/

የአቤ ቶኩቻው ቀኖና 

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)

ባለፈው ሰሞን በፌውብርዋሪ 18 ዕለተ ሰንበት በአቻምየለህ እና በአበበ ቶላ (አቤ ቶኩቻው) መካካል ሕብር ራዲዮ ባደረገላቸው “የትግሬ የበላይነት አለ?” ወይስ “የለም?” ስርዓቱ አፓርታይድ ነው ወይስ አይደለም? ወያኔ የትግራይን የበላይነት ለማስቀጠል፤ለማምጣት የተመሰረተ ነው ወይ? ወይስ አይደለም? የሚል ውይይት አካሂደው ነበር። የሕብር ራዲዮ ጋዜጠኛው ሐብታሙ ጥሩ የሆነ የጋዜጠኛነት ችሎታው ባሳየበት በዚህ የውይይት አያያዛዝ (ምንም እንኳ አቤ ቶኵቻው ጣልቃ እየገባ የታምሩን መልስ ብዙ ጊዜ ሥርዓት ባልተከተለ ቢያደናቅፈውም)።

88201

ሃብታሙ ስርዓቱ የተመሠረተው በዘር መድልዎና ዘረኛ ነው በሚል አቤን በምሳሌ ለማስረዳት ሲል ምርጫ 97 የተደረገ የመታወቂያ ጉዳይ አስመልክቶ ቢያስረዳውመ አልቀበል ሲለው በዜና የተዘገበው የሁለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ታሪክ በማንሳት <<‘አንዱ አማራ’ አንዱ ‘አሮሞ’ የሆኑ ተማሪዎች በማስቆም፤ ‘ፌደራል የሆኑት ትግሬ ወታደሮቹ “ሁለቱንም አቁሞው” አንተ ምንድ ነህ? ‘አማራ’፤ አንተስ? ‘ኦሮሞ’ የሚል መልስ ሲያገኙ “አማራውን” ረሸኑት።  ለምን ገደልከው ብሎ ከመሃላቸው የነበረው አንድ አብሮአቸው የነበረው የፌደራል አማራ የሆነ ወታደር ትግሬ ወታደሮችን ለምን ገደላችሁት ብሎ ሲቃወማቸው፤ ጠመንጃውን አስወርደው እሱንም ጭምር ገደሉት። ኦሮሞውን ተማሪ “አንተ ግን የጀርባ አጥነታችን ነህ” ብለው ለቀቁኝ ብሎ በሰጠው ጋዜጣዊ ምስክርነት ሰጥቷል። ይህ ስርዓት ምንድ ነው የሚባለው? አንድ ሰው በብሔሩ ምክንያት ተለይቶ ሲገደል ምን ትለዋለህ?>>  እያለ ሓበታሙ በዜና የተዘገበውን አሳዛኝ ዜና ለአቤ ቶኵቻው ሊያስረዳው ቢሞክርም “ቀኖናዊ አቁዋም” ስላለው  ከሃብታሙም ሆነ ከአቻም የለህ ከሁለቱም ጋር ሊገናኝ አልቻሉም (ስርዐቱን አፓርታይድ ለማለት አስቸግሮታል)።በጣም የሚገርመው ደግሞ ከላይ የተዘገቡት የግድያ ዜና  ሰምቼአቸው አላውቀም ይላል። የሚገርመው ይህ የቪዲዮ ምስክርነት በቃለ መጠይቅ የተዘገበው ምስክሩ እራሱ ኦሮሞ ነህ እና “የጀርባ  አጥነታችን ነህ” ብለው ሳይገድሉት የለቀቁት ተማሪ ነው። የተዘገበውም እራሱ አቤ ሲሰራበት ከነበረው “ኢሳት” ላይ ተላልፏል። እንዴት ነው ነገሩ!

 

አቤ ቶኩቻው ‘ጭራሽኑ ሰዎች ትግሬው ተጠቃሚ ነው እያሉ ትግሬዎችን ወደ ወያኔዎች እንዲጠጉና እንዲሸሽ እያደረጉት ነው’ የሚል መናኛ እምነቱ እንደመከላከያ አድርጎ ይዞታል። ትግሬዎች መሸሺያቸው ያ ሳይሆን ‘ወያኔን” ከሥልጣን ቦታው ካጣነው አማራ (“ደርግ”) ተመልሶ ሊገዛን ነው የሚል ነው የሚሰጡት ምክንያት (በዓረናው ሊቀመንበር አብርሃ ደስታ ምንጭ መሰረት ደርግ ማለት በትግራይ ሕዝብ እምነት ‘አማራ’ ማለት ነው ብለው የተረጉሙታል ብሎ ነግሮናል)። እንዲያ ሆኖ ግን አቤ ቶኩቻው ለመሸሺያቸው ምክንያት እኛ እንደሆንን ከሳይንስ ትንተና ውጭ የሆነ ሽፋን በመስጠት ተከራክሯል።

የሁለቱን ውይይት ለማድመጥ ይህንን ያድምጡ።

Hiber Radio Special: Abebe Tola (Abe Tokichaw) VS Achamyeleh Tamiru | Tigray | Ethiopia

https://youtu.be/fKx5H9djTF4

የአቤ እምነት  ወያኔ “አፓርታይድ አይደለም ወይንም የሚያዳላ ሥር ት አይደለም መከራከሪያው ምክንያቱን ሲያቀርብ <<ኢሕአዴግ ለማንኛውም ሕዝብ ወገንተኛ ሆኖ አናየውም” ሁሉንም ትግሬውንም ጭምር ይበድላል ይላል። ተጠቃሚ በሚለውም ረገድ አቤ እንዲህ ይላል፦ <<ተጠቃሚዎቹ ወያኔዎች እንጂ ትግሬዎች አይደሉም>> ይላል።

