እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን… ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው – ሰርፀ ደስታ

ይህ ቃል በመጻፈቅዱስ ተጽፎ  ያለ ሁሌም በስታወስኩት ቁጥር በጣም የሚገርመኝና ሁኔታዎችንም ሳስተውል የሚያስደነግጥ ሆኖ አገኘዋለሁ፡፡ ቃሉ የት ምህራፍና ቁጥር ላይ እንዳለ አላውቅም ግን ሙሉው እንደሚከተለው ነው የሚለው፡፡ አስታውሰዋለሁ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው ነው የሚለው፡፡ እግዚአብሔር እውነት ነው! እውነትን (እግዚአብሔርን) ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን ማለት ነው፡፡ አንዴ ለማይረባ አእምሮ ተላልፎ ከተሰጠ ደግሞ በምን አስቦ ነገሮችን ለመረዳት ይቻላል? ዛሬ በእኛ ላይ እየሆነ ያለው እውነት ይሄ ነው፡፡ ሆኖም ለማይረባ አእምሮ ተላልፈን ስለተሰጠን ትክክለኛውን ነገር በምን አእምሮ ማሰብ እንችላለን፡፡ በ60ዎቹ  እግዚአብሔር የለም ብሎ የተነሳው ራሱን ምጡቅና አዋቂ አድርጎ የነበረው ትውልድ እርስ በእርሱ እንደ ኖህ ዘመን ፍጥረታት ተባልቶ አለቀ የተረፈውም ለቀጣይ የአገር ነቀርሳ ሆኖ ቀረ፡፡ አውቃለሁ ምጡቅ ነኝ የለው ደፋር እውነትን ስለካደ በየስርቻው ቀረ ቀሪውም የማይሆን ሆኖ ግን ልክፍቱ እስከዛሬም ለእኛ ተረፈ፡፡ እንግዲህ ለማይረባ አእምሮ የተሰጠ በምን አእምሮ እንዲረዳ ይመክቱታል፡፡ በገዛ ቤቱ ላይ እሳት ለኩሶ ኧረ ውጣ ቢሉት እንኳን  ያለገባህ ደንቆሩ እንዴት ሆኖ ነው እኔ ራሴ የለኩስኩት እሳት እኔን የሚያጠፋኝ እያለ የሚጋይ ነው!

ሰሞኑን በአገራችን እየሆነ ያለው ብዙ ነገር አሳሰበኝ! የሰው ልጅ አእምሮ እውነትን፣ ሠላምንና መልካም ነገርን ጠልቶ ክፋትን በወደደው መጠን ምን እንደሚሆን በድጋሜ ከላይ የጠቀስኩትን ጥቅስ ደጋግሜ እንዳስበው አስገደደኝ፡፡ በመላው ዓለም ያለው የሰዎች እልቂትና መከራ መንስኤው ይሄው ለማይረባ አእምሮ መሰጠት እንደሆነ ደጋግሜ ዳሰስኩት፡፡ ከኢራቅ፣ ሶሪያ፣ ሶማሊያ፣ ሩዋንዳ፣ ሊቢያ፣የመን እያልኩ ወደራሴው ጉድ ገባሁ፡፡ ለአንድ አፍታ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ያለቁበት ሰሞኑን የዓልም ሽልማት የተሸለመው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ታሰበኝ፡፡ ለመሆኑ ያ ጦርነት ዓላማው ምን ነበር? ማን ተጠቀመ? ለማን ተብሎ ያ ሁሉ ሕይወት አለፈ? አንዳች ምክነያት የለኝም ዝም ብዬ ለማይረባ አእምሮ የተሠጠ ትውልድ ጥፋት ከመሆኑ ውጭ፡፡

