በትግራይ እንደርታ ሙስናን ያጋለጠ የሕወሓት አባል ተባረረ

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ እንደዘገበው፦
በትግራይ እንደርታ ወረዳ ነው። የህወሓት አባላት የሆኑ የወረዳው አስተዳዳሪዎች (የዞኑ ሓላፊ ባለበት) እርስበርሳቸው እየተገማገሙ ሳለ አንድ አባል የወረዳው አስተዳዳሪ የ10 ሺ ብር ሙስና ከህዝብ መቀበሉ ያጋልጣል።
የህወሓት ባለስልጣናትም እርስበርስ ተነጋግረውና ተባብረው የ10 ሺ ብር ሙስና ያጋለጠ አባል እንዲባረር ወሰኑ። ተባረረ። አዎ! አብዛኛው አባል በሙስና ከተጨማለቀ የቅጣት ሰለባ የሚሆን ሙስና ያልሰራ ሰው ነው።
ህወሓቶች ሙስና ያጋለጠ አባል ከአባልነት በማባረር ድርጅቱ የሙስና ካምፕ ለማድረግ ያሰቡ ይመስላል። መቼም ሙስና የሚያጋልጡ ሰዎች በማራቅ ሙስናን ማንገስ እንጂ መታገል የሚቻል አይመስለኝም።
ለነገሩ ህወሓቶች ሙስናን ላለመጋለጥ ተስማምተው የለ። ሙሰኛ መቅጣት ከተጀመረ ማን ማንን ሊቀጣ? አስቸጋሪ ነው። ሙሰኛ ለሙሰኛ እንዴት መቅጣት ይቻለዋል? እንደውም ሙሰኞች ተሰባስበው ሙሰኛ ላልሆነ አባል መቅጣት ይቀላቸዋል። እንዲህም እያደረጉ ነው።
ሙሰኛ ስርዓት ሙስናን መቃወም አይችልም። ምክንያቱም ሙስና ለማጥፋት ሙሰኞች ማጥፋት ግድ ይላል። ለገዢዎች ራስ ማጥፋት ከባድ ነው።

የሕዝብ አስተያየት፦

ታዲያ በዚህ ዓይነት እንዴት አዜብ መስፍንን ማጋለጥ ይቻላል?


ተጨማሪ ያንብቡ:  ሞላ አስገዶም ከኤርትራ የከዱት ከሰባቱ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ብቻቸውን በስምንት ላንድ ክሩዘር ከወታደሮች ጋር መሆኑ ተገለጸ፣ አገዛዙ አስቀድሞ ግንኙነት እንደነበረው መግለጹ ለሞራሉ የፈጠረው መሆኑም ተጠቆመ፣ የህወሓት ባለስልጣናት ሲያደርጉት የቆዩትን የስልጣን ሽኩቻ ተከትሎ በደህነቱ መ/ቤት አንዱ የአንዱን ደጋፊ ወደ ማጥቃት መሸጋገራቸው፣ በአገር ቤት የበዓል ገበያው ማሻቀብና የነገሰው ውጥረት መላ ካልተበጀለት አገሪቱን ወደ አደገኛ ሁኔታ ሊከት ይችላል መባሉ፣ የመንግስታቱ ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ ለሚሄዱ የውጭ አገር ሰዎች ያወጣው ማስጠንቀቂያ፣ ቃለ መጠይቅ ከቴዲ አፍሮ የፌስ ቡክ ኮንሰርት አዘጋጆች አንዱ እና ከጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ በአገር ቤት ስላለው ሁኔታ እና ሌሎችም

1 Comment

Comments are closed.

Share