አቻም የለህ ደግሞ በትንሹና በቀላሉ የወታደሮችን ስብጥር ከላይ እስከታች ያሉት ዋና ዋና ቁልፎች 112 ቁልፍ ቦታዎች (ከዚያ በጣም ይበልጣል እኔ እስከማውቀው ዝርዝሩ ላይ ያልተጠቀሱ በርካታ የትግሬዎች ስሞች አሉ) በተቻለ መጠን “እነኚህ ቦታዎች፦—- ህወሓት ወይንም አማራ ፓርቲ፤ ኦሮሞ ፓርቲ… የማንም “ፓርቲ አባሎች” በሚል የሙያ ማሟያ (ክራይቴሪያ) የተቀጠሩ ሆነው ሳይሆኑ “ትግሬዎች” ብቻ ስለሆኑ ነው ያንን ቦታ የተሰጣቸው” ሲል በማስረጃ ሊያስረዳው ቢሞክርም አቤ ቶኩቻው “ሊያምን” አልፈለገም።

እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ያንን ለመከላከል ሲል እንዲህ ይላል <<“በሌላ ዜና ስትሰማ ደግሞ ‘አማራ ብቻ’ እንደተበደለ ተደርጎ ይነገራል፡ በሌላ በኩል ደግሞ ‘ኦሮሞ ብቻ’ እንደተበደለ ተደርጎ ይነገራል። በሌላ በኩል እስር ቤቱ ሁሉ አሮም፤ ኦሮምኛ ይናገራል” የሚል ኦሮሞ ብቻ እንደተበደለ ይነገራል፤፡ ግራ የሚያጋባ ነው፡ ሁሉም ተበድሏል ትግሬዎችም ጭምር”>> ይላል።

አቤ ጋዜጠኛነቱን ረስቶ እንደ ተራ ዜጋ እና እንደተቀሩት ጅላጅል ኢትዮጵያ ምሁራን ክፍሎች የሚከተለውን እምነት አብሮአቸው ሲጋራ እናደምጠዋለን። አቤ እና መሰሎቹ የኦሮሞ እና የአማራ በደል የተለየ መሆኑን አልገባውም። የዘር ማጥፋት የተፈጸመበት “ጠመንጃ ባነገቱ በአክራሪ እስላሞች፤ በኦሮሞዎች እና በትግሬዎች ትብብር “አማራን የጋራ ጠላት በማድረግ” አማራ ላይ ያነጣጠረ ሃይማኖታዊና ጎሳዊ ጥቃት በጠመንጃ፤ በገጀራና በቢላዋ ጥቃት እንደተፈጸመበት የሚያውቅም አይመስልም (አሁንም ድረስ)። ክልል ተብለው ከተከለሉት <ለአካባቢው ነገድ ብቻ የተሰጡ> አፓርታይድ ‘ክልሎች’ ማለትም ከኦሮሞ ቦታዎች፤ ከሶማሊ ቦታዎች ከጉምዝ እየተባረረ የነበረው እና አሁንም ፍዳውን እያየ ጠበቃ ያጣው ያው <አማራ> መሆኑን ሊቀበለው-አልፈለገም።ጥቃቱ እኩል በሁሉም ነው ይላል።

ወያኔዎች ሲገቡ ሶማሌዎች አሮሞዎች ወላይታዎች ሲዳማዎች፤እስላሞች ሻዕቢያ ሳይቀር ‘በወያኔ አዳራሽ’ የሽግግር ወቅት በማን ላይ ነበር ስድቡን ዛቻውን፤የሞራል ድቀቱን ሲሰነዘር የነበረው? በጠራራ ጸሐይ ሲገደሉ፤ ሲታሰሩ፤ ከሥራ ሲባረሩ የነሩትስ ነፍጠኛ የሚል የማጥቂያ ቅጽል ስምስ የተነጣጠረው በማን ላይ ነበር? ግድያው፤መባረሩ፤ውርደቱ በማን ላይ ያነጣጠረ ነበር? በኦሮሞዎች? በእስላሞች? በኤርትራኖች? በትግሬዎች?  በወላይታዎች፤በሶማሌዎች.. ወይስ በአማራ  ላይ ????????!!! እዚህ ዋሺንግቶን የሚኖሮው የእስላሞቹ የፈረስት ህጂራው ሰውየ ወዳጅ የሆነው ጸረ ክርስትያኑ በ<Arab-wannabe syndrome> “በዓረባዊ ብክለት” የሚሰቃየው <<አቡሓይደር>> የተባለው አክራሪ እስላም እንኳ ሳይቀር እርሱና ተከታዮቹ በአቅማቸው ዕድል አግኝተው፤ ወያኔ አይዟችሁ ስላላቸው ‘ቢላል” የሚባል አክራሪ ራዲዮና ቲ/ቪ መስርተው ክርሰትያኑን እና አማራውን በይፋ ሲዘረጥጡት የነበሩበት ወቅት በማን ላይ ይሆን?  <<“አትፍርዋቸው! የኩፍሪል አገር! ኤጭ! እያላችሁ ለኩፍሪሎቹ አትተውላቸው፤ አገሪቷ የኛ ናት! በሞራልም አንኳ አገሪቷ የነሱ እንድትሆን አንፈቅድላቸውም!>> እያለ እስላሙን በክርስትያኑ እንዲነሳሳ ሲያበራታታ የነበረው በማን አይዞህ ባይነት ነው? ይህ የዘረኛነት ስብከት እንዲሰበክ የፈቀደው ማን ነበር? በማንስ ነበር ዘመቻው ያነጣጠረው? አማራው ላይ! አማራና ክርሰትያን በነ አቦሃይደርና ወያኔዎች ለጥቃት የተነጣጠረ ክፍል ነበር። ጥቃቱ በሁሉም ዘንድ ነበር የምትለው አባባል በፍጹም “በሁሉም ዘንድ ያነጣጠረ አልነበረም”።

