/

በጎንደር የቀድሞ አንድነት ፓርቲ አመራር የነበረችው ቀለብ ስዩም ዛሬ የ4 ዓመት የእስር ቀጣት ተወሰነባት

keleb
በፀረ ሽብር ህጉ አንቀፅ 7(1) ክስ የተመሰረተባት ቀለብ ለአንድ አመት ከ11 ወር ያክል በእስር ቆይታለች።
በፅሁፍ ከቀረበ የደህንነት የስልክ ሪፓርት ውጪ ማስረጃ ያልቀረበባት ቀለብ፤ የተከሰሰችበት አንቀፅ እንድትከላከል በአብላጫ ድምፅ ተበይኖ ከተከላከለችም በኋላ በዛው አንቀፅ በአብላጫ ድምፅ ጥፋተኛ መባሏ ይታወሳል።
ቀለብ በእነ ተፈራ በላይ መዝገብ 6ኛ ተከሳሽ ስትሆን የተቀሩት ተከሳሾች እንዲከላከሉ ከተበየነ በኋላ አንከላከልም በማለታቸው 4ዓመት ከ5 ወር የእስር ቅጣት ተወስኖባቸዋል።

 

Source:  ET Court Hearings – የፍርድ ቤት ውሎዎች

የሕብር ራድዮ የዛሬ ዜናዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