የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሁሉንም አምባሳደሮች ጠራ

ለአምባሳደሮቹ ጥሪ የተደረገው በተለያዩ ወቅታዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ላይ ገለፃ ሊደረግ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምንጮች የገለጹ ሲሆን አምባሳደሮቹ በቀጣዩ ሳምንት ወደ ሀገር ቤት ይሄዳሉ ተብሏል::
https://www.youtube.com/watch?v=ncwpPfdrV3E&t=991s
የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ከ100 በላይ የማረሚያ ቤት ሃላፊዎችን ከሥራ ማንሳቱን አስታውቋል፡፡ ርምጃው የተወሰደው በታራሚዎች ላይ ሲፈጸሙ የቆዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመከላከል ነው፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ጀማል አባሶ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በየማረሚያ ቤቶች በተደረገ ክትትል ሙሉ ለሙሉ ባይባልም ባሁኑ ጊዜ ቀደም ሲል የነበሩ ችግሮች መቀረፋቸውን ገልፀዋል፡፡ አራት የፌደራል ማረሚያ ቤቶች በአዲስ መልክ እየተገነቡ መሆኑን የተናገሩት ሃላፊው በአዲስ አበባ የሚገነባው አዲሱ ማረሚያ ቤት 96 በመቶ እንደተጠናቀቀም አስረድተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የ35 ሀገራት አምባሳደሮች የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርን ጠርተው አነጋገሩ
Share