በጎንደር ዩንቨርስቲ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው ተባለ

የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማርኬቲንግ ማኔጅመንት የ3ኛ ዓመት የዲግሪ ተማሪ የሆነው ወጣት አንተነህ አስፋው ለገሰ በፅንፈኛው ወያኔ አባላት በጩቤ ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ ሟች ወጣቱ ያነሳቸው የነበሩ ጥያቄወች በስፋት መነሳት ጀምረዋል ሲል  የ አማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ (አወጋን)  ለዘ-ሐበሽ በላከው መረጃ አስታወቀ።

“ሟች አንተነህ ዘረኛው የወያኔ ወራሪ ቡድን በንፁሃን አማራ ተወላጆች ላይ የሚያደርሰውን ግፍ እና በአጠቃላይ በሀገሪቱ ዉስጥ አየተፈፀመ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ያለፍርሃት ይቃወም የነበረ ሲሆን ደካማው የወያኔ ቡድን የለመደውን ደም ማፍሰስ ተግባሩን ፈፅሞበታል” ያለው  አወጋን  “ወጣቱ የተገደለው በጩቤ ተወግቶ ሲሆን እሬሳው ከዳሽን ብራ ፋብሪካ በስተጀርባ ተጥሎ ተገኝቷል” ሲል ዘግቧል።(

“የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ እሄን አስከፊ የሆነ የጠባቦች ድርጊት አጥብቆ የሚቃወም ሲሆን ወነጀለኞችን በተገኙበት ለመቅጣት ያለ እረፍት ይሰራል ወጣቱ ከዚህ መማር ያለበት ነገር ቢኖር የወንድማቺን የአንተነህ እጣ ሳይደርሰው ወያኔን ለማስወገድ የምናደርገውን ትግል በመቀላቀል የወገኖቻችን የስቃይ አመታት እናሳጥር በማለት መልክቱን ያስተላልፋል” ያለው አወጋን “ለሟች ቤተሰቦች መጥናናቱን ይስጥ” ሲል ሐዘኑን ገልጧል።

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አሁንም ውጥረቱ እንዳየለ ነው ቢባልም የመንግስት ሚድያዎች አንዳችም መረጃ አልሰጡም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኩዌት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ አሳሳቢ ሆኗል

5 Comments

  1. sijemer sirachehu mawonabed silhone denkorowche kemalet weche minim alilem bemjemereyia bemin endmote enkwan lemawok mokru man gedlewm yemelewn ewoku enante dedboche

  2. Addisu Legesse; Bereket Simon, Ayalew Gobeze and Demeke Mekonen are currently in Gondar: no one know exactly what they are cooking.

  3. sgemer ligu twlde amara aydelem sketel bechube mewegatu lay new tyakew enante
    stone heads…………

  4. ዘ፡ሐበሻ እንደ ማንኛውም ሚድያ ተቋም የቀረበለትን ዜና ለሕዝብ
    ማቅረብ እንጂ የወንጀል መርማሪ እኮ አይደለም፡አስተያየት ለመስጠት
    ከመሮጥ ቅድምያ ዜናውን አንብቦ መረዳት ያስፈልጋል፡
    ዘ፡ሐበሻ አወጋን ለግድያው የሰጠውን ሐሳብ ነው ያቀረበው እንጂ
    የዘ፡ሐበሻ ፈጠራ አይደለም፡በሗላ ቀርንት የጎሳ እና የወገን ተለይ
    አስተሳሰብ በሕዝብ ደም ባንሳለቅ ለሑሉም ጠቃሚ ይመስለኛል
    እንደ ማንኛውም ኖርማል ሕዝብ በሐገር ደረጃ መንጋገሩን ትተን
    በዘር በጎሳ የበላይ የበታች እያልን እራሳችን ኢትዮጵያውይ እታችን
    ባናጠፋው ምን ነበር፡

  5. The TPLF regime has bent on obliterating Amhara on the face of Ethiopia and beyond. They have been pouring millions of dollars in neighboring countries in order to eliminate any person who is advocating for Amhara. I have been subjected to inexplicable suffering in Kenya because I have exposed the 2.4 millions Amhara disappearance on the face of Ethiopia and other atrocities committed on the people of Amhara in particular and Ethiopia in general on Social media. The killer of Anteneh Legesse must be punished. We shouldn’t allow TPLF nexus-of-evils to kill our people in cold blood. Enough is Enough.

Comments are closed.

Share