የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት ተማሪዎች በግድ ዩኒቨርሲቲው እንዲለቁ ተደረገ

(ዘ-ሐበሻ) በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የሳይንስና ቴክኖሊጂ ተማሪዎች አስተዳደሩ COC (ፈተና) እንዲወስዱ በማስገደዱና ተማሪዎቹም ካለምንም ዝግጅት አንፈተንም፤ ጊዜ ሊሰጠን ይገባን በሚል ያነሱት አለመግባባት እየተካረረ ሄዶ ተማሪዎቹ በግድ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን ከስፍራው ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ።

ተማሪዎቹ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ይህን ፈተና ድንገት መውሰድ የለብንም ከተማሪዎቹ መካከልም 30 በመቶ የሚሆኑት ውጤት በማጣት ከትምህርት ገበታቸው ሊፈናቀሉ ይችላሉ በሚል ስጋት ለማጥናት ጊዜ ይሰጠን ቢሉም የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ከትናንት በስቲያ ምሳ እንደከለከልና ትናንት ጠዋትም ቁርስ ከከለከለ በኋላ አለመግባባቱ ተካሮ በመሄድ ማምሻውን ደግሞ ማደሪያም በመከልከሉ ተማሪዎቹ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ መደረጋቸውን የአይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ ካለምንም ህጋዊ ማስታወቂያ በአስተዳደሩ ሳቢያ በግድ ከዩኒቨርሲቲው ከወጡ በኋላ በአካባቢው ባሉ ቤተክርስቲያኖች፣ ሆቴሎችና በየሰው ቦታ እንደተጠጉ ተገልጿል።

ዘ-ሐበሻ ጉዳዩን ተከታትላ ትዘግባለች።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራ አስፈላጊነት በህዳሴው ግድብ ዙሪያ

2 Comments

  1. Mamo ante woyane ansemaheme anteme belo mekari woyane facebook laye kemegolet atatenume nebere mejemeriya erasken mekire

Comments are closed.

Share