ሁሉም ተጠቅተዋል የሚለን አቤ ቶኩቻውና መሰሎቹ እነዚህ “ሁሉም” የተባለላቸው የተለያዩ ማሕበረሰቦች (ስክተሮች) “ከባለጊዜው ከወያኔ አፓርታይድ” ቀያሹ ጋር ሆነው አማራውን ፍዳ እንዳሳዩት ከነ ህይወቱ ወደ ገደል እየተገፈተረ ባሰቃቂ ግድያ እንደተዳረገ ጋዜጠኛው አቤ ዜናውን የሰማ አይመስልም። ወያኔ ሥልጣን ከያዘ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ በተለይ ከምርጫ 97 ወዲህ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ‘እስላሞች፤ኦሮሞዎች እና ትግሬዎች’ ጥቃቱ ቀስ በቀስ ወደ እነሱ ሲዞር ‘ሁሉም ተበዳይ’ አድርጎ ከአማራ ጋር እኩል ማቀናጀት  አስገራሚ የጋዜጠኛ ደካማ ብቃት ነው። አቤ ከዚህ ፈቀቅ ብለህ ነገሮችን አጥና።

 

ወደ አቻም እንሂድ። አቻም አቤን እንዲህ ይጠይረዋል። መከላከያ ወታደሩ በሕገ መንግሥቱ መሠረት የማንም ፓርቲ አባል ወይንም ነገድ ክምችት አይደለም የሚል መርሆ አለው! በተግባር ግን የትግሬ ነገዶች በብዛት ቦታውን ይዘውታል (በታሪክ ያልታየ ያልተሰማ)። ይለዋል። ልክ ነው።

አቻም የለህ ሌላው መከራከሪያው ኤፈርት የተባለው የ6 ቢሊዮን ዶላር ባለቤት የትግራይ ሰዎች ተጠቃሚ ሆነው ተቀጥረው የሚገለገሉበት ነው ሲል ፤ አቤ ተኵቻው ደግሞ ‘የወያኔ ንብረት ነው፤ተጠቃሚው ወያኔዎች እና ጥቂት የወያኔ ከርሳም ሆዳሞች ብቻ እንጂ የትግራይ ሕዝብ አይደለም። የወያኔዎች የበላይነት እንጂ የትግሬ የበላይነት አይደለም፤ ይላል።

ጋዜጠኛ ሀብታሙ እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል። <የትግራይ የበላይነት ለማምጣት የመጣ አይደለም አልተጠቀሙም ወይንም የትግራይ የበላይነት የለም የምትለው ማስረጃህ ምንድ ነው? ምንድ ነው መከራከሪያህ? ተብሎ በሃብታሙ ሲጠየቅ፡

<<መሬት ላይ የሚታይ በማስረጃ የተደገፈ ጥናት ተደርጎ እንዲ እንዲህ ብሎ ማሳየት ያስፈልጋል፡ አሁን እኛ ምናያቸው ተከራካሪዎቻችን የሚያቀርቡት ማስረጃ ሥርዓቱ የሚዘግባቸው መረጃዎች ተንተርሰው ነው። አንዳንዶቹም አሳማኝ አይደሉም” አሁን እየተካሄደ ያለው ትግል ዋናው ‘ማጠንጠኛው “የዲሞክራሲ ጥያቄ” ከመጠየቅ ይልቅ “የትግራይ የበላይነት” የሚል ነው። ሲል አቤ ቶኵቻው ደካማ እይታ ይዞ ተከራክሯል። የስርዓቱ መገለጫ ዕጦት ዲሞክራሲ ዕጦት እንጂ አድሎአዊ ሰርዓት የጎሳ ስርዓት አይደለም ሲል ስርዓቱ ፋሺስታዊ የዘር ፖለቲካ ይዞ የመጣ እና ተግባራዊ ያደረገ “የስርዓቱ ማጠንጠኛ፤መገለጫ እና መነሻ ‘ጎሳን’ ያጠነጠነ ዘረኛ/አፓርታይድ/ ስርዓት መሆኑን” አቤ አላወቀም። ጋዜጠኛ ሆኖ እንዴት ይህን የሥርዓቱ መገለጫነት እንደሳተው ገርሞኛል። ያውም አዲስ አበባ የነበረ በጋዜጠኛነት የሠራ። ሠራተኞች በጎሳቸው ከሥራቸው ሲባረሩ፤ ሲገደሉ፤ ሲሰደቡ እንዳላየ ሁሉ! አቤ ተኩቻው “አፓርታይ” ሲተረጉሞው “ዋይትስ ኦንሊ” የሚል ወይንም “ትግሬ ኦንሊ” የሚል ምልክት ካላየሁ በየሬስቶራንቱ “አፓርታይድ” አልለውም ይላል። ይህ አንደኛ ክፍል ተማሪ የሚያውቀው የሴግሪጌሺን ያግላይ መገለጫ አንዷን ብቻ በመምዘዝ። ስርዓቱ አገረቷ በፋሺስቶች አቀያየስ “በክልል” ከልሎ ሲያበቃ እያንዳንዱ ሴጋ በጎሳው እንዲጠራ ማድረጉ የዘር (የጎሳ) ስርኣት ሆኖ በግልጽ ከማወጁ አልፎ ረቂቅና ግልጽ በሆኑ  “ሲሰተማቲክ” አግላይ ስርዓት መሆኑ <እንኳን ለድሮይትዋ ደቡቢትዋ አፍሪካ ለፋሺሰት ኢትዮጵያ አፓርታይድ መንግሥት ደህና መጣችሁ!!!!!> የሚል ማስታወቂያ ቦሌ አየር ማረፊያ ቢሰቀል ስርዓቱን በደምብ ይገልጸዋል።

