ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ የሳዑዲ ኢምባሲ የፊታችን አርብ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ

ታላቅ ሀገራዊ የተቃውሞ ጥሪ!

ከወገኖቻችን ጐን በመቆም ብሄራዊ ክብራችንን እናስመልሳለን

ሰሞኑን የሳውዲ አረቢያ መንግሥት በኢትዮጵያዊያን ላይ እየፈፀመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመቃወም ሰማያዊ ፓርቲ ታላቅ የተቃውሞ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

በመሆኑም በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን ኢሰብዓዊ ድርጊት ለማስቆምና የዜጐችን ህይወት ለመታደግ እንዲሁም ዜጐቻችን በአፋጣኝ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ መንግሥት እንዲያመቻች እና በተጨማሪም በዜጐቻችን ላይ ለደረሰው የአካል መጉደል፣ እንግልት፣ ድብደባ፣ አስገድዶ መድፈርና የህይወት መጥፋት ኃላፊነቱን የሚወስዱ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ፤ ለተጐዱ ወገኖቻችንና ቤተሰቦቻቸውም አስፈላጊው ካሳ እንዲደረግላቸው ፓርቲያችን አበክሮ እያሳሰበ፤ የብሄራዊ ክብርና የወገኖች ስቃይ የሚያሳስባቸው አካላት በሙሉ በዚህ ታላቅ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
የተቃውሞ እንቅስቃሴ አፈፃፀም፡-
1. በዜጐቻችን ላይ የአካል መጉደል፣ እንግልት፣ ድብደባ፣ አስገድዶ መድፈርና የህይወት መጥፋት ያደረሰው የሳውዲ አረቢያ መንግሥት ኢምባሲ በሚገኝበት ቦታ አርብ ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት ጀምሮ የሚደረግ የተቃውሞ ሰልፍ፣
2. ከአርብ ጠዋት ጀምሮ እስከ እሁድ ማታ ድረስ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሀዘን ልብስ (ጥቁር ልብስ) በመልበስ በግፍ ለሞቱና ለተንገላቱ ወገኖቻችን ሀዘናችንን መግለፅ፣
3. የእምነት ተቋማት አርብ በመስጊድ በጁምአ ሥነ ሥርዓት ላይ እና ቅዳሜና እሁድ በአብያተ ክርስቲያናት የፀሎት ሥነ ሥርዓቶች ላይ ወገኖቻችንን በፀሎት እንዲታሰቡ፣
4. ቅዳሜ በሚደረገው የኢትዮጵያና የናይጄሪያ የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ተጫዋቾቻችን ጥቁር ሪቫን በክንዶቻቸው ላይ አጥልቀው እንዲጫወቱ፣ እንዲሁም መላው ደጋፊ ጥቁር ጨርቆችን በመያዝ ወይም ልብስ በመልበስ ሀዘኑንና ቁጭቱን እንዲገልፅ፣

በፓርቲው የተወሰነ በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ሲቪክ ተቋማት፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ዓለም አቅፍ ማኅበረሰቡ በአጠቃላይ መላው ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ወዳጆች በጠራነው የተቃውሞ ሰልፍና እንቅስቃሴዎች ላይ በመገኘት ከግፉአን ወገኖቻችን ጐን መቆሙን እንዲያረጋግጥ በአፅንኦት እንጠይቃለን፡፡
የወገኖቻችን ሰቆቃ እስኪያበቃ በፅናት እንታገላለን!!!

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአ.አ ከንቲባ ጽ/ቤት ጠባቂ ፖሊሶች ተታኮሱ

ሰማያዊ ፓርቲ

6 Comments

  1. waw Semayawi wnetem selamawi ,,Egizeabher Amelak be serachehu hulu kedmo yigegn ye wegenochachen eniba yabes le enaochachen metsenanat yehun ,, selam le emye Ethiopia

  2. Good job blue party leaders,forget about this tplf mafia groups,the don’t have ethiopian peoples legitmacy,so go forward blue party say something for this uncivilized arabs what they did for our brothers and sisters,Ethiopia will never forget what they did for our beloved people,hey you arabs bastard shermuta,one day you will pay the price,we send u hell,ethiopia never forget this,never,never ever forget,,,i told u,never visit and live in ethiopia again,if we see any arab in our country,we will show u,who we are,,,finally we will tell u this again,Ethiopia never forget what u did for our brother and sisters,you will pay the price,go ethiopia forward,,,,,jesus is lord,selam

  3. I wonder the initiative to have such wonderful march against the horrific, barbarian devilish acts have been performed by the Saudi civilians and police. The mass massacre and rape for many is also aggravated to many towns in Saudi. Sorry for the reluctant responses to the Ethiopian government for such inhuman acts. I appreciate the opposition parties to take the initiative to loud your voices to the world for such crime on Ethiopian immigrants. May the almighty God rest their Soul in Heaven who lost their lives in the desert. Ethiopian people, we lost our dignity, proud and heroic heritage of our fathers. We have to restore and re-establesh our dignity and national feeling throughout our country. Long live to Ethiopia and the Ethiopian people.

  4. አወ ብራቮ ሰማያዊ ፓርቲ ይሄን ነው የምንገልገው ተግባር ያስፈልገናል ዘላለም በወሬ መወሰን የለብንም እንደ አንድነት ፓርቴ መግለጫ ማንጎድጎድ ንግግር ማብዛት መፍትሄ አያመጣልንም በግልጽ ተቃውሞ ማሰማት አለብን የሳውዲ ኢንባሲ በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅና ለተጎዱት ወንድሞቻችን ዋጋ መክፈል አለበት ። ወያኔ እንድሆነ አይዛዋችሁ በላዋቸው ነው የሚለው ምንም እስካሁን ጠንከር ያለ መግለጫ እንኮዋን አላወጣም ከነዚህ የባንዳ ጥርቅሞች ምንም መጠበቅ የለብንም።

  5. United we can stop the suffering of not only in Saudi Arabia but also in the entire countries of Middle East with no time.
    Long Live Blue Party!!!
    God bless Ethiopia and protect our people in Saudi Arabia and Middle East.

Comments are closed.

Share