጣ:: ከአብይ ጋር 45 ደቂቃ ከአዳነች ጋር በጥድፊያ ሰላሳ ደቂቃ ጋዜጣዊ መግለጫ 35 ደቂቃ ብቻ በማጥፋት ላስ ብሎ መሄዱ ተሰምቷል:: እንኳን ላሊበላን ሊጎበኝ አዲስ አበባ የHIM ቤተመንግስትንም ሳይመርቅ ዛሬ ራሱ አብይ አህመድ ሄዶ መርቆታል;:

ላሊበላን እንዳታስብ በፋኖ ስር ነው ያለው ተብሎ ተነግሮታል:: አገዛዙ ሰሞኑን በላሊብላ ፋኖን አጠፋለሁ ብሎ ብዙ ሙከራ ሲያደርግ የነበረውም ለዚሁ ለማክሮን ጉብኝት መንገድ ጥርጊያ ተብሎ ነበር::

ፋኖዎች ግን ፋሽስት አብይ አህመድ ወደ ስፍራው የሚልከውን ሰራዊት እያጨደ ከነ አዛዥ ተብዬው ከምሮለታል:: ባጭሩ ማክሮን got the memo!

 

 


 

3 Comments

  1. አጼ ዮሃንስ በሱዳን ጉዳይ ከሱዳን ህዝብ ጥቅም በተቃራኒ
    ለአውሮፓ ቅኝ ገዥ ሃይል ድጋፍ ሰጡ። ያ ስሕተት ለንጉሠ ነገሥቱ ገዳይ፣ ለኢትዮጵያን አጥፊ ነበር። ያስከተለው መዘዝ፣ የኤርትራ ግዛት እና የቀይ ባህር ወደቦች መጥፋትን ጨምሮ ሌሎችም ይገኙበታል። አብይ አህመድ የንጉሱን አስከፊ ስህተት እየደገመ የአፍሪካን ጥቅም በመጻረር ከፈረንሳይ ጋር ኮንሰርት እየጨፈረ ነው። ፈረንሳይ በምእራብ አፍሪካ ግንባር እያጋጠማት ያለውን ኪሳራ
    ለማስተካከል በምስራቅ አፍሪካ ከሃዲ አሻንጉሊቶችን ትፈልጋለች። ይህ የክህደት ተግባር (እንደ
    የጦር መሳሪያ ማስተላለፊያ ማገልገልን ጨምሮ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ መግባት) ለኢትዮጵያ ምን ያህል አስከፊ መዘዝ እንደሚያመጣ ጊዜ ብቻ ይነግረናል።