ከስርዓቱ የሚገኙ መረጃዎች አልቀበልም ስለምትለው መናኛ ክርክር፤ ማስረጃዎች ከሥርዓቱ ማግኘት አንዱ ዘዴ ነው። የወታደሮቹ የበለ ሥልጣኖችብዛት፤ስም፤ማዕረግ፤የያዙት ሥልጣን፤ የደህንንቱ የዳኖቹ ስም ዝርዝር ከነ ማዕረጋቸው ከሥርዓቱ ካልተገኙ ከማን ታገኛለህ? አቤ መከራከሪያህ “ውሸት” ነው “አንዲህ ያለ ማዕረግ ብዛትና አሃለፊነት የለም” ካልክ ከስርዓቱ ውጭ የገኘሃቸው የተሰጠህን ማስረጃዎችን በማፍረስ ማስረጃ አሳየን። ካልሆነ በግድህ ተቀበል።

ስለ ጤና፤ ስለ ትምሕርት፤ ስለ ስልጠና፤ ስለ ፋርማሲ እና ኢንዳስትሪ፤ መገናኛ፤ መብራት አገልግሎት ተጠቃሚነት ኬሎች ነገዶች እየተነጻጻረ ከገለልተኞች (በውጭ አገር በናይጄሪያ አጥኚዎች ሁሉ ሳይቀር የተደገፈ ማስረጃ በራሴ ድረግጽ ተለጥፏል ያንን መመለክት ነው። አርካይቮቹ አሁንም አሉ። የዶ/አሰፋ (ዘ ፒለጅ ኦፍ ኢትዮጵያ መጽሐፍ እና በርካታ የጤና ጉዳይ የሚመለከቱ በሙያው ያጠናቸው የጥናት  ጽሑፎቹ) እና በሞረሽ የተዘጋጀ (ምፅአተ ዐማራ) የሚባሉ መጽሐፍቶችን ማንበብ ማስረጃ ማግኘት ትችላላችሁ (አቤ እነዚህን ገዝተህ ማንበብ ግንዛቤ ይሰጥሃል)። የዶክተር አሰፋ ነጋሽ ጽሁፎች በስሙ ጉጉል ብታደርግ በሕክምና ረገድ የተደረጉ ምርምሮች በነጻ ማንበብ ትችላለህ። ያንን ውሸት ነው ብለህ ና እና ተከራከር። ግን አቅሙ ያለህ አትመስልም።ይሄ ኢሳት የማንበብ ጊዜህን ወስዶብሃል መሰለኝ ብዙ ያነበብክ አትመስልም።

አቤ ቶኩቻንም ሆነ የወያኔ ተቃዋሚዎች ትግሬዎችንም፤ ሆነ የወያኔ አባሎች (ሁሉም በዚህ መስመር አንድ እምነት ስላለቸው)ትግሬዎች ከሌሎቹ ይበልጥ አልተጠቀሙም፤ወይንም የበላይነት የለም ሲሉ በአንድ መስመር ይደመጣሉ። ሃቁ ግን ወደዳችሁ መረራችሁ፤ ሃቁ ትግሬዎች የትም ቦታ የበላይነታቸው ተንሰራፍቶ ይታያል። አስገራሚው ደግሞ ጠላታቸውን የበላይነት የሚያሳዩበትና ጠላታቸውን የሚያስጮሁበት የመግረፍያ (የማሰቃያ) ቦታ ሳይቀር በትግሬዎች ቁጥጥር የተያዘ መሆኑን ለማስረዳት በሚከተለው ሁለት ታዋቂ ሰዎች በሃብታሙ አያሌው እና እንደ እኔው ትግሬ በሆኑት በዶ/ር ሃይሉ አርአያ አባባል ምስክርነት ላስረዳ።

ሓብታሙ አያለው (ወያኔ እስር ቤት ታሰሮ ተገርፎ የወጣ ታሳሪ ነው) እንዲህ ይላል፦

<< እስር ቤት ውስጥ ያሉ ገራፊዎች 99% ትግርኛ ተናጋሪዎች ናቸው። ሲገርፉም በተለያየ ጊዜ እንደተናገርኩት ትግሬ ማለት እንደዚህ ነው፤… ግድግዳ ግፋ እያሉ ሲያስገፉን ይቆዩና እየሞከራችሁት ያላችሁት ይሄንን ነው፤እኛ ማለት እንደዚህ ነን (የማንገፋ ግድግዳዎች) እያሉ ‘ወክለው (እኛ ትግሬዎች እያሉ) ነው የሚነግሩን።>>  ይላል ሃብታሙ አያሌው።

ዶ/ር ሃይሉ አርአያም ይህንኑ በሚገባ አጠናክረው ይመሰክራሉ።

<<“ከቤቴ እየደበደቡና እየተሳደቡ የወሰዱኝ የትግራይ ልጆች ነበሩ። ማዕከላዊ እንደደረስኩ ቀበቶዬን ያስፈታኝ የትግራይ ሰው ነው። ከእርሱ ተቀብሎ አንድ የፍሪጅ ያህል የሚቀዘቅዝ ክፍል አስገብቶ የቆለፈብኝ የትግራይ ሰው ነው። ሲመሽ ሽንት ቤት ወስዶ ያሸናኝ ሰው የትግራይ ሰው ነው። እየተሳደበ ቃሌን የተቀበለኝ የትግራይ ሰው ነው። በእርግጥ እኔ የትግራይ ሰው ሆኜ ከአንድ አካባቢ በወጡ ሰዎች ጥቃት እየደረሰብኝ እንደሆነ ከተሰማኝ ሌላው ሰው ምን ሊሰማው እንደሚችል አስቤ ለትግራይ ህዝብ ከልቤ አዘንኩለት። ይሄ ሁሉ የሚደረገው ለትግራይ ህዝብ ሲባል ነው መባሉ ደግሞ የበለጠ ሰላሜን ነሳው።”>> ምንጭ http://welkait.com/?p=11762

እንግዲህ ይህ የሚያሳየን ትግሬዎች የትም ቦታ ተንሰራፍተዋል ማለት ነው። በትግሬ ስምም ይሁን በሰይጣንም ይሁን በወያኔ ወይንም ባፈለገው የመጠሪያ ስም ይጠሩ፤ እኒዚህ ሰዎች የሚናገሩት ቋንቋ፤ያላቸው ስነ ሉቦና እና ስሜት፤ የመጡበት አካባቢ እና የተወለዱበት ማሕበረስብ ጎሳ ትግሬዎች እና ከትግሬ የመጡ ጎሳዎች ናቸው።ለዚህ ደግሞ የመንጋ (የቡድን/የጎሳ-ስብስብ )ፖለቲካ ውጤት ነው። ባጭሩ ሳይክየትሪስቱ ሃኪም ደ/ር አሰፋ ነጋሽን የሚያስተምረን ነገር እዚህ ልጥቀስ፤

<< የነገድ ማንነትን ይዘው የሚነሱ የመንጋ እንቅስቃሴዎች (crowd movements) እጅግ ጥልቅ የሆኑና የሰዎችን ስሜት ሊኮረኩሩ የሚችሉ ስለሆኑ ተከታዮቻቸውን በስሜት የማሳበድና ህሊናቸውንም የማሳወር አቅምና ክህሎት አላቸው። (Ethno-nationalism has the propensity and quality of fanning affectively or emotionally-charged sentiments among its blind followers).> >

{የአክራሪነትና የጽንፈኝነት ቅኝት የተጠናወታቸው የፓለቲካ እንቅስቃሴዎች ባህርያት – በዶክተር አሰፋ ነጋሽ- ምንጭ welkait.com}

ለዚህ ነው ታሳሪዎችን ‘ግድግዳ ግፉ እያሉ ትግሬ እንደ ግድግዳ የማይገፋ ፍጡር ነው በማለት ህሊናቸው በጎሳ እንቅስቃሴ በመታወሩ ለማመን በሚቸግር ባሕሪ ሲጓዙ በስቃዩ ያለፉ ምስክሮች እነ ሃብታሙና ዶ/ር አርአያ እየመሰከሩ ያሉት።

አሁን አንድ ባንድ እንሂድባቸው።

አቤም ሆኑ ሌሎቻችሁ መገንዘብ ያለባችሁ ይህ የወያኔ አባሎች እንጂ የትግሬ ሕዝብ ተጠቃሚ አይደለም ክርክር መልክ እናስይዘው። ወያኔዎች እነማን ናቸው? ትግሬዎች ናቸው። ወያኔዎች ትግሬዎች እና ከትግሬዎች ወላጆች የተገኙ ናቸው። ትግሬ ማን ነው? ወያኔስ ለመሆን መለኪያው ምንድ ነው?

 

የትግሬነት (የወያኔነት) መለኪየዎቹን በጥቂቱ ልግጽላችሁ።

ትግሬ ማለት ማን ነው? በሕወሓት ፕሮግራም መለኪያ መሰረት፡

በአባቱ እና በእናቱ ወይንም በአባቱ ወይንም በእናቱ ትግሬ የሆነ፤

በትግራዋይነቱ የሚያምን በውጭም ሆነ በውስጥ አገር የሚኖር፤

የትግርኛ ቋንቋውን፤ባህሉን ለማስከበር የሚጥር፤

የትግራይ ጭቆና የሚሰማው፤ ወዘተ….. ወዘተ…

ከሚሉት መለኪያዎች ዋና ዋናዎቹ እነኚህ ናቸው።

የድርጅቱ መሪ ለመሆንም

ሁሉንም ከላይ የተጠቀሱት የትግሬነት ማንነት ትርጉም ያካተተ ሲሆን ከትግሬነቱ  በተጨማሪ፤

በድርጅቱ ዕድሜ 3/4ኛ ዕድሜ የኖረ፤

የትግሬነት ስሜት ያለው

ፀረ-ፊውዳል-ፀረ ካፒታሊዝም፤ፋሺዝም፤ብሔራዊ ጭቆና የሚታገል

ዕድሜው ከ21 አመት በላይ፤ ጥብቅ የማያወላውል፤እና ስነ ሥርዓት አክባሪ የሆነ በዚህ መመዘኛ ለድርጅቱ መሪ መወዳደር ይችላል። ይላል።

እንግዲህ ከላይ ያየናቸው የወያኔ አባልነት መመዘኛ “ትግሬነት” ነው። ትግሬ ያልሆነ ወያኔ ቢሆንም፤ ለድርጅቱ አገልጋይ ለተለየ ጠቀሜታ ተብሎ የተመለመለ ብቻ እንጂ ካልሆነ በስተቀር <<ወያኔ ማለት ትግሬ>> ነው <<ትግሬ ማለት ደግሞ ወያኔ>> ማለት መሆኑን ከዚህ መመዘኛቸው በግልጽ መረዳት ይቻላል።

ትግሬ ሆኖ ከድርጅቱ ጋር የሚቃረን አለ፡ ስለዚህም ሁሉም ትግሬ ተጠቃሚ አይደለም፤ የሚል መከራከያ የሚያቀርቡ አሉ። የወያኔ ተቃዋሚ መሆን ትግሬነትህን እንደማይፍቀው ሁሉ፤ ወያኔነት መሆን ትግሬነትህንም ሊፍቀው አይችልም። ስለዚህ ወያኔዎች እንጂ ትግሬዎች ተጠቃሚ አይደሉም የሚለው ክርክር ወያኔ መሆን ትግሬነትህን እንደማይፍቀው ሁሉ ተጠቃሚነትህ በትግሬነትህ መሆኑን ስለሆነ ወየኔዎች ትግሬዎች ናቸው እንጂ “ወያኔ” የሚባል ከትግሬዎች ውጭ የሆነ ልዩ “ነገድ” የለም።

ወያኔ ስለሆንክ በድርጅትህ ተጠቃሚ ሆንክ እንጂ ትግሬ ስለሆንክ አይደለም የሚለው ደግሞ ልክ አስቀድሜ እንዳለኩት፤ ወያኔ ትግሬዎች የገነቡት ድርጅት እንጂ ከሰማይ የወረደ ድርጅት አይደለም።  ስለሆነም ወያኔ ማለት የትግሬዎች ድርጅት መጠሪያ ነው። እነ ገብሩ እነ አረጋሽ፤ እነ አብርሃ ደስታ፤ አብርሃ በላይ፤ እኔው እራሴ ጌታቸው ረዳ፤ ገብረመድህን አርአያ…ወዘተ… ወያኔዎች ጋር ቅራኔ ቢኖረንም፤ ትግሬዎች እስከሆንን ድረስና ያችን የትግሬነት “መመዘኛ” እስካሟላን ድረስ፤ በማንኛወም ጊዜ ድርጅቱን ለመቀላቀል የሚያግደን የለም።

መመዘኛው ስለምናሟላ በማንኛውም ጊዜ ጥቅም ለማግኘት ከፈለግን የትግሬነት መመዘኛ ስለምናሟላ ስርዓቱ ተጠቃሚ ከመሆን የሚያግደን ነገር የለም። ወሳኙ ወያኔነት ብቻ ሳይሆን ትግሬነት የመጀመሪያው እና

”A must” መመዘኛው ነው። ምክንያቱም ወየኔ ለመሆን ትግሬነት የግድ ነው።

አንድ አማራ/ኦሮሞ/ጉራ/ጋምቤላ ወዘተ… ወደ ወያ”ኔ ልግባ ቢል የአገልጋይነት (ፑፐት) ጠቀሜታ እንጂ እንደ ትግሬዎቹ ተመልሶ “የወያኔ” አባል ሆኖ የድርጅቱ ዋናው የብልቱ ተጠቃሚ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም መመዘኛው አልፋና ኦሜጋው ‘የትግሬ ጎሳ’ መሆን ስለሚጠይቅ። ስለዚህ ወያኔ ማለት ትግሬ፤እንዲሁም ትግሬ መሆን ደግሞ ወያኔ ማለት ነው፤ የምንለው መመዘኛው ትግሬነት ስለሆነ ነው። በመሰረቱ ከወያኔ በፊት የተገኘው ማሕበረሰብ ትግሬ ነው። ትግሬነት ነው ወያኔነትን የፈጠረው። መስራቾቹም ሆኑ መሪዎች እና ተዋጊዎቹ “ትግሬዎች” ካልሆኑ “ወያኔ” ሊመሰርቱ አይቻላቸውምና። ስለዚህ ወያኔ ማለት ትግሬ ነው። ለዚህም ነው መለያነቱ ትግሬነት ስለሆነ “ሕዝባዊ ወያነ ሓርንት ህዝቢ ትግራይ” የሚል ስም የተሰጠው።

“የትግራይ ሕዝብ እና ወያኔ ለየብቻ ናቸው” ማለት ምን ማለት እንደሆነ አቤ እና ብዙ ሰዎች የገባቸው አይመስለም።  ሲጀምር “ሕዝብ” ማለት ምን ማለት ነው? ሕዝብ የግለሰቦች ጥርቅም ቁጥር ማለት ነው። ሕዝብ የሚባል የሚጨበጥ የሚዳሰስ አይደለም። የሚታይ፤ የሚጨበጥ፤ የሚዳሰስ “ግለሰብ” ብቻ ነው። ግለሰቦች ሲከማቹ የሚጠሩበት እንጂ በተጨባጭ ራሱን የቻለ ሕዝብ የሚባል /ጎሳ/ የለም። ያለው ‘ትግሬ/ትግርኛ/ የሚለው ግለሰብ መለያ ብቻ ነው። አንድ ጫካ “ጫካ” ብለን የምንጠራው ጫካ የሚባል ስላለ አይደለም። ጫካ የነጠላ ዛፎች ስብስብ ስለሆነ በዛው እንጠራዋለን እንጂ “ጫካ” የሚባል ከዛፉ የተለየ “ምናብ ነገር አይደለም”።ስለተሰበሰበ ብቻ ነው። የትፍግፍጉ መጠሪያ እንጂ “ልዩ” ነገር አይደለም።

ዛፍ ሲቆረጥ የሚቆረጠው ጫካው ሳይሆን ‘ዛፍ ነው”። ዛፍ ከሌለ “ጫካ” የሚባል መጠሪያ አይኖርም። ሕዝብም ያለ ግለሰብ ሊኖር አይችልም። ስለዚህ ትግሬዎች የሆኑ ግለሰቦች ቁጥራቸው ሚሊዮን ይሁን 10 ሚሊዮን “ግለሰቦች-ናቸው” ። እነዚህ ግለሰቦች “ሕዝብ” ተብሎ የሚጠራው <የትግራይ ሕዝብን> የስብስቡ አባሎች ናቸው። ወያኔ ማለት የድርጅት መጠሪያ ነው። ድረጅቱ የተገነባው ደግሞ በትግሬዎች ነው። የግለሰቦች ስበስብ የሆኑ ላንድ ግብ አብረው ተዋድቀው ወደ ሠልጣን የመጡ ትግሬዎች ናቸው። የተጠቃሚ ብዛት “ሁሉም” ወይንም “ሕዝብ” የሚል ማሰናከያ ውዥምብር  እየተገባ የሚደረገው “ሂፒክሪት’ ክርክር ማቆም አለብን። ድንቁርና ነው። በሕግም በአፈጣጠርም ባንድ ስርዓት በበለጸጉም ባለበለጸጉት አገሮች “ሁሉም ግለሰብ” (ሕዝብ) እኩል እንዲጠቀም እኩል እንዲደሰት የሚጠብቅ ሰው ካለ በሕልም አለም ያለ ብቻ ነው። ሕዝብ የሚባል ልዩ ተደርጎ ግለሰቦችን ከሕዝብ ውጭ እየተደረገ የሚተረጎም ትርጉም “ኮሚኒስታዊ’ ነው። ኮሚኒስቶች በሕብ/በቡድን/በስብሰብ/ የበላይነት ስለሚያምኑ ግለሰቦች ሲጠቀሙ የነገዱ /የሕዝቡ አባል መሆኑን ይዘነጋሉ። በፍጠረትም በሚዛናዊ ፍርድም ‘ቅድሚያ” የሚሰጠው (ሪኮግኒሽን) ለግለሰብ ነው። ምክንያቱም ሕዝብ የግለሰቦች ስበስብ መጠሪያ ስለሆነ። ግለሰብ ተጠቃሚ ሲሆን የዚያ ማሕበረሰብ ነገድ “ግለሰብ” ተጠቃሚ ነው።

ወያኔ ስርዓቱን ይዞታል። ወያኔዎች ስንል በሺዎች ብቻ የሚቆጠሩ አይደሉም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አባሎችና ደጋፊዎች ናቸው። ወያኔዎች ደግሞ “ትግሬዎች” ናቸው።ግለሰቦች ናቸው። ትግሬዎች ናቸው። ስለሆኑም በመመዘኛው መሰረት ትግሬነት ስለሚጠይቅ በትግሬነታቸው ተጠቃሚዎች ሆነዋል። እኔ የማውቃቸው ሰዎች “የወያኔ አባሎች ሳይሆኑ” በባለስልጣኖች ዝምድና ብቻ ተንሰራፍተው ሲፈልጉ ውጭ አገር ሲፈልጉ አገር ውስጥ ተንደላቅቀው ሃብት አከማችተው የሚኖሩ እኔ የማውቃቸው ሰዎች አሉ። ይህ የሚያሳየው ትግሬዎች የበላይንቱን ስለያዙ ትግሬዎች ተጠቃሚነታቸው ከሌሎቹ እጅግ የጎላ ዕድል አላቸው።

በዚህ ማሳረጊያ ልደምድም።

ለምሳሌ በየ 10 አመቱ የሚደረግ የሕዝብ ቆጣራ ትግራይ ውስጥ ሲደረግ የሕዝብ ቆጠራ ትብሎ ይጠራ እንጂ የሚቆጠሩት እና ወሳኝ የሖኑት ግለሰቦች ናቸው። ሕዝብ አይቆጠርም፤የሚቆጠር ሰው ነው/ግለሰብ/ ትግሬ የሆነ ግለሰብ። የወያኔ አባሎች (የወያኔ ጎሳ) ተብለው ነው የሕዝብ ቆጠራ የሚደረገው? ወይስ “ትግሬ” በሚል የጎሳ የሕዝብ ቆጣራ? እያንዳንዱ ትግሬ “ወያኔ” ተብሎ ሳይሆን ‘ትግሬ” በሚል ነው የሕብ ቆጠራ የሚመዘገበው። ስለዚህም ነው ወንድሞቼና እህቶቼ “ወያኔ” ማለት ድርጅት እንጂ ሰዎቹ “ትግሬዎች” ናቸው የምንለው። ስለሆነም ተጠቃሚዎቹ ወያኔዎች ሳይሆኑ ትግሬዎች ናቸው። ወያኔ የሚባል ጎሳ ስለሌ ማለት ነው። ትግራይ ውስጥ መታወቂያ ላይ ዜጋ እንጂ “ብሔር” የሚል የለም ይባላል (አውነት ከሆነ)። በዚህ መልክ ብንሄድ፤ የወያኔ ትግራይ መንግሥት መታወቂያ ደብተር ላይ “ብሔር” በሚል መጠይቅ ላይ “ትግሬ” ነው የሚለው ወይስ “ወያኔ” ነው መባል ያለበት? የፖለቲካ ድርጀት እና ሥራ የሚል ሲኖር ደግሞ “ወያኔ” ሜጀር ጄኔራል (መከላከያ) ይላል፤ አይደለም እንዴ?

