አረና ለአንድነት የውህደት ጥያቄ አቀረበ

(በዘሪሁን ሙሉጌታ/ሰንደቅ ጋዜጣ) በትግራይ ክልል እየተንቀሳቀሰ ያለውና በቅርቡም ጠቅላላ ጉባኤ በማካሄድ ነባር አመራሮቹን በአዳዲስ የተካው የአረና ትግራይ በዲሞክራሲና በሉአላዊነት (አረና) ፓርቲ ለአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የውህደት ጥያቄ ማቅረቡ ታወቀ።
ፓርቲው በቅርቡ መቀሌ ላይ ባካሄደው ጉባኤ ዋነኛ አጀንዳ የነበረው ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር መዋሃድን እንደ ቀዳሚ አጀንዳ በማንሳት በጉዳዩም ላይ በመወያየት ውሳኔ ማሳለፉ አይዘነጋም። በዚሁ መነሻ ቀደም ሲል መድረክ ከግንባር አደረጃጀት በላቀ መንገድ እንዲዋሃድ ከሚያደርገው ግፊት በተጨማሪ ከአንድነት ፓርቲ ጋር ለማዋሃድ በግልፅ ጥያቄ ማቅረቡ ታውቋል።
ፓርቲው የውህደት ጥያቄውን ለአንድነት ማቅረቡን ያረጋገጡት የአረና ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ብርሃኑ በረኸ ናቸው። እንደሳቸውም አጭር ገለፃ ፓርቲው በቅርቡ ባካሄደው ጉባኤ መነሻ በማድረግ የውህደት ጥቄው ቀርቧል፤ መልሱንም እየተጠባበቀ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የአንድነት ፓርቲ የጽ/ቤት ጉዳይ ኃላፊ አቶ አስራት ጣሴ በበኩላቸው አረና ለአንድነት ፓርቲ የውህደት ጥያቄ ማቅረቡን አረጋግጠዋል። ም/ቤቱ በጉዳዩ ላይ እንደሚወያይበት ታውቋል። በቅርቡ የአንድነት ፓርቲ በሚያካሂደው “ስትራቴጂካዊ ጠቅላላ ጉባኤ” ጉዳዩ ቀርቦ ውሳኔ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ አንድነትና መኢአድም በተመሳሳይ ለመዋሃድ አስር አባላት ያሉበት ኮሚቴ አቋቁመው እየመከሩ መሆኑም አይዘነጋም።n

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጋምቤላን መሬት የተቀራመተው የህንዱ ካራቱሪ የንግድ ባንክን 62 ሚሊዮን ብር ዕዳን መክፈል ተስኖታል

7 Comments

  1. wellabu G you are one of left over in the jangle when you going to be a real human thinking I think in your life you never been smart student becaus your point is zero be sevilaized be humane get outvfrom dedebit thinking we will help you

  2. Good news, ethnic poletics is becoming out dated. But it should be done with atmost caution. You know what I mean. Hope blue party and obco will join them soon.

  3. United we are stronger and indomitable, divide we are stronger and vulnerable to the worst dictatorial, divisive and ethnocentric regime. Ethiopian Opposition Political Parties must unite and establish one stronger opposition that can organize and mobilize the people from East to West and South to North for change, as time is off the essence. It is then that Opposition political parties make a different in Ethiopia; otherwise we will remain enslaved under Machiavellian ruling of EPRDF/TPLF.

Comments are closed.

Share