እድሜ ልኬን ያየሁትን ወደኋላ መቃኘቱ ይደክማል ብቻም ሳይሆን አይቻልም፡፡ አሁንስ ምን እየሆነ ነው ያለው የሚለወን እንኳን ማሰብ ከባድ ነው፡፡ አዝናለሁ፡፡ የበጎ አሳቢዎች በእግዚአብሔር አሳሰቢነት በሚመራ አእምሮ ሲመሩ የክፉ አሳቢዎች በተቃራኒው ጠላት ይመራሉ፡፡  ለማይረባ አእምሮ አንዴ ተላልፈህ ከተሰጠህ በኋላ ገዳይህን እያወደስህ ወዳጅህን ትገድላለህ፡፡ ለገዳይ እየሰገድህ ለአዳኝህ ታሴራለህ፡፡ በአጠቃላይ የጠላትህ ባሪያ ትሆናለህ! የክፉውን ድምጽ ትሰማለህ የሠላም ነገር እንደ እብድ ያደርግሀል፡፡ ዛሬ የሕዝብ ጠላቶች ትልልቅ ሰሚ አላቸው  በእነሱ የአስተሳሰብ ባርነት የያዙት በሚሊየን እየተቆጠረ ነው፡፡ ሌላው አዚም ተደርጎበት ዝም ብሏል፡፡ ሰሞኑን በኦሮሚያ የሆነው ሁሉ አንድን ከልጅነቱ ጀምሮ በጠላት ተቀጥሮ እየሰራ ያለን ግለሰብ ከመደገፍ አልፎ ወደማመለክ የተለወጠ ለማይረባ አእምሮ ተላልፎ የተሰጠ በገዳዮቹ አስተሳሰብ ባርነት ሥር የወደቀ ሊገድልና ሊዘርፍ ሊያጠፋም ለጥፋት ጥሪ አደባባይ ወጥቶ ግን ያሰበው ባለመሳካቱ እየተቆጨ አሁንም እዛው አስተሳሰብ ውስጥ ሲደነፋ እየታየ ነው፡፡ ክልሉን እንመራለን የሚሉት ይሄን ሁሉ ጥፋት እንዲደርስ የጥፋት አዋጅ የጠራውን ወንጀለኛ በሕግ ቁጥጥር ሥር ማድረግና ሌላውንም ከአስተሳሰብ ባርነቱ እንዲወጣ መልካም አስተሳሰብ እንዲኖረው ከማስተማር ይልቅ ጭራሽ ወንጀለኞችን እያወደሱ ራሱን ለመከላከለ የወጣውን ሌላውን እየከሰሱት ይገኛል፡፡ ችግሩ እንዲህ ነው፡፡ እንግዲህ በመንግስትነት ሥም ወንጀለኞችን አሰማርቶ ከኋላ ደጀን ሆኖ ሌላውን የሚያስገድልና የሚገድል ቡድን በአለበት ሌላው እጁን አጣጥፎ ዝም ሊለው ፈልጎ እንደሆነ እያየን ነው፡፡ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሺን ተወካይ የተባለ በናዝሬት አዳማ አሁን በወንጀለኛውና አሸባሪው ግለሰብ ጥሪ ለመግደልና ለመዝረፍ ወጥቶ ሌሎች ራሳቸውን ለመከላከል በወሰዱት እርምጃ ያልጠበቀው አደጋ ስለገጠመው ያንኑ የሽብር ጥሪን የተቀበለን ቡድን ሰብስቦ ጭራሽ መሳሪያ እናስታጥቃችኋለን ሲል ቃል ሲገባ ሰምተንዋል፡፡ እንግዲህ ለማይረባ አእምሮ ስትሰጥ እንዲህ ነው! ሌላው የሞት አዋጅ እየታወጀበት ዝም ብሎ የሚጠብቅ ይመስለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የቅሌትና የውርደት ዘመን - ፍቅር ይበልጣል

የሰሞኑ ችግር የጥፋት አዋጅ ከአወጀው ግለሰብ ወንጀለኛ በፊት ጀምሮ ሲታሰብበት እንደነበር ታዝበናል፡፡ ይህ ከመሆኑ በፊት በየቦታው ፎቶግራፍና መጻሕፍ እያቃጠሉ ሲደነፉ የነበሩ አእምሯቸው በጥላቻ የጨለሙትን ተመለክተን ነበር፡፡ ጉዳዩ በምን ሰበብ መጠነሰፊ የሆነ ጥፋት መጀመር እንደሚችሉ ሲያሴሩ ከርመው የወንጀለኛው አዋጅ ነጋሪ ከሌሎች ጋር በአቀዱት መልኩ መጠነሰፊው ጥፋት እንዲጀመር ነው የተደረገው፡፡ ሆኖም ፍጹም በአልጠበቁት ሁኔታ ሌላው ራሱን ለመከላከል እርምጃ ወሰደ፡፡ ሊገድል የወጣው ሞት ገጠመው፡፡ በባሌ፣ በአዳማ በሌሎችም ቦታ የሆነው ይሄ ነው፡፡ አዲስ አበባን በሚያህል የፌደራሉ ዋና መቀመጫና የ7ሚሊየኝ ሕዝብ ከተማ የአንድ ወንጀለኛን እንጠብቃለን በሚል በወንጀለኛው የአስተሳሰብ ባርነት በወደቁና ለጥፋት በተመረዙ ሲወረር ፖሊስ ተብዬ አንዳች መከላከል አላደረገም፡፡ እንዲህ እየታሰበና እየተሰራ ነው መሪ ነን የሚባለው፡፡ የኦሮሞ ፖለቲካ በምን ላይ እንደተመሰረተ ደጋግሜ ተናግሬያለሁ፡፡ አሁን እየለየለት ስለሆነ ሁሉም በራሱ ሲደርስ ይረዳዋል፡፡

ትናንት በአምቦ ወጣቶች ሲያሰሙት የነበረው ድምጽ ያው በአስተሳሰብ ባርነት የወደቀ ትውልድ መሆን እንጂ እውን የሚያውሩትን የሚያስቡበት አእምሮ ቢመለስላቸው እንዴት የሚያሳፍር ነው፡፡ አብይ ሀበሻ ነው ይላል የአምቦ ቄሮ! እንግዲህ ሀበሻ አደለህም ተብሎ እየተነገረው ስላደገ ራሱን ሀበሻ እንደ ሀበሻ አለማሰቡ ብቻም ሳይሆን ሌላውን በሀበሻነት ለመጥላት ትልቅ ገደል እንዲሆንለት ነው ጠላቶቹም የነገሩት እሱም የተቀበላቸው፡፡ ሀበሾኒ የሚቲለዋ ቃል ለአብዛኛው ዛሬ ላለው የኦሮሞ ወጣት ደሙ እየፈላና ጥርሱን ነክሶ የሚጠራት ናት፡፡ አዝናለሁ! እንግዲህ የአምቦ ቄሮ ከሸዋው አማራ በላይ ለሀረር ወይም ለቦረና በደምምም በአኗኗርም እንደማይቀረብ የዘመኑን ሳይንስ ሳይጠይቅ መረዳት በተቻለ ነበር፡፡ አምቦና አካባቢው ከጥንት ጀምሮ የሸዋ ነገስታት ቤተሰቦች መኖሪያ እንደነበርና ይሄም ሕዝብ የእነዚሁ ዘር እንደሆነ የታሪክ መረጃዎች ብቻም ሳይሆን ዛሬ ራሱ የሚኖረውን ማንነቱን ቢያስተውል በተረዳው ነበር፡፡ ይሄን ስል ኦሮሞን ለመከፋፈል የሉታል፡፡ ይሄ የእኔ አላማ አደለም፡፡ የአምቦ ኦሮሞ ግን ከቦረናና ሀረር ኦሮሞ ለሸዋ አማራ እንደሚዛመድ ስለማውቅ እንጂ፡፡ ያም ቢሆን ሀረርም ቦረናም ከአማራም ሆነ ከአምቦ መዛመዱን አሳምሬ አውቀዋለሁ፡፡ የዝምድናውን ቅርበት በአምቦው ኦሮሞና በሸዋው አማራ ይበልጣል ማለቴ እንጂ፡፡ በያድለን እንጂማ በምድር ላይ ልዩ ሕዝብ ነበርን፡፡ ሐበሻ የሚለው ደብልቅ ሕዝብ ማለት ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ከጥንት ጀምሮ የሚነገርልን ሰዎች በመልካቸው ቀለም የሚለዩባት ምድር (አበባ መልክ) ኢትዮጵያን ጨምሮ ዛሬ በሱዳን፣ ኤርትራ፣ ጂቡቲና ሱማሌ እና በከፊል የመንና ግብጽ ነው፡፡ በሰሜን አፍሪካ የተውረግ ነጀገድ የሚባው ሕዝብ ይመስለናል፡፡ ይሄ ሕዝብ በመልክ ብቻም ሳይሆን በሚያስደነግጥ ሁኔታ በባህሉም የምስለናል፡፡ ማስንቆና ክራር እየመታ በተውረግኛ ከመሆኑ በቀር ይሄ የአገሬ ዘፈን ነው ብለህ ለተወሰነ ጊዜ ከአደመጥህ በኋላ ቋንቋው ሌላ እንደሆነ ስትረዳ ነው የአገርህ ዘፈን እንዳልሆነ የምታውቀው፡፡

ሠላምንና ፍትህን በጋራ በአንድነት ሆነን ወደፊት ብዙ መሄድ ስንችል ይሄው 50 ዓመት የተጠጋ ጊዜ በሴረኞች የአስተሳሰብ ባርነት ወድቀን ዘመናችንን ሁሉ እሞትንና መከራው የማያባራ ሆኖብን ጠላቶቻችንን አፈር አይንካህ እያለን እንኖራለን፡፡ በየቀኑ ሴራ ይሸርባሉ  እነሱን እያወደስን  የታሪክና የመንፈሳዊ ወኔ ታላላቅ አባቶቻችንን እየረገምን ከቀን ወደቀን እዘቀጥን ፍጹም ማየት የተሳነው ሆነናል፡፡ ኦሮሞን ዛሬ ኢትዮጵያን የሠሩ እነ ጎበና ዳጬን የመሰሉት ጀግኖች አባቶችህ ናቸው ብትለው አይሰማህም፡፡ የሚሰማው ለዛሬ ባርነት የዳረጉትን በራሱ እድሜ አይኑ እያየ እየገደሉትና መከራ እያጸኑበት ያሉትን ነው፡፡ ለኦሮሞ ዛሬ ከጎበና ዳጬና ገበየሁ ጎራ ይልቅ እነ ተስፋዬ ገብረ አብ ይቀርቡታል ብቻም ሳይሆን ያመልካቸዋል፡፡ ሰሞኑን ለሽብር የጠራውን ወሮበላ ከእነጭርሱም ወደማምለክ እየቀረበ ነው፡፡ ሚኒሊክን መጥላት ብቻም ሳይሆን ሥሙ ሲጠራ ገና ይበረግጋል፡፡ እነዚህ የቀደሙ አባቶች ግን ለዝህ ዛሬ በኦሮሞነት ራሱን ለባርነት በጠላቶቹ እጅ የሰጠን ትውልድ ቀና ብሉ ሊኮራበትና በዓልም ፊት ሳይቀር የሚመካበት ትልቅ ውርስን አውርሰውት ነበር፡፡ የሚኒሊክ ታሪክ የኦሮሞ አባቶች የመሪነት ብቃት የታየበት ታላቅ ታሪክ ነበር፡፡ ዛሬ በተራ ወሮበላ አስተሳሰብ የወደቀው ትውልድ ይሄ እስኪገለጥለትና አባቶቹን ከልቡ በመንፈስ ይቀርታ እስከሚጠይቅ ድረስ ውድቀቱ ይቀጥላል፡፡ ይሄን ስል ብዙዎች በማፌዝ እንደሚስቁ አውቃለሁ፡፡ በዛው ልክ ግን የተናገርኩት እንደሚሆንም አውቃለሁ፡፡ ትውልድን ማከም ያስፈልጋል፡፡ አንድም ሀኪም ግን የለም! ይሄን መሰል ጉዳይ በደንብ ቢያስተውል ብዬ ለዐመታት ስናገር ነበር፡፡ ችግሩ በባርነት የወደቀንና ለማይረባ አእምሮ የተሰጠን እንዴት እንዲያስተውል ማድረግ ይቻላል?

ተጨማሪ ያንብቡ:  ህገ-ፓርቲ/ ኢህአዴግ  ህገ-ህዝብ አይደለም

አምቦ ከመጀመሪያው ጀምሮ የሁሉም ችግሮች ሰለባ ነው፡፡ በብዙ መልኩ ጠላቶቹን ሲፋለም ነበር፡፡ ሆኖም እንደትናንቱ በብዙ ባለማስተዋሉ ሁሌም የሌሎች መጠቀሚያ እየሆነ እናየዋለን፡፡ እኔ በአብይ ደስ ካልተሰኙት ሰው ነኝ ሆኖም ግን የአምቦዎቹ የትላንቱ ሁኔታ ለማን እንደጠቀመ ሳስብ አዝናለሁ ማስተዋል ባለመቻላቸው፡፡ አሁንም እላለሁ አምቦ፣ በአጠቃላይ የምዕራብ ሸዋ ኦሮሞ አስተውል በብዙ ነገር መጠቀሚያ እየሆንክ መሆኑን፡፡ ዛሬ አብይን ሐበሻ ብለህ ስድብ እስክታደርገው ድረስ ማንነትህን ያስጣሉህን ለአፍታ ቆም ብለህ ወደኋላ እስከ 1983 ከዚያም ዘለግ አድርገህ ተመልከት፡፡ በደም ከሆነ እርግጥ ነው አብይ ሀበሻ ነው! አምቦ ግን ከሀበሻነትም የሀበሻ መሪዎች ልጆች ናቸው!ይሄን አውቃለሁ!  ዛሬ ጥቁር አንጪኒ ምናምን እያልክ የምትጠራቸውን ቦታዎች የእነማን ምድር ነበር? ግንደ በረትስ? ዛሬ ኦሮምኛ ስለተናገርክ አደለም! ኦሮምኛ መናገር ስህትት ነው እያልኩ አደለም፡፡ ከቋንቋ በላያ ደምህ ምስክር ይሁንህ እያልኩ እንጂ፡፡ ይህ ሲባል አሁንም ከሌላው የኦሮሞም ሆነ ሌላው ወገንህ ለማራቅ አደለም! ግን በእርግጥም ሥርህ ያለው በቋንቋ የተለያያችሁት ጉራጌውና የሸዋ አማራው እንደምትቀርብ ግን አልጠራጠርም፡፡ ያም ሆኖ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የአንድ አባት ልጆች እንደሆኑ አውቃሉ፡፡ በረና ኢትዮጵያዊ አባት ሲኖረው ጎረቤቱ ኬንያ (ከማሳይ ውጭ) ነገዱ ሌላ ነው፡፡ ሱማሌ፣ አፋር፣ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ሌሎችም በርካታ በማያሻማ ሁኔታ ከአንድ እንደተወለዱ ሳይንስ ዛሬ ምስክር ነው፡፡ ከማዳካስካር መጣ ከባህር ወጣ የሚል መረጃ የለንም በሳይነሱ፡፡ ለመሆኑ ባህሩስ የት አለና? ታሪኩን የጻፉት ሰው ቃላቸው ተንሸዋሮ እንጂ ዛሬ እንደሚነገረው እንዳልሆንም አውቃሉ፡፡ ለታሪክ ጸሀፊው ከባህር ብለውት የነበረው የገላናን ወንዝ ወይም የአባያን ሀይቅ ከአልሆነ በቀር፡፡

አእምሮአችሁ እስካሁን በሰላም ያለ አማራ ሆንክ ኦሮሞ እስኪ ትውልድን ለማነጽ ሥራ፡፡ በሱማሌ ምሁር ወንድሞቻችን እጀግ የሚያስደስት ማስተዋል እናያለን፡፡ ጠላታቸውን በደንብ የለዩትና ትኩረታቸው ወደነበረ ማንነታቸው ላይ እንደሆነ እያየን ነው፡፡ በብሔር ነጻነት ሥም ብዙ ወንድሞቻቸው ሲረግፉና መከራ ሲቀበሉ አይተው ትምረውበታል፡፡ ይሄው በኦሮሞም ሆኖ ነበር፡፡ ግን ለማስተዋል አልሆንም

ተጨማሪ ያንብቡ:  አጭር ቅኝት: የኦሮሙማ አፈግፍጉ ሴራ እስከ ግማሽ ነጻ መውጣትና ለድርድር እስከ መሞዳሞድ ድረስ (እውነቱ ቢሆን)