“አስገራሚ የቶኩቻው ነጥብ ደግሞ “ትግራይ በዘመነ ወያኔ ተጠቅሟል ስለሚባል ለጥቃት ክፍት እየሆነ ነው፤ወይንም ወደ ወያኔዎች ደጋፊ እንዲሆን ማድረግ ነው” ሲል ደምድሟል። ይህ አባባል የትግራይ ወያኔ አባባሎችም ሆኑ ወየኔን የሚቃወሙ ትግሬዎች ይህ የአቤ ቶኵቻው ውንጀላ የሚያስተጋቡት ደካማ ሙግት ነው። አለፍ ብለው በቁጣ የተጠቁ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ? ይህ ባሕሪያዊ ነው።የተቆጣ ሕዝብ ሲኖር ሕዝባዊ አመጽ በስርዓት የሚመራው ቡድን/አካል እስከሌለ ድረስ ድብቅም ሆነ ይፋ አስተባባሪ እስከሌለ ድረስ እንቅስቃሴዎች ከግባቸው በላይ በመሄድ “ዱርየዎች” ንብረት መዝረፍ፤ የተቆጡ ግለሰዎችም “በንጹህ ላይ ጥቃት ማድረስ” ያለ እና ባህሪያዊ ሊከሰት የሚችል አሳዛኝ ግን መከላከል የማይቻል “ያልተገራ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ” ውጤት የሚታይ ክስተት ነው።

ቢሆንም ባጠቃላይ አገላለጽ ግን የሥርዓቱን ደጋፊዎች እና ተጠቃሚዎች ሕዝቡ ከአበበ ቶኵቻና ከተጠቀሱት አባሎች በላይ አብሮ የሚኖር ስለሆነ ማን ምን እያደረገ እንደሆነ፤ምንስ እንደተጠቀመና እንዴትስ እንደሚኖር የመረዳት ችሎታ ስላለው እኛ የትግራይ ሕዝብ ተጠቃሚ ነው ስላልን የትግራይ ሕዝብ በግፍ ለአደጋ እያጋለጣችሁት ነው የሚለው ውንጀላችሁ እናንተም ሆናችሁ የወያኔ አባሎች ያደረጋችሁት ማስረጃ ካለ ለመስማት ዝግጁ ነን። ትግሬው “ተጠቃሚ ነው አትበሉ” ካልሆነ በዚህ መንገድ ‘ዝም ልናሰኛችሁ ነው’ የሚለው መሟገቻ ማስረጃ እጥረት ከመሆን ያለፈ ዘዴ ከመሆን-አያልፍም።

አቤ ቶኵቻው የትግራይ ተጠቃሚነት እና የበላይነት አቻም የለህ በመለስተኛና በቀላል መልኩ ለማስረዳት ቢሞክርም አቤ ቶኲቻው “አንዴ” በቀኖና መስመር ስለቆመ ሊያምን አልቻለም። የበላይነቱ በኢኮኖና በወታደራዊ እና በፍትሕ ተቋማቱ ብቻ ሳይሆን የትግሬዎች የበላይነት የሚታየው፤ በሚዲያውም አለ። አቤ አዲስ አበባ ነበርክ? አዎ እዛው ተወልደህ አድገህ ጋዜጠኛ ነበርክ (ካልተሳሳትኩ)። ጋዜጠኛነትህ ግን ውሃ በልቶታል። የትግራይ የበላይነትን እንደገና እንድታየው አንተ በጋዜጠኛነት ሙያ የተሳተፍክበት የሥራ ሙያ በእነ ማን እንደተያዘ በማስረጃ ላሳይህ።

የኢትዮጵያ (ኢ ቢ ሲ) ተብሎ የሚጠራው በትግሬዎች/ኤፈርት/ የሚተዳደረው ቴ/ቪዥን ከ እስከ ውስጥ የሚሠሩት በአነስተኛ ቁጥር 25ቱ ትግሬዎች ናቸው። (ቴቪዥን ብቻ ነው እየገለጽኩልህ ያለሁት) ከምኒስትሩ ዘርአይ አስገዶምን እና በስሩ ያሉት ሌሎች ዘርፎችን ሳያካትት፤-.. ከ ቴ/ቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ጀምሮ እስከ ቴ/ቪዥን ፎቶ ቀራጭ ትግሬዎች ናቸው። አቤ ይግረምህ እና ይህንን ልጨምርልህ፡ “በአማራ ቴ/ቪዥን 4ቱ ትግሬዎች ሲሆኑ”  እንደገና “ደቡብ ቴ/ቪዥን 2ቱ ትግሬዎች” ናቸው። ስም ስማቸውን ከፈለግክም በሞረሽ የተጻፈ  {ምጽአተ አማራ} የሚለው መጽሐፍ በገጽ 595 የ25ቱ ሰዎች ስም ዝርዝር ተዝግቧል። የትግራይ የበላይነት በኢትዮጵያ ቴ/ቪዥን ታሪክ ታይቶ ታውቋል? መልሱ ከአቤ ቶኵቻው እንጠብቃለን። እንዳይበዛባችሁ እዚህ ላቁም እና ስለ ተቀሩት ነጥቦች በሚቀጥለው ክፍል ሁለት እንመለስበታለን። ይቀጥላል…….

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮፕያን ሰማይ አዘጋጅ)