  2. ያፈተለከው ወሬ የቱ ነው? የፈረንሳዪ መሪ በሃገሩ ተደራራቢ ችግር ያለበት፤ በማዳካስካርና በሞዛቢክ መካከል ባለች ማይዪቲ (Mayotte) በሚባል የደሴቶች ክምችት ላይ በደረሰ የተፈጥሮ አደጋ እዚያው አቅንቶ ወደ 300 ሺህ የሚሆነውን ህዝብ ለማረጋጋት ሞክሮ ወደ ኢትዮጵያ ያቀናው የፈረንሳይ መሪ 4 ሰአት ቆየ ሁለት ሰአት አፈትላኪ ወሬ አይገኝበትም። ግን ያው ልክ እንደ ነጮቹ የዜና አውታር ነገር ማጋነንና ፈጠራንም የሃበሻውም ወሬ አቀባዪች እየተካኑበት በመሆኑ ራሳቸው ባጠመድት ወጥመድ ተጠልፈው ሲወድቁ ማየት የተለመደ ሆኗል። ሰከን በሉ። ልብ ግዙ፤ ሁሉ ወሬ አይሆንም!
    ጊዜው መሽና ሰው እረሳው እንጂ ባድመን ሰበብ አድርገው የሃገራችን እብዶች ሲጨራረሱ በድንገት በመቀሌ ዙሪያ አንድ አውሮጵላን ተመትቶ ወድቆ ዜናው ይሰራጫል። ወያኔዎችም በጃንጥላ የወረደውን ፓይለት ተሸክመው ሆ ይላሉ። አብረን ይህን ጉዳይ የማናይ አሁን በህይወት ያለ ጓደኛዬን ጎሸም አረኩትና ተው እባክህ ይህ የኤርትራ ፓይለት አይደለም የራሳቸውን ሰው ነው መትተው የጣሉት ስለው ተቆጣ። በህዋላ ግን ጉዳዪ እውነት እንደሆነ ተደረሰበት። ሌላ ልጨምርበት። ወያኔና ብልጽግና ከአንዴም ሶስት ጊዜ ሲፋለሙ ወያኔ ሙቱን እየለቀመ ወንዝ ዳር ወስዶ ሲጥል ሱዳናዊቷ የ CNN ወሬ አቀባይ ያለምንም መረጃ ወንጀሉ የተፈጸመው በኢትዮጵያ መከላከያ እንደሆነ አሰራጨች። የኢትጵያ መከላከያ እንኳን እንዲህ ሊያደርግ ቀርቶ እግሬ አውጭኝ በማለት ወደ መሃል ሃገር በመንጎድ ላይ ነበር። ቆይቶ ዜናው እንደተሰራው ሳይሆን የወያኔ ሴራ መሆኑ ታወቀ። አንድ የቅርብ ቀን ወሬ ልጨምርና ላብቃ። ቡና እየጠጣን ሶሪያ ውስጥ አሁንም የCNN ወሬ አቀባይ የሆነች ነጭ ስለ አንድ ከሥር ስለተፈታ ሰው ወሬ ስታናፍስ እስር ቤቱ ድረስ ገብታ የለበሰው ብርድ ልብስ እስኪገፈፍ ታይ ነበር። ታዲያ ያለቅጥ የተቅበጠበጠውና ፊቱ የወዛው እስረኛ እስረኛ ሳይሆን የሶሪያ ወታደር የነበረ መሆኑን ቆይቶ ታወቀ። እነዚህ እብዶች በስመ ጋዜጠኝነት ጊዜን ማንበብ የማይችሉ፤ አዙሮ ማየት ያልተፈጠረባቸው፤ ልክ እንደ እንስሳ ከነጎደው ጋር የሚነጉድ ወሬን ለንግድ የሚያቀርቡ የዘመናችን የወሬ መደብሮች ናቸው። ጎኔ ለተቀመጠው ጓደኛዬ ወገኔ ይህ ሰው ዛሬ እስር ቤት ገብቶ ካለሆነ እስረኛ አይመስለኝም ስለው እንዴ ያምሃል እንዴ በሩን በጥይት ተሰብሮ ከውስጥ ሲያወጡት እያየህ አለኝ። ራሱን ቆልፎ ነው ስለው ተናደደብኝ። አሁን ወደ ልቡ ተመልሱ እኔ ግን አንተ ያየኸውን እንዴት ማየት አልቻልኩም ሲለኝ በቀልድ እኔ መነጸር ለብሼ ስለነበረ ነው በማለት ተሳሳቅን።
    ዓለሙ ሁሉ አብዷል፤ ወራሪው ተወረርኩ፤ ዘራፊው ተዘረፍኩ የሚልበት ነጫጭባ ጊዜ ላይ እንገኛለን። ወሬም ሆነ ጫወታ መሰረት ሲኖረው ትምህርት ይገኝበታል። ዝም ብሎ ጭራ ይዞ አንገቱን ይዠዋለሁ ማለት እብደት ነው። ግን እኮ አሁን ላይ ምንም አይነት ነገር ቢሆን እውኑን ከፈጠራው መለየት እየተሳነን ነው። አይ ስልጣኔ። ድንቄም ስልጣኔ የሰው ንግድ፤ የወሬ ንግድ! የፈረንሳዪ መሪ የኢትዪጵያ ጉብኝትም በፊትም በሌሎች የሆነ ወደፊትም የሚሆን ነው። ያፈተለከ ለወሬ ፍጆታ የቀረበው ምናባዊው የውሸት ተስፈኝነት ብቻ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop