ይድረስ ለኢትዮጵያ መንግስትእንደ አንድ ዜጋ እጠይቃለሁ !! – ታማኝ በየነ

እኔ በደረሰኝ መረጃ ከትናንት ጀምሮ በወሎ ከሚሴና በሽዋ አጣዬ በደረሰ ግጭት ንጹሃን ዜጎች እዬሞቱ ነው፡፡

ለመሆኑ ሰላም የነበር አካባቢ በአንዴ ወደ ጦርነት ቀጠና እንዴት ሊለወጥ ቻለ?

የእማራ ክልል መንግስት በእካባቢው የታጠቁ ሃይሎች ሲገቡና ሲወጡ አላየም ነበር?

የኦሮሚያ መንግስትስ ከራሱ ሃይል ውጭ የታጠቀ ሃይል ሲያይ ማን ነህ ብሎ አይጠይቅም ወይ?

ኦዴፓና አዴፓ በእርግጥ እየተነጋገራችሁ ነው የምትሰሩት? ከሆነስ የአንድ ንጹህ ዜጋ ህይዎት ከማለፉ በፊት ለምን ግጭቱን ተነጋግራችሁ አትፈቱትም ነበር?

የፌደራል መንግስት እንደ እኛ ውጭ እንዳለነው እኩል ነው ግጭቱን የሰማው?

በአጠቃላይ ለተፈጠረው ቀውስ ከፌደራል መንግስቱና ከሁለቱ የክልል መንግስታት ውጭ በዚህ ጉዳይ ተጠያቂ የለም

በአጠቃላይ በየቦታው የሚታዩት ግጭቶች ነገን አስፈሪ እያደረጉት ነው፡፡ መንግስት ሁሉንም በእኩል አይን አይቶ በጥፋተኛው ላይ የማያዳግም እርምጃ ካልወሰደ ወደ ፈራነው እልቂት እንደምንገባ ለመናገር ትንቢት ተናጋሪ መሆን አያስፈልግም፡፡

ገና በጠዋት የአብዮታዊ ዲሞክራሲ የዘረ ፖለቲካ መሰረት ሲጣል አይበጀንም ብዬ አደባባይ የወጣሁት የዘረ ፖለቲካ መጨረሻው ዛሬ የምናየው በእጅጉ በከፋ ሁኔታ ነገ የምንጋፈጠው መሆኑን በመረዳት ነበር።

ዛሬ የዘር ፖለቲካ በድርስ ዘዋሪ አፍላ ጎረምሳዎችም እድሜ በተጫናቸው በችግሩ አምጪ አዛውንቶችም በአስፈሪ ሁኔታ እየተራገበ እሳቱ ደግሞ በየቀኑ አገር የቆመችበትን ምሶሶ እየለበለበ፤ የዜጎችን ነፍስ እየቀጠፈ ነው።

አስገራሚው ነገር በተመሳሳይ ወቅት ያልተማርንበት የሩዋንዳ የዘር ፍጅት መታሰቢያ ለ25ኛ ጊዜ በዓለም መድረክ እየታወሰ ነው። እኛ እንደሌሎቹ ካለፈው መማሩ ቢሳነን ዛሬ እየሆነ ባለው በራሳችን ውድቀት ለመማር እንኳን ዝግጁ የሆንን አንመስልም።

እርግጥ ነው መንግስት በቅርቡ የአገራችን መሰረታዊ ችግር የምንከተለው የብሔር ፖለቲካ ነው ሲል የደረሰበትን ድምዳሜ በግልፅ ማሳወቁ የተስፋ ምልክት ሆኖ ሊታይ ይችላል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዶ/ር አብይ አህመድ  በአዲስ አበባ የለገሀር የተቀናጀ መንደር ግንባታ ፕሮጅክትን መርቀው በከፈቱበት ወቅት ያደረጉት ንግግር

ይህ በራሱ ግን ከዛሬው እልቂት የሚታደገን አይደለምና የፌደራል መንግስቱም ሆነ የሁለቱ ክልል መንግስታት በአፋጣኝ ይህን ሁኔታ ቀልብሰው ከዚህ በላይ ሌላ ጉዳት እንዳይደርስ እንዲከላከሉ ይህንን ሰይጣናዊ ተግባር የሚፈፅሙ አካላትንም በህግ ተጠያቂ እንዲያደርግ እንደ አንድ ዜጋ ለመጠየቅ እወዳለህ።

አርቲስት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ

7 Comments

  1. ወነድም ታማኝ፣ እንደ ስምህ ታማኝ ለምሆን፤
    እውነትነ ደጋግመህ ፈልግ፣
    እውንትን አግኝ።
    እውነትን ደጋግመህ ስማ፣
    እውንትን ተናግር።
    እውነትን ደጋግመህ አንብብ፣
    እውነትን ፃፍ።
    እውነትን ደጋግመህ እይ፣
    እውንትን አሳይ።
    እውነትን ደጋግመህ አቅድ፣
    እውነትን ስራ።
    እውነተን ደጋግመህ ተመኝ፣
    እውነትን ተንቢይ።
    ያለ በለበዝያ ታማኝ መሆንህ ቀርቶ -ታማኝ ትሆናልህ።

  2. Tamagn, this is just an atrocity by criminal gangs. Do not paint it as if it is between the peoples of Amara and Oromo. That is only playing the card of the perpetrators. It will be handled – Teregaga!

  3. ሁሉም ልብ ሊለው የሚገባ ጉዳይ፦አንድ ወዳጄ አሁን እጣዬ አክባቢ ይገኛል። እርሱ በሥልክ እንደነገረኝ ከሆነ የዘር ግጭቱ በመንግሥት የተደገፈ ነው። ለምሣሌ ገበሬው ራሱን ለመከላከል የቆፈረውን ምሽግ ፌደራሎች እያስለቀቁ ለኦነግ እንደሚሰጡና ህዝቡ እንዲያልቅ እየተደረገ መሆኑን ከሥፍራው በሥልክ የሚናገሩ አሉ።ያማራው ክልልም ምን እንደነካው አይታወቅም ዕልቂቱን ማስቄም አልቻለም። በፌደራል ተብየው በኦህዲድ የሚታዘዘው ጦር ሳይከለከል አቀረም። ለማንኛውም ለዚህ የንጹሓን ፍጅት ዋናሽተጠያቂ የመንግሥትን ሥልጣን ያለተቀናቃኝ የጨበጠው ኦህዴድና አባቱ አነር ማለቴ ኦነግ መሆናቸው ግልጽ ነው።

  4. When Queros get few military rifle weapons Queros right away becomes OLF fighter, when Quero runs out of bullets they return back to being Quero doing their crimes with just knives . Queros operate as a reserve for OLF’s military. Queros got intelligence by sending spies, For example they knew Saturday night was where most were asleep or intoxicated so they picked that time to attack.

    Same person can be Quero or OLF fighter in the same day depending on what the person is armed with.Maybe some of the victim’s are Jawar’s own blood cousins or even blood brothers and sisters that are victimized.

    Quero jumps from one tree to another at night in all corners of Oromia and neighboring towns including Addis Ababa , when Quero get the chance they attack . The current attack is done because Abebe Gellaw claimed Jawar’s father is Menze Amara from northern Shewa , Quero wanted to change the demography of the area so they picked up rifles.Quero and OLF are one and the same. Queros are reserve while those that showed up from Eritrea “OLF fighters” are active duty in OLF’s military. Queros displaced Amara from Northern Shewa , residents are fleeing the areas with many vowing not to return because Federal is favoring the attackers not the victims.

  5. ዶክተር ዐቢይ አህመድ ይህችን ደባል ተባራሪ እስኪ አይንዎን ለምግለጥ ይረዳዎታልና ይመልከቷት፤ወርቅነህ ገበየሁ ስንት ነገር ሊያደርግ እንደሚችል አሳሰብን አማካሪዎት ላይ እንደያማካኙ።እባክዎት በተለይ የኢሃድግ ካድሬ አባላት ስለመደመር የአንድ ቀን ተሃድሶ ሥልጠና ካልተሰጣቸው ሕዝብን ማጋደል ይቀጥላሉና በፍጥነት ርምጃ ሊወስዱበት ይገባል።
    የጠቅላይ ሚኒስቴር ኃላፊነትዎን ለመወጣት እግርዎን ከኢትዮጵያ ባወጡ ቁጥር ምን ያህል ተንኮለኞችን እንደተሸከሙ ሊገነዘቡት እንዳልቻሉ ከጠንካራው የኢሣት ሚዲያ ትንተና እንኳን እንዴት ለመገንዘብ አይችሉም?ወንድሜ ተወልደ በየነ እንደተነተነው እስኪ እኔ ደግሞ በቀላሉ ለመታየት በሚችል ስሌት ከምሥጋና ጋር ላቅርበው፤
    እርስዎ ኢትዮጵያውያንን ለማግኘት-
    አሜሪካ ሲሄዱ የቡራዩን ሕዝብ ለማጋደል ተንኮሎቹን ፈፅመው ስንት ሰው አጋደሉ፤
    ኤርትራ ” ሻሸመኔ
    ኤምሬትስ ” የጨለንቆ
    ግብፅ ” የጎንደር
    ኬንያ ” ሞያሌ
    ስዊዝ ” ድሬድዋ
    ሩዋንዳ ” የአጣዮ
    ኢትዮጵያ ” የሱማሌና ለጋጣፎ ግድያ እንደነበር ሁሉ ደግሞ መቼ እና የት ሲሄዱ ነው የት እና ለምን ሌሎች ዜጎቻችን ደግሞ ይገደላሉ?ስለዚህ ያለምንም ይሉኝታ(ይሉኝታ ቢሶች ናቸው)ፋሺሽ-ወያኔዎች የተሃድሶ ሥልጠና በፍጥነት መግባት አለባቸው።

  6. Dear Tamang

    I share your appeals for peace and mutual understanding among the Ethiopian peoples. Nobody deserves a death which is caused by violence. The human dignity is inviolable.

    But what do you mean, when you say the causes of the political conflicts in Ethiopia is the politics of ethnicity (YEZER POLITIKA)? Is it new for you? Since the formation of the new Ethiopian state about 140 years ago, we have  been experiencing and suffering under the worst ethnic politics which are full of psychological war on different cultures and languages, degradation of human values and latent discrimination. Now it is time to solve all these problems peacefully and build a new Ethiopia with new visions, so that human dignity will not be violated again.

    The worst ethnic politicans are those who are working day and night against the democratic rights of the differet nations in Ethiopia. They have been using always derogatory terminologies in order to undermine the demands of the Oromo, the Somali, the Afar, the Sidama and all other nations. Such efforts are futile. If we will not solve our problems step by step, we can jeopardize our common existence. Our other main problem is the malicious politics of the hatemongers and greedy politicians.

    Let us stand together hand in hand for the truth  mutual respect and mutual understanding!

  7. ታማኝ!! ኣንተና ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ የሰረቃችሁትን ገንዘብ ካልመለሳችሁ፤ እንደ ውሻ፤ እንደ ቁራ፤ እንደ ጧት ወፍ እንደ ለማኝ ስትጮሁ ብትኖሩ የሚያምናችሁ ሰው የለም። ሚልዮን ጊዜ ሌቦች!!!

Comments are closed.

Share