በሌላ በኩል በየቦታው የዚሁ አይነት ችግር አለ፡፡ አንዱ የአማራና የትግራይ ክልል የሚባሉት ናቸው፡፡ የአማራ ክልል ተወላጆች የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች የሄዱበትን መንገድ እየተከተሉ እንደሆነና አሁን ማሰብ ያልቻለ ለማይረባ አእአምሮ የተሰጠው እየበዛ ይመስላል፡፡ ሴረኞች በሚፈጥሩለት ጉዳይ ማስተዋል ሳይችል ራሱን ለጥፋት እየዳረገ ነው፡፡ ለብዙ አማራ ወያኔ የፈጠረችው የክልል መሬት ጉዳይ ትልቅ ጉዳዩ ሆኖ እውነትን ማስተዋል እንዲሳነው ተጋርዶበታል፡፡ ፍትህና ሠላም መስፈን ላይ ማንም እየሰበም እየሰራም አደለም፡፡ ዛሬ ኦሮሞ ነፍጠኛን እንዲህ እናደርግልሀለን ሲሉት እንደሚፈነድቀው አማራው ወያኔን እንዲህ እናደርጋለን የሚለው ነው መዘወሪያው፡፡ ጉዳዮን ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ የራያና ወልቀይትን ጉዳይ ብናነሳ እውነቱ ከአማራነትና ከትግራይነት ጋር የተያያዘ ሳይሆን ወያኔ በምታሴረው በወያኔ አድገው ዛሬ የወያኔ ጠላት በሚመስሉ ግን በተግባርም በባህሪም የማይለዩ የክልሉ መሪ ነን የሚሉት የሚቆምሩበት ሆኖ ይሰማኛል፡፡ በወልቀይት ትግሬም አማራም ዛሬ ብቻ ሳይሆን ለዘመናት አብሮ ሲኖር ነበር፡፡ አሁን ጥያቄው ስለፍትህና ሠላም ሳይሆን ስለቦታ ባለቤትነት ነው፡፡  ማንም ከየትም ያመጣው ቦታ የለም ቦታው ላይ የሚኖረው ሕዝብ ነው ባለቤቱ፡፡ በአማራነት ወይም በትግሬነት ቦታን ሸንሽና የሚቆምሩት ወያኔና እስከዛሬም በለውጥ ሥም ተለውጠናል እያሉ በዛው በወያኔ ሕግና ሥርዓት የሚቆምሩ ለዘመናት በወንጀልና በዝርፊያ የኖሩ መሪዎች ናቸው፡፡ አንድን ቦታ የእኔ ነው የሚል የወሮበላ ስብስብ አስተሳሰብ የት እንደሚወስድ ግልጽ ነው፡፡ የችግሩ ሁሉ ቁልፍ እነሱ ሕገ-መንግስት የሚሉት ነው ስንል ይሄን አደገኛ አስተሳሰብ የወለደ እንደሆነ ስለምናውቅ ነው፡፡ አገር እንደአገር እንድትቀጥል ከተፈለገ አሁንም እናሳስባልን የአስተዳደር ወሰኖች በፍጹም  ከዘርና ቋንቋ ጋር በጅምላ የተዋቀሩበት መዋቅር መፍረስ አለበት፡፡ በደርግ ጊዜ የነበረው የክፍለአገራት አስተዳደር በተወሰነ መልኩ ብቻ ማሻሻያ ቢደረግበት ጥሩ አክላለል ነበር፡፡ የሁለት ቋንቋ ተናጋሪዎች በአሉበት የወሰን አካባቢዎች እንደውም በልዩ ሁኔታ መስተጋብሩን በሚፈጥር መልኩ የአስተዳደር ወሰን ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ይህን ግን ማን ሊያስብ ይችላል?

ከሕግና ሥርዓት ውጭ ማንም እየተነሳ ይሄ የእኔ ቦታ ነው ቢል አይሆንም፡፡ አሁን በቅርቡ ሲዳማና ወላይታም ራሳችንን ችለን ክልል እንሁን የሚል ጥያቄ ተነስቷል፡፡ የክልል እንሁን ጥያቄው የሚነሳው ለመዝረፍና ሌላውን ለማግለል ነው፡፡ ዲሞክራሲ ማለት ምን ማለት እንደሆነ የማይገባው ስለ ዲሞክራሲ ዋና ይሆናል፡፡ መብት ማለት የማይገባው ቀማኛና ነብሰ ገዳይ ዋና የነጻነትና መብት ተከራካሪ ይሆናል፡፡ የማይረባ አእምሮ በበዛበት ይሄ ሊሆን ግድ ነው! እንግዲህ ዲሞክራሲ የሚባለው በሕግና ሥርዓት ሕዝብ በሚወስነው መንግስት መመስረተ ነው፡፡ ሲዳማ ክልል እሆናለሁ የሚለው አዋሳን ታሳቢ አድርጎ ነው፡፡ አዋሳ ሕግ በሆነ የሕዝብ ድምጽ ቢወሰን ሲዳማ አይሆንም፡፡ በጉልበትና በሕግ አልበኝነት ከአልሆነ፡፡ ሌሎች ብዙ ቦታዎችም ይሄው ነው የሚኖረው እውነት፡፡ የእያንዳንዱ ዜጋ መብት ከታበ ሁሉም የወሳኝነት መብት እንዳለው መቀበል ግድ ይላል፡፡ ይሄን ግን ማን ያደርገዋል?

