Hiber Radio: ወያኔ ከመውደቁ በፊት ተቃዋሚዎች በጋራ ተባብረው በአስቸኳይ የጋራ ራዕይና አጀንዳ እንዲቀርጹ ሕዝቡ ተጽዕኖ እንዲያደርግባቸው ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ጠየቁ፣የሕወሃት/ኢሕአዲግ የመከላከያ ጦሩን ለሶስተኛ ጊዜ ከደ/ሶማሊያ ጠራርጎ ወጣ፣አልሽባብም አካባቢውን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ዛሬ ይፋ አደረገ፣በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ወደ አገር ቤት በሚልከው ዶላር ላይ ዕቀባ በማድረግ የወያኔን የግፍ አገዛዝ በኢኮኖሚ እንዲያዳክም ጥሪ ቀረበ፣አሜሪካ ዜጎቿ ወደ ኢትዪጵያ ከመጓዛቸው በፊት እንዲጠነቀቁ መመሪያ አወጣች፣ አዲስ አበባ ያለው ኤምባሲዋ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሳቢያ ስራዬን መስራት አልቻልኩም አለሌሎችም

/

የህብር ሬዲዮ ጥቅምት 13 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…በውጨ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ለዚህ የግፍ አገዛዝ ምዕራባውያን ከሚለግሱት በላይ ዶላር ወደ አገር ቤት በየዓመቱ ይልካል ከእሱ ያነሰ ጉልበት ወዳላቸው ምዕራባውያን ተሰልፎ ገዳዩን ስርዓት አትርዱ ይላል ይሄን ዶላር ለተወሰነ ጊዜ መንፈግ ቢቻል ስርዓቱን በኢኮኖሚ ማዳከም ይቻላል…> አክቲቪስትና ጋዜጠኛ ዘሪሁን ተስፋዬ በቅርቡ ይፋ ያደረጉትን በወያኔ ላይ የዶላር ማዕቀብ በማድረግ ስርዓቱን ማዳከም ስለሚቻልበት ስትራቴጂ ለህብር ከሰጠው ቃለ መጠይቅ (ቀሪውን ያዳምጡት)

<…ወገኖቻችንን የሚገድለው ስርዓት ለመሳሪያ መግዣ ዶላር የሚያገኘው እኛም ከምልከው ነው። ቤተሰብ ሳይጎዳ የህዝቡን ትግል በመደገፍ ተጽዕኖ መፍጠር ይቻላል…ወደ አገር ቤት የሚላከው ዶላር ለቤተሰብ ይላክ እንጂ ከየቦታው ተሰብስቦ ወያኔ ጋር ይደርሳል:፡ ገንዘቡ ለጊዜው ቢቋረጥ ወይ ቢቀንስ በቤተሰብ ላይ ተጽዕኖ አያመጣም። ይሄን በጥናት አረጋግጠናል።ነገር ግን በተለምዶ የሚባለው ከዚህ የተለየ ነው…> አክቲቪስት ተጉዋዘ ብርሃኑ ከዲሲ ግብረ ሀይል በጋራ ስለ የዶላር ማዕቀቡ ዘመቻ ከዲሲ ግብረ ሀይል ስለዘመቻው ከሰጠን ቃለ መጠይቅ(ቀሪውን አዳምጡ)

<…በዲላ፣በይርጋ ጨፌ፣በወናጎና በሌሎችም አካባቢዎች ዜጎች ተወልደው ከኖሩበት ቀዬ በተወሰደባቸው ጥቃት ብዙ የሰው ሕይወት ጠፍቷል በአሁኑ ወቅት በየቤተ ክርቲያኑ በየመስጊዱ የተጠለሉ የት እንዳሉ የማይታወቁ አሉ ዜጎች በዚህ ጥቃት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገለዋል አሳዛኙ ደግሞ ይሄ መረጃ ታፍኗል…የእኛ ጥረት ይሄ ሜዳ ላይ የተበተነው የሚሄድበት ያጣው ንብረቱ ፣ቤቱ የወደመበት ከልዩ ልዩ ብሄረሰብ የተውታጣው ወገናችንን ቢያንስ በተወሰነ አስተዋጽዎ ለመርዳት ነው..> አቶ መድሃኒት ሳሙኤል በቅርቡ በደቡብ ክልል በዲላላ በተለያዩ አካባቢዎች ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ስለደረሰው ጭግርና ስለ ጀመሩት የእርዳታ ጥረት ከሰጠው ማብራሪያ(ቀሪውን ያዳምጡት)

ተጨማሪ ያንብቡ:  "ጠላት አለኝ ከሚለው የደጀን ኃይሉ እየራቀ በመጣ ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ወደ ወጥመዱ እየገባ ነው"፦ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ

<…በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለበርካታ ጊዜ እየተሰለፉ ለምዕራባውያን ያቀርቡት የነበረው አቤቱታ ይሄ አገዛዝ ላይ ተገቢውን አቁዋም እንዲይዙ ለማድረግ ነበር አሁን ተፈላጊው ከምዕራባውያን ተገኝቷል። ዛሬ መሰለፍ የሚያስፈልገው ወያኔ መውደቁ አይቀርም ከዚያ በፊት ተቃዋሚዎች ተባብረው የጋራ አጀንዳ እንዲቀርጹ ነው ።ሕዝቡ የተቃዋሚ መሪዎች ላይ ተሰልፎ ተባበሩና በጋራ አጀንዳ ቅረጹ ተባበሩና ምሩን ማለት አለበት። እነ ዶ/ር ዲማን እነ ዶ/ር ብርሃኑን ተባበሩና ምሩን ማለት አለበት..> ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ቪዥን ኢትዮጵያና ኢሳት ተባብረው ባዘጋጁት ጉባዔ ላይ ከተናገሩት በከፊል(ያድምጡት)

<…አክቲቪስትና አርቲስት ታማኝ በየነ በተገኘበት በዚህ ጉባዔ ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ ብሄረሰብ የተውጣጡ የማህበረሰብ መሪዎች በተገኙበት ልዩነትን አቻችለው በጋራ ተወያይተዋል። ይሄ ውይይት በየቦታው መቀጠል አለበት..> አቶ ደረሰ ለማ በሚኒሶታ የጽናት የውይይት ፎረም ሊቀመንበር ትላንት በሚኒሶታ ስለተደረገው ጉባዔ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ(ቀሪውን አድምጡት)

ከሁለቱ አሜሪካውያን ዕጩ ፕሬዝዳንቶች ማናቸው ቢመረጡ ለኢትዮጵያውያን አገራዊ ጉዳይ ጠቃሚ ነው ውይይት ከዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን ከቬጋስ አቶ ከባዱ በላቸው ከዋሽንግተን(ያድምጡት)

በኢትዮጵያ በተከሰተው ህዝባዊ ተቃውሞ ሳብያ እርሻቸው ከጥቃት የተረፈው ሆላንዳዊው ባለ ሀብትስለ ተሞክራቸው ይናገራሉ( ልዩ ጥንቅር)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ተቃዋሚዎች በጋራ ተባብረው በአስቸኳይ ወያኔ ከመውደቁ በፊት የጋራ ራዕይና አጀንዳ እንዲቀርጹ ሕዝቡ ተጽዕኖ እንዲያደርግባቸው ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ጠየቁ

የኢሕአዲግ የመከላከያ ጦሩን ለሶስተኛ ጊዜ ከደ/ሶማሊያ ጠራርጒ ወጣ

አልሽባብም አካባቢውን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ዛሬ ይፋ አደረገ

በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ወደ አገር ቤት በሚልከው ዶላር ላይ ዕቀባ በማድረግ የወያኔን የግፍ አገዛዝ በኢኮኖሚ እንዲያዳክም ጥሪ ቀረበ

አሜሪካ ዜጎቿ ወደ ኢትዪጵያ ከመጓዛቸው በፊት እንዲጠነቀቁ መመሪያ አወጣች

ተጨማሪ ያንብቡ:  አዲሱን አመት ከወለጋ ተፈናቃዮች ጋር - ገለታው ዘለቀ (ደብረ ብርሃን_ኢትዮጵያ)

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የእለት ስራችንን እንዳናከናወን

እንቅፋት ሆኖብናል” በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኢምባሲ

የሕወሓት አገዛዝ በቅርቡ ማንነቱ የተጋለጠበትን የቀድሞ የፌዴራል ፖሊስ አዛዥ ከአዲሱ የኦሮሚያ ክልል ሹመት አገለለ ሌሎች ያልተጋለጡ ጭምር ተሹመዋል

ኢትዮጵያዊያኖች በአውስትራሊያ ታላቅ ስላማዊ ስልፍ አደረጉ

“አውስትራሊያ አሽባሪው የኢሕአዲግ አገዛዝን መርዳት የለባትም“አቶ ኑሩ ስይድ በፐርዝ የኦሮሞ ኮሜኒቲ ተወካይ

“ኢሕአዲግ ስልጣኑን በጠመንጃ ሀይል ለማቆየት እየተጣጣረ በመሆኑ አውስትራሊያ ግንኙነቷን ማቋረጥ ይገባታል“አቶ ኦማር ሀስን የኦጋዲን ማህበረስብ ተወካይ

የአሜሪካው ፕ/ታዊ ተወዳዳሪ ዶናልድ ትራምፕ በቀጣዩ 100 ቀናት ውስጥ ስለሚያካሄዱት እርምጃ ይፋ አደረጉ

“ከዚህ በሁዋላ በትራምፕ ዙሪያ አስተያየት በመስጠት ጊዜዪን አላባክንም“ሂላሪ ክሊንተን

ሌሎችም

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas/hiber-radio-102316
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Share