በአጠቃላይ ነገሮች አብረን ልንኖር በምንችልበት መልኩ ሳይሆን ጠላቶቻችን በሰሩልን ሴራ ተጠልፈን ወደለየለት የእርስ በእርስ እልቂት እንዲሄድ እየሰሩ ያሉትን ገብቶን ከወዲሁ እርምጃ መውሰድ ከአልቻልን የተፈራው መምጣቱ አይቀርም፡፡ ሁሉም እራሱን ይጠይቅ ምን እያደረገና ምን እያሰበ እንደሆነ? ለሌች ከፈጠሩለት የአስተሳሰብ ባርነት ወጥቶ በራሱ ቆም ብሎ ሊያስተውል ይገባል፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር አእምሮአችንን ከፍቶ እንድናስተውል ይርዳን! አሜን!

ለሀሐኀሐሀልሀለለ

ሰርፀ ደስታ

4 Comments

  1. አንተ ወገን ታላቅ አስተማሪ ነህ:: ሳልረዳህ ከዚህ በፊት ተቃውሜህም ነበር:: ይቅር በለኝ:: ስለኦሮሞ ፅንፈኞች ጉዳይ ብዙ ስትዘረዝር እኔ የእነሱን ፀረ ኢትዮጵያዊነት ደላላነት ሳልረዳህ ብዙ አስተያየት ፅፌም ነበር:: ዛሬ ጎራው ለይቷል:: ፀረ ኢትዮጵያ በህውሀትና ጃዋር መንጋ ጋር ተሰልፈዋል:: እኛ ኢትዮጵያውያን አሸናፊዎች ነን:: እኔ ሸዋን ከጫፍ እስከጫፍ አውቃለሁ:: በኢትዮጵያዊነቱ ከመጡ ለማምከን ወደሗላ አይመለስም::

  2. You get the verse you mentioned on Romans 1:28! But, that includes your ‘METETENYA’ qes na ager meri tebiyewoch since the founding of this cursed empire that created at the cost of Oromo blood, life and resource, and still continued to do so. “……NO MATTER HOW LONG THE NIGHT IS, THE DAY SHALL FOLLOW IT!!!!………”

  3. በእንዳንተ አይነቶቹ ፍጹም ኦሮሞ ጠል የምንልክ አምላኪዎች የተደራጁና ገንዘብ የተከፈላቸው ነብሰ ገዳዮች፣ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣውን ህዝብና ተራውን መንገደኛ በጥይት፣ በድንጋይና በዱላ በመግደልና በማቁሰል የፈጠሩትን ሽብር የሃይማኖትና የዘር ጦርነት ለማንሳት ሞከሩ። ጠቅላላው የሃበሻ ሜዲያና አፍ ያለው የፌስቡክ ጦረኛ አማራ ሁሉ ባንድ ቃል ሌት ተቀን በኦሮሞ ህዝብ ላይ መጠነ ሰፊና ልቅ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ እና የጦርነት ከበሮ ይጎስማሉ። የሩዋንዳን አይነት እልቂት ለማየት ሳትታክቱ እየሠራላችሁ በሚትሠሩት ወንጀል ሌላውን ትከሳላችሁ! ምን ለማትረፍ እንዳሰባችሁ ግራ ያጋባል። ካላበዳችሁ በቀር ከኢህአፓ በወረሳችሁት ነጭ ሽብር/ቀይ ሽብር የኦሮሞን ህዝብ ወደ ባርነት እንመልሳለን የሚለው ህልማችሁ ከቶውንም ዕውን ሊሆን እንደማይችል ማወቅ ነበረባችሁ!

  4. እባጫላ በመጀመሪይ እንደ ሰው አስብ:: ተጨፍጭፈው መንግስት ተብዬዎች ያልቆሙለትን ምስኪን ህዝብ አንተ ፈርድ አልፈረድ እግዚአብሄር ግን ያያል ይፈርዳል:: ምንድን ነው የታሰበው ኢስላሚክ ኦሮሚያ? ለምን ግልፅ ሆናችሁ አትወጡም:: ጃዋር እጅግ ብዙ ሚሊዮን ህዝብ ያሸንፋል::? ድንቄም የፖለቲካ ሳይንቲስት:: he is a terrorist. አሜሪካ ድግሞ ምን እንደሚያደግ ታውቃለህ:: ይህን ወንጀለኛ ኢትዮጵያውይን በመተባብር ለፍርድ ማቅረብ ይኖርባቸውል:: የጊዜ ጉዳይ ይህ ያልስለጠነ መንጋ ስርአት ይይዛል::

Comments are closed.

Share